በፖለቲካ ሳይንስ ምሁር፣ በግል የፖለቲካ አቋማቸው አክራሪ አካሄድን የሚጻረሩ፣ ሃሳባቸውን በነጻነት ከመግለጽ ወደሁዋላ ያምይሉና የማክረር ፖለቲካን በማሽመድመድ በሚታወቁት ዶክተር መረራ ጉዲናን መዝገብ ዛሬ ያስቻለው የልደታ ምድብ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት፣ ዓቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሻሽል ሲያዝ ፣ የኢሳትና  ኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ወርክን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ያልተሰማ ማብራሪአ እንዲቀርብለት ጠይቋል።

በመረራ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል ኢሳትና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ለመከሰስ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች መሆን እንዳለባቸው ችሎቱ አመልክቷል። በዚሁ መሰረት ሁለቱም ሚዲያዎች እንዴት እንደተቋቋሙ፣ የት እንደተቋቋሙ፣ በማን እንደተቋቋሙ፣ በየትኛው አገር  ህግ እንደተቋቋሙ አቃቤ ህግ በዝርዝር እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ አዟል። ክሱንም እንዲአሻሽልና እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

የመረራ ጠበቆች ተጨማሪ መቃወሚያ በማቅረብ ደንበኛቸው በጸር ሽብር አዋጁ ሊከሰሱ እንደማይችሉ ጠቁመዋል። መረራ ተላለፉ የተባለው በ1999 የወጣውን የወንጀለኛ ህግ የተለያዩ ድንጋጌዎች እንደሆነ በመጥቀስ በክሱ የቀረቡት ሁለት ማስረጃዎች እሳቸውን የማይመለክቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአቃቤ ህግን የመቃወሚያ መቃወሚያ በንባብ ያሰማው ችሎት ለሰኔ 13 ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል። የቪኦኤ አዲስ አበባ ዘጋቢ መለስካቸው አመሃ ዘገባ ያድመጡ

Related stories   በአዲስ አበባ ከ1ሺህ በላይ ህገ ወጥ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጄንሲዎች እገዳ ተጣለባቸዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *