የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ አራት ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾችና በዐቃቤ ህግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብይን እንዳልደረሰለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ፡፡ ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል።

ቀደም ሲል ከተመሠረተባቸው የሽብር ክሥ በነፃ ተሰናብተው የነበሩት የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺና የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ እንዲቀርቡ አራተኛ ወንጀል ችሎት አዝዟል፡፡

የችሎቱ ትዕዛዝ የወጣው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሠረት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *