የአውሮፓ ፓርላማ ዶክተር መረራ ጉዲና እንዲፈቱ ሲጠይቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው መልስ መግለጫውን ለጻፉት አካላት እንኳን የሚገባ እንዳልሆነ ተጠቆመ። ምላሹ ዝም ከማለት ከሚል እሳቤ በመነሳት የተሰጠ እንጂ ለቀረበው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ እንዳልሆነም ነው የተመለከተው።

ጉዳያቸው “ፍርድ ቤት” እየታየ መሆኑንን ጠቅሶ የህብረቱን መግለጫ ” ፋይዳ ቢስ ” ሲል የሚያጣጥለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ “አገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ እየሰራች የምትገኝ፤ ለዚህም አበረታች ድጋፍ እየተሰጣት ባለበት ወቅት፥ የህብረቱ የህግ አውጪ አካል የሆነው የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ካልተገነዘቡ አባላቱ እይታ ተነስቶ የወጣው መግለጫ ” በማለት ወሳኔውን የግለሰብ ማድረጉ ” ነገሮች ሁሉ እሱ እንደሰራው ፓርላማና የፖለቲካ ድርጅቶች አይነት ይመስለዋል” ሲሉ ነው ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉ አስተያየት ሰጪው የሚናገሩት።

የህዝብን ጥያቄ ስለመመለስና ስለ ሰላም የሚጠቁመው የውጪ ጉዳይ መግለጫ ለማን እንደተጻፈ ግራ ያጋባል  የሚሉት አስተያየት ሰጪ፣ “እኔ እስከሚገባኝ የህዝብ ጥያቄ መረራ ይፈቱ፣ የፖለቲካ እስረኞችና ያለ አግባብ የታሰሩ ነጻ ይሁኑ፣ የሃይል እርምጃ ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ ሰላም አያመጣምና ንጽሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ መጨረሻው አያምርምና ይቁም …. የሚል እንጂ ሌላ አይደለም” የሚለው አስተያየት ሰጪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልስ እንዳስገረመው ተናግሯል። አያይዞም ኢህአዴግ ከህብረቱ ጋር መመካከሩን እንደሚቀጥል ህብረቱን ባጣጣለበት መግለጫው ላይ ማካተቱ ደጋፊዎችሁን ከማበረታት የሚያልፍ ትርጉም እንደሌለው አመልክቷል።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

የጀርመን የህብረቱ መግለጫ ከመግለጫ ያላለፈ እንደሆነ አስተያየት የሰጡ ወገኖችን ጠቀሶ ሪፖርት አድርጓል። ህብረቱ አቋም ቢይዝ መረራን ማስፈታት እንደማይከብደውም አክሎ ገልጿል። በተቃራኒው የውጪ ጉዳይን መግለጫ “እቅ እቃ ጨዋታ” ሲል የተቹ እንዳሉ በሪፖርቱ አካቷል።

የአውሮጳ ምክር ቤት መረራ  በአስቸኳይ ይፈቱ ሲል ጥሪ አቀረበ፤ጉዳዩ በሚቀጥለው ወር በጄኔቫ በሚካሔደው የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እንዲጀመር አሳስቧል

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪውን አልተቀበለም። ምክር ቤቱ ትናንት ባጸደቀው የውሳኔ ኃሳብ በኢትዮጵያ ተቃውሞ የተፈጸሙ ግድያዎችን የሚያጣራ የተ.መ.ድ. መራሽ ቡድን ለማቋቋም ፌዴሬካ ሞግሔሪኒ ጥረት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የአውሮጳ ሕብረት ምክር ቤት በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪው በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ የቀረቡ ክሶችም ውድቅ እንዲደረጉ ጠይቋል። ጥሪው ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ቀና ምላሽ አላገኘም። ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያለው ራዲዮ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር የአውሮጳ ፓርላማን ጥሪ «ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማሳነስ ከመሞከር የዘለለ ፋይዳ» የለውም ብሏል።

“መረራ በአስቸኳይ እንዲፈቱ” ጉዳዩ በጄኔቫ የሰብአዊ መብት ጉባኤ እንዲቀርብ ማሳሰቢያ ተሰጠ

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸዉ የአውሮጳ ምክር ቤት ጥሪ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር ምላሽም ውሐ አያነሳም» ይላሉ። የፍሎሪዳው ነዋሪ አብደላ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአውሮጳ እና አሜሪካ መንግሥታት ድጋፍ መጠበቅ የለበትም ባይ ናቸው።  አቶ አብደላ ከአፍ ያላለፈው የአውሮጳውያኑ ማሳሰቢያ ዋጋ የለውም ባይ ናቸዉ።

Friedensnobelpreis EU Europäische Union Symbolbild (Getty Images/AFP)

«እውነት የአውሮጳ ኅብረት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት እንዲከበሩ የሚሹ ቢሆን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋ በግልፅ በመነጋገርና አቋም በመውሰድ በሳምንታት እድሜ ማስፈታት ይችሉ ነበር» የሚሉት አማን ቢን ያሲር «ከመግለጫነት ያለፈ ጠብ የሚል ነገር የለውም።ህብረቱ እርምጃ የሚወስድባቸውና የማይወስድባቸው መንግስታቶች(አምባገነን መንግስታትን) ከኅብረቱ ጥቅም አንፃር እንጂ ዜጎቻቸውን ስለሚጨቁን በሚል አይደለም» ሲሉ ተችተዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲናን ለእስር የዳረጋቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያስፈለገው በመንግሥት ጥፋት ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪ ደግሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪው ጥፋት የለባቸውም ብለዋል። የመንግሥትን ምላሽ «የእቃ እቃ ጨዋታ» ያሉም ኢትዮጵያዊም አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ሰጥተዋል።

የአውሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ትናንት ባፀደቀዉ ሌላ የዉሳኔ ሐሳብ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከታኅሳስ 2015 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 2016 በኢትዮጵያ በተቀሰቀው ተቃውሞ የተፈጸመው ግድያ እና የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል። ምክር ቤቱ ያጸደቀው የውሳኔ ኃሳብ የአውሮጳ ኅብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ፌዴሬካ ሞግሔሪኒ ግድያዉን የሚያጣራ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ግፊት እንዲያደርጉ ኃሳብ አቅርቧል። ጥረቱን በሚቀጥለው ወር በጄኔቫ በሚካሔደው የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እንዲጀምሩም ጠይቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቀሶ ፋና የሚከተለውን ዘግቧል

የፋና ዘገባ – ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባሉት ዶክተር መረራ ጉዲና የፍርድ ሂደት ላይ ያወጣው መግለጫ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማሳነስ ከመሞከር የዘለለ ፋይዳ እንደሌለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ እየሰራች የምትገኝና ለዚህ አበረታች ድጋፍ እየተሰጣት ባለበት ወቅት፥ የህብረቱ የህግ አውጪ አካል የሆነው የአውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ካልተገነዘቡ አባላቱ እይታ ተነስቶ ያወጣው መግለጫ ስለመሆኑም አንስቷል። ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ህዝቡ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የህዝቡን ጥያቄ መመለስ እንደሚያስፈልግም ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ይህን ለመመለስ በመንግስት በኩል ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት መግለጫው መውጣቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ላለው የትብብር መንፈስ ገምቢ አለመሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል። በህግ ጥላ ስር ያሉ ወገኖችን በተመለከተ የተሰጠው አስተያየትም የኢትዮጵያን የፍትህ አካሄድና ስርዓት ያላገናዘበ መሆኑም በመግለጫው ጠቅሷል።

ሚኒስቴሩ የህብረቱ ፓርላማ መግለጫ በሀገሪቱ የእድገት ጉዳይ ላይ ትርጉም ያለው ተጽእኖ የሚያሳርፍ አለመሆኑንም ነው የጠቀሰው። ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር እያሳደገች ላለው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚመጥን፣ በመመካከር፣ በጋራ ጥቅም፣ በእኩልነት ላይ የተመሰረተና የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ አመለካከት እንዲሰፍን፥ በተጠናከረ መልኩ ከህብረቱ ጋር ምክክሯን እንደምትቀጥልም አስታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *