የንግድ ሚኒስትሩ ዶክተር በቀለ ቡላዶ ” ሆነን መገኝት አለብን፣ ድራማው ይቁም ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ከቃላት ባለፈ የመንግስት ሃላፊዎች፣ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የመዋቅር አካላት የተግባር ሰው ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል። ኮንትሮባንድን አስመልከተው እንደተናገሩት አሁን የተደረሰበትን ደረጃ ” መገዝገዝ” እንዳሉት ሪፖርተር እሳቸውን ጠቅሶ አመልክቷል።

Bekele trade ministre

ሙስና አገሪቱን እንደወረራት በስፋት በመግልጽ አቶ ሃይለማሪያም በአንድ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ እርምጃ እንደሚወሰድ መግለጻቸው የሚታወሰ ነው። በሪፖርተር ዜና ኮንትሮባንድን ሚኒስትሩ ከሙስና ጋር አያይዘው ስለማቅረባቸው የተባለ ነገር ባይኖርም፣ በተለያዩ ደረጃ ያሉ የመንግስት መዋቅር አካላት ተባባሪ መሆናቸውን፣ አይተው ዝም አንደሚሉ ተመልክቷል።

ሙስና የስርዓቱ አደጋ እንደሆነ በተለያዩ አውደ ጥናቶች እና መድረኮች በስፋት የሚቀርብ በመሆኑ ይሁን በሌላ፣ ሚኒስሩ ኮንትሮባንድን ምርር ባለ ሁኔታ ከመግለጽ በዘለለ ወይም በአፍ ማውገዝ ብቻ ሳይሆን፣ በሚወራው መጠን ሆኖ በመገኘት አደጋውን ማስወገድ እንደሚገባ ተናገረዋል።

በአገሪቱ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩት ክፍሎች እነማን ናቸው? እንዴት ነው ኬላውን የሚያልፉት፣ የኬላ ቁጥጥር ላይ እነማን ናቸው ሃላፊዎቹ? እነማን ለማን በር ይከፍታሉ፣ ፈቃድ የሰጣሉ? በኬላዎች ብቻ ሳይሆን በጉምሩክ የተለያዩ ዘርፎች ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር የተመደቡት….. ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች ሲመለሱ ችግሩ ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቱን የሚገዘገዙት ክፍሎች የሚታወቁ እነደሚሆኑ ኮንትሮባንድ እያነካከታቸው እንደሆኑ የገለጹ ነጋዴዎች ለአቶ መለስ አቤት ብለውም ነበር። እንደ ነጋዴዎች ገለጻ በህጋዊ የንግድ አግባብ ለመቀጥል መቸገራቸውንም አስታውቀውና አደጋው አገሪቱንም ወደ ከፋ ችግር እንደሚከታት አሳስበው ነበር።

ሚኒስትሩን ጠቅሶ ሪፖርተር የሚከተለውን ዘግቧል።

  • ባለሥልጣናት ድራማ መሥራት ማቆም አለባቸው ብለዋል

የኮንትሮባንድ ንግድ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየገዘገዘ መሆኑን የንግድ ሚኒስትሩ በቀለ ቡላዶ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ የተቋማቸውን የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የተጋረጠውን የኮንትሮባንድ አደጋ ግንዛቤን በመፍጠር መፍታት ለጊዜው እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

አፋጣኝ የአጭር ጊዜ መፍትሔው መጠነ ሰፊ የኮንትሮባንድ ዘመቻ ማካሄድ ነው ብለዋል፡፡

ዘመቻው ከተጀመረም ከከፍተኛ የመንግሥት መዋቅር እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ አመራሮችን በጥልቀት መመልከት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ‹‹በኮንትሮባንድ ጉዳይ እርር ድብን ብሎ መድረክ ላይ የሚናገር አመራር ራሱ በር ከፋች ነው፡፡ አልያም አይቶ አላፊ ነው?›› ሲሉ በመንግሥት መዋቅሮች የንግድ ወይም የሕግ ማስከበር ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማት ውስጥ ያሉ እውነታዎችን ጠቁመዋል፡፡

ኮንትሮባንድ አገሪቱን እየገዘገዛት መሆኑን የጠቆሙት ማኒስትሩ በመንግሥት መዋቅሮች ያሉ አመራሮች፣ ኮንትሮባንድ አገሪቱን እየገዘገዛት እንደሆነ እየተናገሩ ነው ብለው፣ የሚናገሩትን ከመድረክ ፍጆታ በዘለለ አምነውበት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

‹‹የአመራሩ ድራማ መቆም አለበት፡፡ ሆነን መገኘት መቻል አለብን፤›› ሲሉ ለምክር ቤቱ የገጠማቸውን ፈተና ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው የወጪ ንግድ ዘርፉ (Export) ከዕቅዱ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ ባሻገር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸምም በታች መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከወጪ ንግድ ዘርፍ (Export) ባለፉት 11 ወራት 4.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የነበረ መሆኑን፣ አፈጻጸሙ ግን 2.53 ቢሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዱ 59 በመቶ ብቻ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ ከ2008 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀርም በሁለት በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡

ለዚህ ዘርፍ ዝቅተኛ አፈጻጸም ምክንያት ከሆኑት መካከል የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ፣ በከፍተኛ መጠን አለማምረትና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ ማውጣት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይ የቁም እንስሳትና የወርቅ ምርቶች በከፍተኛ ደረጃ በኮንትሮባንድ ከአገር እየወጡ ነው ብለዋል፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *