Skip to content

ሃይለማርያም ለፊሊስጤም ኤርትራን ምሳሌ አድርገው ምክር ለገሱ፤ በ2020 አፍሪካ ጥይት ኮሽ አይልም?

 

ኤርትራ ከኢትዮጵያ በሕዝብ ፍላጎት እንደተገነጠለች በመጥቀሰ ሕዝብ በግልጽ የሚናገረውን ጉዳይ ” እኛን ሰዎች ኤርትራን ሸጣችኋል እያሉ ያሙናል” በሚል አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ መስጠታቸው ተገለጸ። “ሕዝቡ” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ” ሕዝቡ ከኢትዮጵያ መገንጠል በመፈለጉ ተገነጠለ” ሲሉ መንግስታቸው የህዝብን ድምጽ መሰረት አድርጎ ውሳኔውን እንደተቀበለ አመላክተዋል።

ይህ የተባለው የፊሊስጤም ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አባስ አዲስ አበባ ሆነው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እስራኤልን ሁለት ጊዜ ሲጎበኙ ፍልስጤምን ዝም በማለታቸው የተሰማቸውን ቅሬታ በገለጹበት ወቅት ነው። ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት ተገኝቶ መዘገቡን የጠቆመው ሪፖርተር እንዳለው አባስ በአገራቸውና በእስራኤል መካከል ላለው ችግር በተመለከተ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ድጋፍ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ ወይም ሃይለማርያም ደሳለኝ እስራኤል ላይ ጫና እንዲያሳደሩ ይሁን ሌላ የድጋፉ አይነት አለተብራራም።

በስፍራው ተገኝቶ የሰማውን እንዳሰፈረ የጠቆመው ሪፖርተር ኢትዮጵያ በሁለቱ አገሮች መካከል ጣልቃ እንድትገባ የፊሊስጤሙ መሪ መጠየቃቸውን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በተደጋጋሚ ፍልስጤምን እንዲጎበኙ ተጋብዘው ግብዣውን ባመቀበላቸው ፕሬዚዳንቱ ቅር መሰኘታቸውን፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር የመጡ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል ብሏል።

በዚህ መነሻ ነበር አቶ ሃይለማርያም፣  ከዚህ በፊት ወደ እስራኤል ያቀኑት በግላቸው እንደሆነ በማስታወስ  ‹‹ፍልስጤምን መጎብኘት አለመቻሌን ከእስራኤል ጋር አታያይዙት፤ ሁሌ የማምነው በግንኙነትና በተሳትፎ ፖሊሲ ነው›› ብለዋል። አያይዘውም ‹‹እናንተም ሕዝቦቻችሁን መሠረት አድርጋችሁ በመካከላችሁ ያለውን ግጭት መፍታት ይገባችኋል፤ እኛን ሰዎች ኤርትራን ሸጣችኋታል እያሉ ያሙናል፡፡ እውነታው ግን የሕዝብ ውሳኔ ነው፤›› ሲሉ  መገንጠል የኤርትራ ሕዝብ ውሳኔ መሆኑን አመልክተዋል።  ሕዝቡ ከኢትዮጵያ መገንጠል በመፈለጉ የተገነጠለ መሆኑንም እንደ ምሳሌ አስይተዋል።

Related stories   ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

 ‹‹በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ውሳኔ ዘላቂነት ላይ ጥርጣሬ ቢኖረኝም ጅምሩ ጥሩ ነው፤ በማለት አባስ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በሁለቱ ባላንጣ አገሮች መካከል ስላለው ችግር ለተናገሩት መልስ መስጠታቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል። 29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ  በጎንዮሽ ስብሰባ ሁለቱ መሪዎች መገናኘታቸው ታውቋል። አቶ ሃይለማርያም ከፍሊስጤም ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ቃል መግባታቸው በዜናው ተጠቁሟል።

ሪፖርተር 29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጋር በተያያዘ የሚከተለውን ዘግቧል

29ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ከ20 የማይበልጡ የአፍሪካን መሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2020 አፍሪካን ምንም ዓይነት ኮሽታና የጥይት ድምፅ የማይሰማባት አኅጉር ለማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በዚህ ጉባዔ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና እንዲኖር የሚፈቅድ አዋጅን ማፅደቅ የተመለከተ ነው፡፡ ስለነፃ የንግድ ቀጣና ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኒጀር ፕሬዚዳንት ማሃማዱ ኢሱፍ፣ ድርድሩ አገሮች እስከ 90 በመቶ የሚደርሱ የሌሎች አገሮችን ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ አገራቸው እንዲያስገቡ ለማስቻል የሚደረግ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የአገሮች ምርት ወደ አባል አገሮች ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ በማሰብ ያቀደው ኅብረቱ እክል እንዳጋጠመው መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያም ከቀረጥ ነፃ ከሚገባ የምርት መጠን አንፃር የኅብረቱን የንግድ ቀጣና ስምምነት ሳትቀበለው ቀርታለች፡፡

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የዙምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ 300 ላሞች ለአፍሪካ ኅብረት በስጦታ የሰጡ ሲሆን፣ ካስፈለገ በማለት የላሞቹን ዋጋ አስበው አንድ ሚሊዮን ዶላር ለኅብረቱ በስጦታ መልክ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ስጦታ የኅብረቱን የበጀት ጉድለት ለመሙላት ሌላ አዲስ አማራጭ ሆኖ እንዲቀርብና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎችም ይህን አርዓያ እንዲከተሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በዋናነት በሦስት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ውሳኔ እንዳስተላለፈ የኅብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት በጉባዔው መዝጊያ ላይ ገልጸዋል፡፡ የመጀመሪያው አጀንዳ ኅብረቱን እንደገና ማደራጀት የተመለከተ ሲሆን፣ የአፍሪካ ኅብረትን እንደገና ለማደራጀት የተሰየመውን ኮሚቴ በዋና ኃላፊነት ሲመሩት የነበሩት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፓል ካጋሜ ያቀረቡትን ሪፖርት አድምጦ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ሁለተኛው ርዕሰ ጉዳይ የአኅጉሪቱ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በሚጎለብትበት ላይ ውሳኔ መተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ሦስተኛና የመጨረሻው ጉዳይ በአኅጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ በሚሰፍንበት ላይ የኅብረቱ አባል አገሮች ቁርጠኛ ሆነው እንደሚሠሩ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ እየተባባሰ የመጣውን አሸባሪነት ለመከላከልም፣ ኅብረቱ በገንዘብ መደራጀት እንዳለበት ስምምነት ላይ መደረሱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Related stories   ወርቃማ ድል የተጎናጸፍነው ትልቁን ስዕል ማየት የሚችሉ ፣ ችግሮቻቸውን የመፍታት ልምድ ያላቸው እናትና አባቶች ስላሉን ነው – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

በምሥራቅ አፍሪካ በተለይም ከኳታር ቀውስ ጋር ተያይዞ ፍጥጫ ውስጥ ያሉትን ኤርትራና ጂቡቲን ለማሸማገል ኅብረቱ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ኤርትራ ሁለቱን አገሮች በሚያዋስነው ድንበር የተሰየመውን የእውነታ አፈላላጊ ቡድን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነች ለኅብረቱ አገሮች ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ኅብረቱ ይህንን ችግር የሚያጣራ ኮሚቴ በቅርቡ ተቋቁሞ ችግሩን ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጂቡቲ ኳታር የሁለቱን አገሮች አወዛጋቢ ድንበር ጥላ ከወጣች በኋላ የአፍሪካ ኅብረት የእውነታ አፈላላጊ ቡድን እንዲያሰማራ ከመጠየቋም በላይ፣ ኅብረቱ ተጠባባቂ ኃይል እንዲያሰማራ ጥሪ አቅርባለች፡፡ ለዚህም የአፍሪካ ኅብረት በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ብላለች፡፡ ጂቡቲ ኤርትራ አወዛጋቢውን ድንበር ተቆጣጥራለች በማለት ክስ ማሰማቷ አይዘነጋም፡፡ ኤርትራ የእውነታ አፈላላጊ ቡድኑን አልቀበልም ማለቷን ኢጋድ ማስታወቁ፣ የአካባቢውን ሰላም እንዳያደፈርስ ሥጋት ፈጥሯል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የደኅንነት ኮሚሽነር ኢስማኤል ቼሪጉዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በሁለቱ አገሮች ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተሰምቷል፡፡

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Copyright - zaggolenews. All rights reserved.

Read previous post:
MONACO QUOTE ARSENAL HUGE PRICE FOR LEMAR, 80 ሚሊዮን ፓውንድ!!

ቶማስ ለማርን የሚፈልጉት ክለቦች በርካታ ናቸው። በርካታ ብቻ ሳይሆኑ አሉ የሚባሉት ክለቦች ናቸው። አስገራሚው የተጨዋቹ መፈለግ ብቻ ሳይሆን በተቃራኒው ሞናኮ...

Close