ሰመጉ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ (ከመስከረም 28 2ዐዐ9 ዓ.ም) ጀምሮ

በዜጎች ላይ የሚፈፀም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ ይቁም!

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰመጉ በምስል፣ በሙሉ ስም፣ በአባሪ ማሰጃዎችና በአድራሻ አስደግፎ አጣርሁ ያለውን የስቃይ፣ የግያና በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸሙ የማይገባ ያለውን ግፍ ዘርዘሮ በ142ኛ መግለጫው ይፋ አድርጓል። በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ አሥራ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ሕገ ወጥ ግድያ ሲፈጸም ፣ ከሃያ ሺሕ በላይ ሰዎች ታስረዋል። ቀላል በማይባል ደረጃ በዜጎች ላይ የሰው ልጅን መብት በጣሰ ሁኔታ በማሰቃየት ምርመራ መካሄዱን አስታውቋል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

ሰመጉ ይህንን ሰፊ ማሰረጃ ላይ የተመረኮዘ መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ ከመንግስት በኩል ማስተባበያም ይሁን ተቃውሞ እስካሁን አልተሰማም። የቀደሞው ይምርጫ ቦርድ ሃላፊና የአሁኑ ኢህአዴግ ያቋቋመው የሰብአዊ መብት ኮሚሽንም ያለው ነገር የለም።

 

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በዜጐች ላይ የተፈፀሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አጋለጠ። ሰመጉ ሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ。ም ባወጣው በ142ኛ ልዩ መግለጫው በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች የተፈፀሙና ሰመጉ ምርመራ አከናውኖ በቂ መረጃ እና ማስረጃ ያሰባሰበባቸውን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፋ አድርጓል።

Related stories   WAR, JUSTIFIABLE WAR? "ጦርነት ለሃገር ህልውና" by Dr. Haymanot

በዚህ ልዩ ሪፖርት በዜጐች ላይ የተፈፀሙ ህገወጥ ግድያዎች፣ ማቁሰል፣ድብደባ፣ ማሰቃየት፣ የጅምላ እስር እና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተካተዋል። ይህ የ142ኛው ልዩ ሪፖርት በተጠቀሱት ክልሎች በሚገኙ በ18 ዞኖች፣ በ42 ወረዳዎች እና ክፍለ ከተሞች የተፈፀሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ብቻ የሚያካትት ነው። በልዩ ሪፖርቱ ማጠቃለያም ሰመጉ መንግስት ተገቢውን እውቅና፣ የመሥራት ነፃነት፣ ድጋፍና ጥበቃ እንዲያደርግለት ጠይቋል።

Related stories   Ministry Urges Amnesty Int’l to Use Appropriate Sources in Report to Uncover the Truth

ሙሉውን መግለጫ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ያንብቡ

የሰብዓዊ-መብቶች-ጉባዔ-142ኛ-ልዩ-መግለጫ-ግንቦት-2009-ዓ。ም

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *