banner1

ፓርቲዎች ከኢህአዴግ ጋር እያደረጉት ያለው ድርድር ዋጋ ቢስና የይስሙላ መሆኑን ኦፌኮና ሰማያዊ ፓርቲ አመለከቱ። መድረክም በተመሳሳይ ድርድሩ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከመዋሉ በቀር ፋይዳ እንደማያመጣ በማመን በጊዜ ራሱን ማገለሉ አይዘነጋም። አሁን እየተደራደሩ ያሉት ድርጅቶች ቀድሞውንም ቢሆን ኢህአዴግ በሚመራው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ውስጥ አባል በመሆን የአጃቢነት ሚና ሲጫወቱ የኖሩ በመሆናቸው ተደራዳሪ ሳይሆኑ ተወያይ መሆናቸውም ተመልክቷል። የሚደረገውም ውይይት ከህገ ወጥ ድርጅቶች ጋር ነው ተብሏል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሽህ ዋስ አደራዳሪ፣ አወያይ፣ መካከለኛ አካል የሌለው ንግግር ዋጋ አልባ መሆኑን በመጠቆም ለ16 ድርጅቶች ይቅናቸው ሲሉ መርቀዋቸዋል። ምርጫ ቦርድ አምስት ፓርቲዎች ብቻ ህጋዊ ሰነድ እንዳላቸው ይፋ አድርጎ ሳለ ከአስራ ስድስቱ ጋር ውይይት መቀመጡ የጉዳዩን ቀልድነት አመላካች መሆኑን ያሳያል ብለዋል። አያይዘውም እንዲህ ያለ የቀልድ ሳይሆን እውነተኛ ድርድር እንዲጀመር እየጠየቁ መሆኑንንም ተናገረዋ። ከዚህ ውጪ ” መናጆ መሆን አንፈለግም” ብለዋል።

Related stories   ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረንስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ እንዳሉት ቀደሞውንም ለድርድር ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማያገኙና ድርድሩ በራሱ የድርድር መስፈርቶችና ቅድመ ሁኔታዎች የሌሉት በመሆኑ አስቀድመው ራሳቸውን ማግለላቸው አግባብ እንደሆነ አመልክተዋል። ባለፈው ሳምንት ከቀረቡት 13 አጅንዳዎች መካከል ኢህአዴግ አንዱን ብቻ መቀበሉን ገልጸን መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ሙላቱ አስራ ስድስቱ ድርጅቶች የኢህአዴግ ፎረም አባል ድርጅቶች መሆናቸውን ይናገራሉ። አያይዘውም እንደ ቤተስብ አብረው ሲሰሩ የነበሩ ድርጅቶች ለምን ታዛቢ እንዳስፈለጋቸው ግልጽ እንዳልሆነላቸው ተናግረዋል። ዓላማውም ተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መሆኑን ጠቁመዋል። እውነተኛ ድርድር በማካሄድ አገሪቱ የገባችበትን የፖለቲካ ቀውስ ማሰውገድ ይቻላል የሚል እምነት እንደነበራቸው የጠቆሙት አቶ ሙላቱ፣ የራስን ጥቅም ወደ ሁዋላ በማድረግ እውነተኛ ድርድር ማድረግ ቆራጥ ውሳኔ የሚጠይቅ፣ ፍርሃት ሳይሆን ጀግንነት ነው ብለዋል። እስካሁን ግን የተመለከቱት በተቃራኒው የማጭበርበር ዓይነት የፖለቲካ ቁማር ነው። ህዝብ የጠየቀውን ጥያቄ ወደሁዋላ በመተው ዝም ብሎ መሮጥ ዋጋ ቢስ ነው በለዋል።

Related stories   በዓድዋ ከተማ የመብራት አገልግሎት ዛሬ ጀመረ

አቶ የሺህ ዋስ የህዝብን ጥያቄ ሳይመለሱ ዝም ብሎ መባከን የትም እንደማያደርስ ጠቁመው አሁንም ጊዜ ከመግደል ወደ እውነተኛው ድርድር ማምራት ግድ መሆኑንን አመልክተዋል።  አቶ ገመቹ “እቺ አገር የሁላችንም ናት” ሲሉ አገሪቱ ሳትበታተን እንድተቀጥል፣  ሁሉም ተስማምቶ የሚኖርባት እንደትሆን ቅድመ ሁኔታ ያለው ድርድር አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል። አያይዘውም  የፖለቲካ መሪዎች ደጋፊዎችን  አስሮ ድርድር ማለት ግራ የሚያጋባ መሆንን ያመለክታሉ።

Related stories   በሰሜን የኤርትራና ሶማሊያ ወታደሮች ጣልቃ ገብተዋል መባሉን መንግስት " ፈጠራ የሮኬት ተኳሹ ወሬ" አለው

በአስቸኳይ አዋጅ አውጅ ስራ በምትተዳደር አገር ውስጥ፣ መሰብሰብና መገናኘት በህግ በተከለከለበት አገር ውስጥ በድርድር እርቅ አውርዶ መቀጠል አስቸጋሪ እንደሚሆንም አመልክተዋል። ኢህአዴግ የሰበሰባቸው ድርጅቶች ከህዝብ ጋር ብዙም የማይተዋወቁ፣ የሕዝብ ተቀባይነታቸው ይሄ ነው ተብሎ የማይገለጽ፣ አንዳንዶቹ ከቤተሰብ አባላት የዘለለ ስፋትየሌላቸው፣ ከዋናና ህዝብ ከሚወዳቸው ፓርቲዎች ተገንጥለው የወጡ፣ በተቃውሞ ደረጃና በፖለቲካ አቅማቸው የሚታሙ እንደሆኑ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። ኢዴፓም ቢሆን የአስቸኳይ አዋጁን በአደባባይ የደገፈና እንዲራዘም የጠየቀ፣ ከአቶ ልደቱ ጋር በተያያዘ ተአማኒነቱን ያጣ እንደሆነ ተደርጎ የተወሰደ ድርጅት መሆኑ ፓርቲው ባይቀበለውም በስፋት ሲዘገብ ሰንብቷል።

መድረክ እውነተኛ የሚባል ድርድር እንዲደረግ ጠይቆ መልስ በመጠባበቅ ላይ መሆኑም ተመልክቷል።

 ያድምጡ

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *