ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጥሩ ያልሆነ ውጤት ምጣቱን ተከትሎ የክለቡ አሰልጣኝና ተጫዋቾች ደጋፊውን ይቅርታ ጠይቀዋል። በ2009 የውድድር ዘመን ያልተሳካ ሊባል የሚችል የውድድር ዘመን ያሳለፉት ቡናማዎቹ እንዳለፉት አመታት ሁሉም ዘንድሮም በቀጣይ አመት በአፍሪካ መድረክ ሊያሳትፋቸው የሚችለውን ውጤት ማስመዝገብ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ ከክለቡ ደጋፊዎች በርከት ያሉ ወቀሳዎች እየተሰሙ ይገኛሉ፡፡
2017-06-17