ዛፍ የሰረቁት ሶስት ሰዎች በ8 አመት እስራት እና በገንዘብ ተቀጡ

 በደቡብ ምዕራባዊ ቻይና ዩናን ግዛት ዛፍ የሰረቁት ሶስት ተከሳሾች በስምንት አመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። ግለሰቦቹ በዩናን ከሚገኘው የቻይና የሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ውድ እና ጥሩ ሽታ ያለውን እንጨት(ሮዝውድ) በጥቅምት ወር 2015 ሰርቀዋል በሚል ነው ክስ የተመሰረተባቸው።

ተከሳሾቹ ዛፎቹን ለመቁረጥ የሚረዷቸውን መሳሪያዎች ይዘው ወደ አካዳሚው የአትክልት እና አዝዕርት ቦታ ማምራታቸውን ክሱ ያመለክታል። አንደኛው የዛፍ ዘራፊ ከአንድ ሳምንት በኋላ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ግብረ አበሮቹን በመጠቆሙ ሶስቱም ወዲያውኑ ሊያዙ ችለዋል።

rosewood.jpg

ክሱን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ግለሰቦች ለፈፀሙት ተግባር የስምንት አመት እስራት ፈርዶባቸዋል።

ከእስራት ቅጣቱ ባሻገር እያንዳንዳቸው በ100 ሺህ ዩዋን (1 ሺህ 472 የአሜሪካ ዶላር ገደማ) እንዲቀጡም ተወስኖባቸዋል።

rosewood1.jpg

ጥሩ ሽታ ያለው የሮዝውድ ዛፍ በቻይና ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ዛፎች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አንዱ ሮዝውድ እስከ 360 ሺህ የቻይና ዩዋን (ከ52 ሺህ 900 በላይ የአሜሪካ ዶላር) ያወጣል።

የሮዝውድ ዛፍ በቻይና ሃይናን፣ ፉጂያን፣ ዠጂያንግ እና ጉዋንዶንግ ግዛቶች ብቻ ነው የሚያድገው።

ለቤት ውስጥ ቁሳቁሶች እና ጌጣጌጦች መስሪያነት የሚያገለግለውን ሮዝውድ በተለያዩ የቻይና ክፍሎች ለማሳደግ ጥረት ቢደረግም በሚፈለገው ልክ ውጤታማ አልሆነም።

rosewood2.jpg

የእንጨቱ ተፈላጊነት እጅጉን እየጨመረ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን፥ ጥቅም ላይ ለመዋል ለአስር አመታት ማደግ ያለበት መሆኑም ሌላኛው ችግር ሆኗል።

የእንጨቱ ዋጋ ከዚህም በላይ እየጨመረ ይመጣል የተባለ ሲሆን፥ እንደ አውሮፓውያኑ በ2012 በጉዋንዶንግ ግዛት 20 ሜትር ቁመት እና 65 ሴንቲሜትር ዲያሜትር ያለው ባለ ጥሩ ሽታ ሮዝውድ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር በላይ ማውጣቱ ተዘግቧል።

ምንጭ፦   (ኤፍ.ቢ.ሲ)   https://news.cgtn.com/   በፋሲካው ታደሰ

Related stories   CHELSEA WIN THE PREMIER LEAGUE!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *