በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ፣ ምእራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በደረሱ ሶስት የትራፊክ አደጋዎች በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ላይ በምእራብ አርሲ ዞን ከሻሸመኔ ወደ አርሲ ነገሌ 15 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ቀርሳ አድቬንትቲስት ኮሌጅ አካባቢ ሲድርስ ድልድይ ውስጥ ገብቶ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው አሽከርካሪው እና ረዳቱን ጨምሮ በተሸከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሰባት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፥ በሰባት ሰዎች ላይ ከባድ በአንድ ሰው ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ ነው ተብሏል፡፡

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

በተያያዘ ዜና ትናንት ማለዳ እና ረፋድ ላይ በክልሉ ምእራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በደረሱ ሁለት የትራፊክ አደጋዎች 28 ሰዎች ሲሞቱ በሰው እና በንብረት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ከሁለቱ አደጋዎች መካከል ረፋድ 4 ሰዓት ላይ ከድሬደዋ ከተማ ወደ አዲስ አበባ 60 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ምእራብ ሀረርጌ ዞን ሂርና ከተማ ሲድርስ ፍሬን እምቢ ብሎት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በተሽከርካሪ አደጋውም መንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩ የ14 ወንዶች እና የ8 ሴቶች በድምሩ የ22 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉ ተነግሯል። በተጨማሪም በአራት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ በሶስት ሚኒባስ እና በአንድ አይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት አድርሷል። በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ላይ ግን የደረሰ አደጋ አለመኖሩ ተገልጿል።

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ተሽከርካሪው የቴክኒክ ምርመራ አለማድረጉ ለአደጋው ዋነኛ መንስኤ ነው።በአሁኑ ጊዜም የህዝብ ማመላለሻው አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ ወደ አዲስ አበባ አስከሬን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ፥ ትናንት ማለዳ 12 ሰዓት ላይ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቴ ወረዳ ሲደርስ ተገልብጦ ገደል ውስጥ በመግባቱ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት ሰዎች ውስጥ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አባት እና ሁለት ልጆች ይገኙበታል። አደጋው እንዲደርስ ምክንያት የሆነው ደግሞ አሽከርካሪው ለሶስት ቀናት ሳይተኛ በማሽከርከር ላይ ስለነበረ መሆኑን ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ተናግረዋል።

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *