የቡና ላኪነት ፈቃድ በማውጣት ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሚገዛውን ቡና ወደ ውጭ መላክ ሲገባው ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለ ቡና ነጋዴ፣ መንግሥትን ከ10.9 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ በማሳጣት ተጠርጥሮ ታሰረ፡፡

ተጠርጣሪው ቡና ነጋዴ እምሩ ሙርሺድ መሐመድ የሚባል ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ 1,265 ኩንታል ኤክስፖርት የሚደረግ ቡና የገዛ ቢሆንም ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ቡናውን ለግል ጥቅሙ ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አስረድቷል፡፡

Related stories   በእነ ጃዋር የህክምና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪዎች ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤ ቃሊቲ ሆነው ይታከማሉ፤

በተጠርጣሪው ላይ ንግድ ሚኒስቴር ጥቆማ በማቅረቡ የፌዴራል ፖሊስ ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎት በምርመራ ላይ መሆኑን፣ ኤክስፖርት የሚደረግን ቡና ለግል ጥቅሙ በማዋሉ 10,940,838 ብር የውጭ ምንዛሪ ማሳጠቱን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን በማስገባት ላይ መሆኑን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ቀሪ የሰነድ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብና የምስክሮችን ቃል ለመቀበል ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደሚያስፈልገው በመግለጽ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር አንቀጽ 59/2 መሠረት የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል፡፡ ተጠርጣሪው ዋስትና እንዲፈቀድለት የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ አሥር ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለሰኔ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Related stories   በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በተጠርጠሩ አራት ተከሳሾች ብይን ሰጠ

 ከቡና ንግድ ጋር በተያያዘ በብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ በማሳጣት ተጠርጥረው የተያዙ ቡና ነጋዴዎች ክስ ተመሥርቶባቸው ክሳቸው በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

ዜናው የሪፖርተር እዚህ ላይ ይመልከቱት

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *