“Our true nationality is mankind.”H.G.

በድርደሩ-ኢህአዴግ አጀንዳ አደራጅና የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ሆነ

ከጅምሩ ንትርክን አለመግባባት የበዛበት፣ ከሁሉም የተሻለ የሚባለው መድረክና ዋናው ተቃዋሚ ኦፌኮ  ራሳቸውን ያገለሉበት የፖለቲካ ፓርቲዎች ” ድርድር” የተለያዩ አመራሮችን ሰየመ። ኢህአዴግ የአጀንዳ አደራጅ እና የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ኮሚቴም መሪነቱን እንዲወስድ ተደርጓል።

ለዘጠነኛ ጊዜ በተካሄደው ስብሰባ ኢህአዴግ የአጀንዳ አደራጅ እና የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ኮሚቴም መሪነቱን በቀጥታ እንዲወስድ የተደረገው “እህአዴግ ድርድሩን የጠራ በመሆኑ” እንደሆነ የፋና ዘገባ ያስረዳል። በዚሁ ውሳኔ መሰረት ኢህአዴግ የድርድሩ ዋና ተግባር የሆነውን የአጀንዳ ቀረጻ እንዲሁም  የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራውን ይመራል።

ፋና የሚከተለውን ዘግቧል –

ፓርቲዎች በቀጣይ ለሚያካሂዱት ውይይትና ድርድር ሶስት አባላት ያሉት አደራዳሪ መረጡ

ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ ለሚያካሂዱት ውይይት እና ድርድር ከመካከላቸው በቋሚነት የሚያደራድራቸው ሶስት አባላት ያሉት አደራዳሪ መርጠዋል።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ባካሄዱት ዘጠነኛ ዙር ስብሰባ ላይ አደራዳሪዎቹን የመረጡ ሲሆን፥ አደራዳሪው ሶስት አሊያም አምስት አባላትን ያቀፈ ይሁን የሚል ሀሳብን በአማራጭነት አቅርበው ነበር።

በአደራዳሪዎቹ ቁጥር ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላም ሶስት አደራዳሪዎች እንዲሆኑ በመስማማት በእጩነት ከቀረቡላቸው አምስት ሰዎች ሶስቱን ለአደራዳሪነት መርጠዋል።

በዚህም መሰረት አቶ አሰፋ ሀብተወለድ ከመኢአድ የአደራዳሪው ሰብሳቢ፣ አቶ ዋስይሁን ተስፋዬ ከኢዴፓ የአደራዳሪው ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ አለማየሁ ደነቀ ከአትፓ የአደራዳሪው ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።

Related stories   ‹‹የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም አለው፤ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠነክራል››

በአደራዳሪነት የተመረጡት ግለሰቦች በድርድሩ ሂደት የአደራዳሪነት ሚና ብቻ ሚጫወቱ ሲሆን፥ የፖቲካ ፓርቲያቸውን በመወከል በተደራዳሪነት የማይቀርቡ መሆኑም ተገልጿል።

በተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የአጀንዳ አደራጅ እና የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ኮሚቴም በዛሬው ስብሰባቸው መርጠዋል። በምርጫው ወቅትም ፓርቲዎቹ እህአዴግ ድርድሩን የጠራ በመሆኑ በአጀንዳ አደራጅ እና የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ኮሚቴ ውስጥ በቀጥታ እንዲሳተፍ ተስማምተዋል።

ቀሪ ሁለት የኮሚቴው አባላትን ለመምረጥም አራት እጩዎች የቀረቡ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱን በድምፅ ብልጫ መርጠዋል። በዚህም መሰረት አቶ ገብሩ ብርኸ ከኢፍዴኃግ የኮሚቴው ሰብሳቢ ሆነው ሲመረጡ፥ አቶ አስመላሽ ገብረስላሴ ከኢህአዴግ እንዲሁም አቶ መላኩ መሰለ ከኢራፓ የኮሚቴው አባላት ሆነው ተመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲዎቹ በዛሬው ውይይታቸው ሶስት አጀንዳዎች ላይ የተወያዩ ሲሆን፥ በ8ኛው ዙር የተደረገ ውይይት ቃለ ጉባኤም አፅድቀዋል። በ8ኛው ዙር ያፀደቁትን ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር ደንብ ላይም ያቀረቧቸው ማሻሻያዎችና ሀሳቦች መካተታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፥ በደንቡ ውስጥ ያልተካተቱ እና መውጣት ያለባቸው ሀሳቦች ላይ እርምት በማድረግ ደንቡን አፅድቀዋል።

ፓርቲዎቹ በድርድር ደንቡ መሰረት ከነገ ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ የመደራደሪያ አጀንዳዎቻቸውን የአጀንዳ አደራጅ እና የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ኮሚቴ እንደሚያስገቡም ታውቋል። ከ15 ቀን በኋላም አደራዳሪ ኮሚቴዎቹ ቀን በመወሰንና ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጥሪ በማድረግ ስራቸውን እንደሚጀምሩም ተገልጿል። በሌላ ዜና በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል ከወሰን ማካለል ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን አለመግባባት መፍታት የሚያስችል ሥምምነት ተደረሰ ስል ኢዜአ የሚከተለውን ዘግቧል።

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

 ሥምምነቱን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድን ጨምሮ የክልሎቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፈርመውታል።

ክልሎቹ ከወሰን ማካለል ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ተስማሙ

 ቀደም ሲል በሁለቱ ክልሎች አጎራባች ወረዳዎችና ቀበሌዎች በሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ሊከሰቱ የነበሩ አለመግባባቶችን ለማስቀረት ማኅበረሰቦቹ በመረጡት ክልል እንዲተዳደሩ ተደርጓል።

 የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሰረትም ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 14 ቀን 1997 ዓ.ም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በሆኑ 422 ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ ማካሄዱ ይታወሳል።

 በቦርዱ ውሳኔ መሰረትም በሁለቱ ክልሎች የሚኖረውን አስተዳደራዊ ወሰን መለየት እንዲቻል የፌዴራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስቴር የወሰን ማካለል ሥራ ሲሰራ ቆይቷል።

 በተለይም ከ2004 አስከ 2006 ዓ.ም የተካሄደው የወሰን ማካለል ሥራ የአካባቢው አስተዳደርና ኅብረተሰቡ በንቃት የተሳተፉበት በመሆኑ  አመርቂ ውጤት ማምጣት ተችሏል።

 ይህን ልምድ በመውሰድ ውስብስብ ችግር በታየባቸው በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ በፋፈን፣ በበነጎብና ሲቲ ዞኖች ሥር በሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች የማካለል ሥራዎች ተሰርተዋል።

Related stories   ‹‹የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም አለው፤ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠነክራል››

 በተለይም ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ተደጋጋሚ ውይይቶችና ምክክሮች እንዲሁም ኮሚቴ በማዋቀር መፍትሄ ለማምጣት ጥረት ቢደረግም ውጤታማ ባለመሆኑ ለዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

 የዛሬውም ሥምምነት ቀደም ሲል በተጠናቀቁት ላይ ተጨማሪ ሥራዎችን ለማከልና አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለማስቀረት ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

 በሁለቱ ክልሎች መንግሥታት የፌዴራል አካላትና በሕዝቡ የጋራ ጥረት ሥምምነት ላይ ደርሰው ወደ ተግባር የገቡትን አካባቢዎች የወሰን ማካለል ሥራም ይጨምራል ተብሏል።

 ስምምነቱ በሰባት ዞኖች 33 ወረዳዎች ሥር በሚገኙ 147 ቀበሌዎችና መንደሮች መካከል አስተዳደራዊ ወሰን ማካለልንም ያጠቃልላል።

 በመሰረታዊነት አጎራባች ማኅበረሰቦችን በልማትና በመልካም አስተዳደር በማስተሳሰር ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚረዳ ተሰምሮበታል።

 በእነዚህ አካባቢዎች እንዲሁም በአገሪቷ አስተማማኝና ዘላቂ ሠላም ማረጋገጥ የሚያስችል ሥምምነት መሆኑም እንዲሁ ተጠቅሷል።

 የሁለቱ ክልልሎች ርዕሰ መስተዳድሮችም የተደረሱ ሥምምነቶችን ለመተግበርና በአካባቢው ልማትና መልካም አስተዳደር ለማስፈን እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ጎን ለጎንም በሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ያደረጉ ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ እንደሚሰራ የፌዴራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0