(ክፍል ሦስት – ከክፍል 2 የቀጠለ) Adam Reta

….  አለም በቃኝ ያለው አዲስ አባ ከርቸሌ ነው (ምንም እንኳን በዘወትር ቃል አጠቃቀም ‘እከሌ ከከርቸሌ ወጣ’ አንልም። ‘ወረደ’ ነው። አዘቅት ነው)። ከከርቸሌ በኋላ አስኮ የሰዎችን የአሰፋፈር ስልት ተከትሎ በየትም ደረጃ ባሉ ከተሞች ይኖራል ብለን በምንገመተው የቁጥጥር ጫማ ስር ያርፋል። በአጭሩ የጭቆና ሪትም ወይም ምት አለ።

አስኮ ጌታሁን “አንዳንዴ እንኳን ሳላስበው ዓለም ሰፊ አፍ፣ ሰዎች ሁሉ ጥርሶቿ ይመስሉኛል” (አንቀጽ 12) ሲል ዓለም ማለቱ አገሩን ነው። የልምዱ ስፋት ፕላኔታዊ አይደለም።

በተዋረድ በሚሰራ ዘመናዊ አስተዳደር ባለው አንድ ሉዓላዊ ክልል የተክለሃይማኖት አደባባይ የተለዋጭነት እሴት (Metaphorical Value) ሰፊ ነው። ተክለ ሃይማኖት ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ናቸው። ከእስር ቤት ሲወጣ የተጠለለው እሳቸው በተሰየሙበት ደጀ ሰላም ነው። ህብረተሰቡ ከገነባቸው መንፈሳዊም ይሁን ዓለማዊ መሸሸጊያዎች ለአስኮ ያዳላ ወይም በሩን የከፈተ የለም። አላመለጠም። አስኮ ቦታ ቢለዋውጥም ያለበት የህልውና ስፍራ አንድ ነው። በሕይወት ጎዳና ሲጓዝ ተመልሶ የመጣው ወደነበረበት አዲስ አባ ነው። ክብ ነው።

ይሄ ስለ ጭቆና ሁሉ ቦታ መኖር (Omnipresence) ብቻ ሳይሆን ስለ ቦታ ምት ይነግረናል።

ከታሪኩ ጀርባና ፊት እየተወሰወሰ ከመጣው የጭቆና ስልት ጋር አብረው የሚነቃነቁ ድርጊቶች አሉ። አንዱ ጫማ ስራ ነው። ሁለተኛው የማይሳትና ቁልፍ የሆነው ‘ታስፈሩኛላችሁ’ የሚለው ቃል ነው። ይሄ ቃል ውይይት (Dialogue) ተከትሎ አልመጣም። ምክንያቱም ውይይት ሊደረግ የሚቻልበት ሁኔታ አይደለም። በዚያን ‘ነጠላ’ ወቅት ባየው ነገር ተገርሞም አይደለም። ከሃያ አመት ልምዱ ነጥሮ የወጣ ቃል ነው።

ይሄ ቃል ታሪኩ ውስጥ አራቴ አለ።

አንደኛው በክፍል አንድ (ሰሌዳ ) ላይ (ሁለት ጊዜ)፣ ሁለተኛው ታሪኩ መዝጊያ ላይ (ሰሌዳ ሀ’) (ሁለት ጊዜ)። በዚህ ሂደት በሁለት ሰሌዳዎች ( እና ) ላይ የሰፈረው ታሪክ ውህደት ያገኛል። ተራኪው ትረካውን በ ለ-ሀ-ሀ’ ሞዴል ቢሰራው ኖሮ በድርሰቱ ውስጥ ያለው ጥብቀትና ትስስር ይጠፋ ነበር።

ድግግሞሽ እዚህ የቋንቋና የኩነት ነው። ‘ታስፈሩኛላችሁ’ ቃል ነው። በተደራቢም በአካላዊ ንቅናቄ የሚሰራ በመሆኑም ኩነት ነው። አንዱ ምዕራፍ ወይም ሰሌዳ ከሌላ ሰሌዳ የመጣውን ድምጽ ተቀብሎ ማሚቶ እንደሰራም ይቆጠራል። ኤሚሌ ዞላ ‘ምት ለድርሰት አካልና ጠንካራ ትስስሮሽ ይሰጠዋል’ ይላል፤ ወይም አንድ ሀሳብን ወይም ስሜትን ያጠናክራል።

ጫማ ስራ በሁለቱም ሰሌዳዎች (ሀ/ለ) ለአስኮ ችግር መቅረፊያ የኢኮኖሚ መሳሪያዎች ናቸው። ከሰሌዳ “” ላይ ግን የተለየ ሁኔታ ይከሰታል። ጫማ መስራቱን እንደ ሰሌዳ “” ለራሱ መጠቀሚያ አያደርግም። ለሚሰራው ስራ የሚቀበለው ክፍያ ለምስማሮቹ መግዣ የሚበቃውን ያህል ብቻ ነው (አስኮ እንደሚለው)።

ዝርዝር ጽሁፉን አስፈንጣሪውን በመጫን ያንብቡ  andemta.com

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *