” በአስቸኳይ አዋጅ አዋጅ ውስጥ ሆነን በአስቸኳይ አዋጁ ዙሪያ አንደራደርም”

ድርድር

ተደራዳሪ ፓርቲዎች – ፎቶ ቪኦኤ አማርኛ

ኢህአዴግን ጨምሮ አስራ ሰባት ፓርቲዎች በሚሳተፉበት የድርድር መድረክ ከቀረቡት አስራ ሶስት የመደራደሪያ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ላይ ብቻ ስምምነት ላይ ሲደረስ በተቀሩት ላይ ኢህአዴግ ማብራሪያ በመጠየቁ ለጊዜው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። የአስቸኳይ አዋጁን በተመለከተ ድርድር አይደረግም ተባለ።
በምርጫና ተያያዥ የምርጫ ህጎች ዙሪያ ለመደራደር ፈቃደኛነቱን የገለጸው ኢህአዴግ ” በአስቸኳይ አዋጅ አዋጅ ውስጥ ሆነን በአስቸኳይ አዋጁ ዙሪያ አንደራደርም” ሲል እንቅጩን ተናግሯል። የኢህአዴግ ዋንኛ ተደራዳሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዳሉት ፓርቲያቸው በተቀሩት የመደራደሪያ አጀንዳዎች ዙሪያ ማብራሪያ እንደሚፈልግ፣ ማብራሪያውን ከሰማ በሁዋላ አቋም ለመያዝ ያመቸዋል።
ፓርቲዎች በተራ ቁጥር 2 ፣ ንዑስ አንቀጽ 6 መሰረት የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ፣ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣ የንግድ ኢንቨስትመንት፣ ፋይናንስ፣ ታክስ ህጎች፣ የፍትህ አካላት፣ የበጎ አድራጎት እና የአስቸኳይ አዋጁ ላይ ድርድርድ እንዲደረግባቸው ጠይቀዋል።
የጸረ ሽብረትኛነት አዋጁ የዜጎችን ሰብአዊ መብት ማፈኛ፣ ማሰሪያ ፣ ማሰቃያ ወዘተ አዋጅ መሆኑ ከተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች በኩል አስተያየት ተሰጥቶበታል። በዚሁ መሰረት አዋጁ ላይ መደራደር አስፈላጊ መሆኑንን አመልክተዋል።
ዜናውን የዘገበው የቪኦኤ አማርኛ ክፍል እንዳለው ፣ በጥቅሉ ከቀረቡት 13 አጀንዳዎች መካከል ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ የተስማማው በአንዱ በምርጫው አዋጅ ብቻ ሲሆን፣ በተቀሩት 12 አጀንዳዎች ዙሪያ ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ድርድሩ ለቀጠያ ሰኞ በእንጥልጥል የያዛቸው ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ቀጠሮ መያዙ ታውቋል። በአስቸኳይ አዋጁ ጉዳይ ኢህአዴግ እንደማይደራደር አረጋግጧል። ይህ ማለት የጸጥታ ችግሩ ላይ መተማመን ስለሌለ መሆኑንን ያመላክታል ተብሏል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኤስ አይ ዲ ፣ የዓለም ባንክና የተለያዩ አምባሳደሮች በታዛቢነት ተገኝተዋል ተብሏል።

ተጨማሪ ይህንን ያድምጡ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *