via ዝውውር፡ የዕለተ እሁድ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች — ኢትዮአዲስ ስፖርት

 • • አርሰናል ለኪሊያን ምባፔ 125 ሚ.ፓ. በማቅረብ ሪያል ማድሪድ በሞናኮው ወጣት አጥቂ ላይ ያለውን ፍላጎት ለማስተጓጎል ተዘጋጅቷል።
 • • ምባፔ ከግል የትዊተር ገፁ ላይ ሞናኮን ማስወገዱን ተከትሎ በዝውውር ወሬው ላይ ቤንዚን አርከፍክፏል።
 • • አርሰናል በተከላካዩ ኪራን ጊብስ ላይ የ8 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለጠፈ።
 • • የርገን ክሎፕ ዳንኤል ስተሪጅ ሊቨርፑልን እንዳይለቅ ያግዳሉ። ምክኒያቱም እሱን ለመተካት ብዙ ገንዘብ ያስወጣቸዋል።
 • • የርገን ክሎፕ ተከላካዩን በቅድመውድድር ዘመን ለመጠቀም ማሰባቸውን ተከትሎ ሊቨርፑሎች ለጆ ጎሜዝ የሚቀርብላቸውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ የሚያደርጉ ይሆናል።
 • • ዌስት ሃሞች የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ የኻቪየር ኸርናንዴዝ የውል ማፍረሻ የሆነውን 13 ሚ.ፓ በመክፈል ተጫዋቹን ለማስፈረም ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።
 • • ዌስት ሃሞች መረጋጋት ላይ የማይገኘውን የበርንሌይ አጥቂ አንድሬ ግሬይን በ15 ሚ.ፓ ለማዛወር እንቅስቃሴ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።
 • • ኒውካሰሎች የቪላሪያሉን አጥቂ ሰድሪች ባካምቡን ለማስፈርም ቢፈልጉም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ግን የዝውውር ክብረወሰናቸውን መስበር ይጠበቅባቸዋል።
 • • ሞናኮዎች የማንችስተር ዩናይትድ ዒላማ ለሆነው ፋቢንሆ ከፒኤስጂ የቀረበላቸውን የ40 ሚ.ፓ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረጉ።

sunday telegraph

 • • ዲያጎ ኮስታ ቼልሲ ከክለቡ ሊቀንሰው መዘጋጀቱን ተከትሎ በከፍተኛ የክብር ስሜት ወደአትሌቲኮ ማድሪድ ለመመለስ ራሱን አዘጋጅቷል።
 • • የስዊንሲ ዒላማ የሆነው ሮኩ ሜሳ በ11 ሚ.ፓ ከላስ ፓልማስ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደእንግሊዝ ይበራል።
 • • ኸደርስፊልዶች የቼልሲውን አማካኝ ካሲይ ፓልመርን ዳግም በውሰት ሊያስፈርሙ ሲሆን የኢዚ ብራውንንም ዝውውር እያጤኑበት ይገኛሉ።

sunday times

 • •  የአርሰናሉ አማካኝ አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን አዲስ የቀረበለትን ኮንትራት ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ባልፈው አመት የፈረመውንና አሁን ከክለቡ ጋር ያለውን ኮንትራት ጠብቆ በሚቀጥለው ክረምት ኤመራትን ለመልቀቅ ፈልጓል።

mail on sunday

 • • አርሰን ቬንገር አሌክሲ ሳንቼዝ በዚህ ክረምት ማንችስተር ሲቲን እንደማይቀላቀል ነገረውታል።
 • • ቼልሲ በሶስት ዓመት ጊዜያት ውስጥ ከ10 ጨዋታ በታች ከተስለፉ ተጫዋቾች ሽያጭ 100 ሚ.ፓ ማግኘት ችሏል።
 • • አትሌቲኮ ማድሪዶች ዲያጎ ኮስታን ከቼልሲ ለማስፈረም የተዘጋጁ ቢሆንም በውሰት አሳልፈው ግን አይሰጡትም። ይህ ማለት ደግሞ የስፔኑ ክለብ ባለበት ተጫዋች የማስፈረም እገዳ ምክኒያት እስከጥር ወር ድረስ እግርኳስ የማይጫወት ይሆናል።
 • • ዎልቭሶች በሊቨርፑልና ቼልሲ የሚፈለገውን የፖርቶውን ኮከብ ሩበን ነቨስን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀመሩ።
 • • ጆን ቴሪ ለአስቶን ቪላ ለመፈረም ይፋዊ የሆነ ንግግር ጀመረ።
 • • ኒውካሰል የማንችስተር ሲቲ እና እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነው ጆ ሃርት ፈላጊ ሆኗል።
 • • በርንሌዮች በኤቨርተን የተፈለገውን ማይክል ኪን ምትክ ይሆናቸው ዘንድ የሼፍልዱን ቶም ሊን እየማተሩ ነው።

the sun on sunday

 • • ሆዜ ሞሪንሆ አልቫሮ ሞራታን ከሪያል ማድሪድ ቢያዛውሩም ባኤቨርተኑን አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ ላይ አሁንም ድረስ ፍላጎት አላቸው።
 • • ዋይኒ ሩኒ የኮንትራት አማራጩን ከፍ በማድረግ በማንችስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሊቆይ ይችላል።
 • • ኤቨርተን በአስገራሚ ሁኔታ ለአርሰናሉ አጥቂ ኦሊቪየ ዥሩ 20 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።
 • • አርሰናል ለናፖሊው ኮከብ ጆርጊንሆ ያቀረቡት 15 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ውድቅ ተደረገበት።

sunday express

 • • የማንችስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ፣ ጆ ሃርትን ወደተቀናቃኙ ዩናይትድ እንዲዛወር ፈቃደኛ ሆነ።
 • • የአርሰናሉ ተከላካይ ሄክቶረ ቤለሪን በአውሮፓ ከ21 ዓመት በታች ፍፃሜ ላይ ሁለተኛ በመውጣታቸው ሜዳዩን ያደረገ ብቸኛ ተጫዋች በመሆኑ የማህበራዊ ሚዲያው መሳለቂያ ሆኗል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *