በአራጣ አበዳሪነት ጥፋተኛ ተብለው በ20 ዓመት እስራት የተቀጡት አቶ ከበደ ተሰራ በቅጽል ስማቸው አይኤምኤፍ ንብረት የሆነው አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው ግዙፍ ሕንጻ የፊታችን ዓርብ በሐራጅ ሊሸጥ ነው።

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐቃቤ ህግ እና በፍርድ ባለዕዳ አቶ ከበደ ተሰራ መካከል በነበረው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጎን የሚገኘው በመከታ ሪል ስቴት ስም የተመዘገበውና ከስድስት ዓመታት በላይ ሥራው ቆሞ የነበረው ማጠናቀቂያ ላይ የሚገኝ እና በ2 ሺ 926 ካሬ ሜትር ይዞታ ውስጥ ያረፈ ሕንጻ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 72 ሚሊየን 740 ሺ 53 ብር ከ24 ሳንቲም ሆኖ ሰኔ 23 ቀን 2009 ለመሸጥ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል።

የክሱ አመጣጥ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 11ኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 5 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአራጣ አበዳሪነት የተጠረጠሩትን አቶ ከበደ ተሰራ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ በመተላለፍ ለጌታነህ ኃ/የተ/የግል ማህበር 12 ሚሊየን 90 ሺ ብር ብድር ሰጥተው በየወሩ 4፣ 5 እና 7 በመቶ ወለድ እየተቀበሉ በመጨረሻም የተበዳሪውን ንብረት በመውረስ ስሙን ወደራሳቸው በማዛወር በፈጸሙት ወንጀል ተጠርጥረው መከሰሳቸው የሚታወስ ነው።

በተጨማሪም ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ተከሳሹ የነበረባቸውን የትርፍ ግብር ማለትም 5 ሚሊየን 286 ሺ 136 ብር ከ72 ሳንቲም በመሰወራቸውም ክስ ቀርቦባቸው ፍ/ቤቱ በ20 ዓመት እስራት እና በ165 ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው ሲሆን በሕገወጥ ገንዘብ ያገኙትንም ንብረት እንዲወረስ መወሰኑ አይዘነጋም።

sendek newspaper

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *