– አቻምየለህ ታምሩ

ሌላው ተክለሚካኤል «ጎንደር ጎንደር ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ዋልታና ማገር» በጣም annoy አደረገኝ ያለው ምናልባት ታሪካችንን ስላላወቀው ፈረንጆቹ እንደሚሉት «a text without a context is only a pretext» ሆኖበት ሊሆን ይችላል። ታሪካችንን ለሚያውቅ ሰው «ጎንደር ጎንደር ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ዋልታና ማገር» የሚለው አገላለጽ አናዳጅ ሳይሆን ገላጭ ሆኖ ነው የሚያገኘው። ማንም ስምንተኛ ክልፍ የደረሰ ተማሪ ፈርሳ የነበረችው ኢትዮጵያ አንድነት የተጀመረው ጎንደር፤ ጀማሪውም ዓፄ ቴዎድሮስ መሆኑን ያውቃል። ዋልትና ማገር ማለት ምን እንደሆነ የሚያውቅ ደግሞ የኢትዮጵያ ዳግም አንድነት ጅማሮ ማዕከል የሆነችዋ ጎንደር ዋልታና ማገር መባሏ ለምን እንደሚያበሳጨው ሊገባኝ አይችልም።

የካናዳው ተክለሚካኤል አበበ «ጎንደር» በሚለው የቴዎድሮስ ካሳሁን አዲስ ዘፈን መናደዱን ከሰሞኑ ከአቶ ክንፉ አሰፋ ጋር በሲያትል ባደረገው «ክርክር» ተናግሯል። ተክለሚካኤል በቴዲ የጎንደር ዘፈን የተናደደበትን ምክንያት ሲያብራራ አንድም ዘፈኑ «ብሔርተኞች» ያላቸው ፖለቲከኞች የዓፄ ቴዎድሮሷ ኢትዮጵያ ተጭና፣ ጨፍልቃና ማንነታችንን ያጠፋች ኢትዮጵያ ናት ስለሚሉ መስማት የማይፈልጓትን ኢትዮጵያ ስለሚያጎላ፤ ሁለትም «ጎንደር ጎንደር ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ዋልታና ማገር» የሚለው የዘፈኑ ግጥም በጣም ስላናደዱው በተክለሚካሄል አገላለልጽ annoy የሚያደርገው ስንኝ በዘፈኑ በመካተቱ መሆኑን ገልጧል።

ተክለሚካኤል አበበ ብሔርተኞች ከአማራ አንጻር የቀፈቀፉትን የውሸት ታሪክ እንዳለ የተቀበለው ይመስላል። እስቲ የትኛው ብሔርተኛ ፖለቲከኛ ነው በጭካኔ ከዔፄ ቴዎድሮስ የተሻለ ሩህሩህ አባት ነበረኝ የሚለው? እስቲ ጎላ ብለው የሚሰሙትን የትግራይና የኦሮሞ ብሔርተኞች «የኛ ናቸው» የሚሏቸው የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ዘመን «አባቶቻቸው» ምን አይነት «የጎበዝ አለቆች» እንደነበሩ እንይ።

የትግሬው በዝብዝብ ካሳይ ወይንም ዓፄ ዮሐንስ ጎጃምን ቤት እየዘጉ ያቃጠሉ፤ ለምለሙን ምድር ድምጥማጡን ያጠፉ፤ ወሎን በኃይማኖት አሳበው የጨፈጨፉ፤ የእህታቸውን ባል ንጉስ ተክለጊዮርጊስን ሳይቀር አይን በጋለ ብረት አፍርጠው በዱልዱም ያረዱ፤ እጅና እግር የሚቆርጡ፤ ከንፈርና አንፍንጫ የሚፎንኑ ጨካኝ እንደነበሩ ታሪክ የመዘገበው ሀቅ ነው።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ራስ አሉላንም ብንወስድ እ.ኤ.አ. በ1886 ዓ.ም. በባሕረ ነጋሽ ባርካን ክልል ባካሄዱት ወረራ ሁለት ሦስተኛውን የኩናማና የናራ ሕዝብ እንደጨፈጨፉ፤ የደጋማው ባሕረ ነጋሽ ገበሬዎችን አፈናቅለው መሬታቸውን በሙሉ እንደወረሱ፤ በኤርትራ ደጋማው አካባቢ የሚኖሩትን ባላገሮች ቤሳ ቢስቲ ሳያስቀሩ እንደዘረፉ፣ ሁሉንም ኤርትራውያን በክልላቸው አስተዳደር ባጠቃላይ እንዳገለሏቸውና አስመራ ከተማን አቃጥለው እንዳጠፏት ተመዝግቧል።

በ1800ዎቹ የነበረውን የኦሮሞ አባ ገዳ፡ አባ ጉጂንም ብንወስ ሰውየው በጭካኔ የሚዝናና sadist የነበረ ሰው ነበር። አባ ገዳ ጉጂ በምርኮ የያዛቸውን ሰዎች አይን እንደሙጀሌ እያወጣ ፤ጭንቅላታቸውን እያስፈለጠ የሚደሰት ጨካኝ እንደነበር ዶሴው ያሳያል።

ዳግማሮስ ካሳ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ከሰሩት የተለየ ጭካኔ ምን ሰርተው ነው የጭካኔ ቁንጮ፤ ብሔርተኞችን የሚያስኮፉ ተደርገው የሚቆጠሩት? በራሳቸው ዘመን መመዘን ያለባቸውን ባላባቶች፡ በዚህ ዘመን መለኪያ ሰፍሮ እንዲህ ነበሩ ማለት፡ የራስን ድንቁርና ከማወጅ በቀር ትርጉም ያለው ንጽጽር ሊሆን አይችልም።

የዛሬዎቹንና የቀድሞዎቹን [ነገሥታቱን] መሪዎች በዚህ ዘመን ሚዛን ማወዳደር ማለት፤ የዛሬዎቹ የዘመናዊ ትምህርት እና ፍልስፍና ንክኪ [exposure] ‘ውጤት’ የሆኑ ገዢዎችንን አስተሳሰብና ዝንባሌ፡ ካለፉት የዘመኑ መንፈስ ውጤት ከሆኑት መሪዎች ጋር አንድ ረድፍ በማስቀመጥ፤ ነገስታት መሪዎችን ከፍ ባለ መለኪያና ፍትሀዊ ባልሆነ ሚዛን እየሰፈሩ፥ የዛሬዎቹን ግን በጣም ዝቅ ባለ ልኬት በመመዘን፡ ትይዩ ሊሆኑ ወደማይችሉበት ሚዛን እንዲቀመጡ ማድረግ እንደማለት ነው። በተመሳሳይ መንገድ፡ የዛሬዎችንና የመጪዎችን መሪዎች ባንድ ረድፍ ወይም ባንድ መደብ ማስቀመጥ ማለት፡ ሚዛናዊ የማይሆንና መጪዎቹን ካሁኖቹ በጣም በማግዘፍ፤ ያሁኖቹ ከመጪዎች እንዳይመጣጠኑ አድርጎ ባንድ ሚዛን እንደማስቀመጥ ማለት ነው። ባጠቃላይ ያለዘመኑ በሌላ ዘመን መስፈርት መመዘን፣ መተቸትና መናቅ ቀርቶ ማሞገስም እንኳ ከፍተኛ ድንቁርና ነው።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በዚያ ላይ የባላባት አስተዳደር [Empire State ] በሁሉም የአገራችን ብሔረሰቦች የጎበዝ አለቆች ዘንድ ይሰራበት የነበረ መሆኑ ተዘንግቶ ቴዎድሮስ ወይንም ምኒልክ እንዳመጡት አድረጎ ማስቀመጡ ትልቅ ስህተት ነው። ቴዎድሮስን ከዘመኑ የጎበዝ አለቆች የሚለየው ሌሎቹን እጥረት በመስበር ፈርሳ የነበረችውን አገር አንድ ለማድረግ የሰነቀው ራዕይ ነው። ይህ ከዘመኑ የላቅ ትልቅ ራዕይ ደግሞ በዘፈንም ሆነ በሌላ ጥበብ ቢነሳ ያንስበታል እንጂ የሚያሳድድ ሊሆን አይችልም።

ሌላው ተክለሚካኤል «ጎንደር ጎንደር ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ዋልታና ማገር» በጣም annoy አደረገኝ ያለው ምናልባት ታሪካችንን ስላላወቀው ፈረንጆቹ እንደሚሉት «a text without a context is only a pretext» ሆኖበት ሊሆን ይችላል። ታሪካችንን ለሚያውቅ ሰው «ጎንደር ጎንደር ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ዋልታና ማገር» የሚለው አገላለጽ አናዳጅ ሳይሆን ገላጭ ሆኖ ነው የሚያገኘው። ማንም ስምንተኛ ክልፍ የደረሰ ተማሪ ፈርሳ የነበረችው ኢትዮጵያ አንድነት የተጀመረው ጎንደር፤ ጀማሪውም ዓፄ ቴዎድሮስ መሆኑን ያውቃል። ዋልትና ማገር ማለት ምን እንደሆነ የሚያውቅ ደግሞ የኢትዮጵያ ዳግም አንድነት ጅማሮ ማዕከል የሆነችዋ ጎንደር ዋልታና ማገር መባሏ ለምን እንደሚያበሳጨው ሊገባኝ አይችልም።

በስተመጨረሻም ተክለሚካኤል አበበ የዓፄ ቴዎድሮስ ታሪክ መጉላቱ ብሔርተኞች የዓፄ ቴዎድሮሷን ኢትዮጵያ ሊጭኑብን ነው የሚለው ቅስቀሳቸው እንዲሰምርላቸው ያግዛቸዋል ብሏል። ተክለሚካኤል እዚህ ላይ የዘነጋው ትልቁ ነገር ዓፄ ቴዎድሮስ ዛሬ ቢኖር ኖሮ ልክ በዘመኑ እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ከተክለሚካኤልም ሆነ ብሔርተኛ ከሚላቸውም ፖለቲከኞች ሁሉ የላቀ ተራማጅና ባለራዕይ መሪ ሊሆን እንደሚችል አለመገመቱ ነው። አለም ባልሰለጠነበት ዘመን በያካባቢያችን ከነበሩት የጎበዝ አለቆች ሁሉ የላቀ ተራማጅና አርቆ አሳቢ የነበረው ቴዎድሮስ ዛሬ በዚህ ዘመን በድጋሚ የመፈጠር እድል ቢያገኝ ኖሮ ከተክለሚካኤልምን ሆነ ከተክሌ ብሔርተኞች አልያም በካድሬዎቹ «ታላቁ መሪ» እየተባለ ከሚሞካሸው ከመለስ ዜናዊ ስንት እጥፍ የላቀ አስተሳሰብ የሚኖረው ተራማጅ ክስተት ነበር የሚሆነው።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ልጅ ተክሌ:- የዓፄ ቴዎድሮስ ዘመን የመገበርና የማስገበር እንጅ የሪፈረንደም ዘመን አለመሆኑን [ስለራቅናት] ያገራችንን ታሪክ ባናነብ እንኳ በቅርብ ከምንኖርባቸው ከሰለጠኑት ከጀርመኑ ቢስማርክና ከጣልያኑ ጋሪባልዲ ታሪክ መማር መቻል አለብንኮ። ብሔርተኖች የምትላቸውን ደግሞ በጭካኔ ከቴዎድሮስ የተሻለ አባት ካላችሁ እስቲ ንገሩኝ በላቸው?! ብሔርተኞች እንደሚሉት ዓፄ ቴዎድሮስ ተጭኖ፣ ጨፍልቆ ማንነታቸውን ካጠፋ ለምን ማንነታቸው አልጠፋም ታዲያ? እስኪ ጠይቃቸው?

ወያኔን [ በተክሌ አገላለጽ ኢሕአዴግ] ለንጽጽር አስገብተህ ያቀረብኸው ነገር ግን አይነሳ ይቅር። በቢሊዮን ዶላር የውጭ ርዳታና ብድር እየጎረፈለት፤ ከሌላው አለም ሊያገኘው የሚችለውን ስልጣኔ ሁሉ ‘እያገኘ’፡ አገር ማስተዳደር ያቃተው ነውረኛ የትግራይ አገዛዝ፤ በጠላት ተከበው፡ ከግራ ከቀኝ የሚመጣባቸውን ጠላት በትክሻ ወይም ባህያ እንዲሁም በበቅሎ የተያዘ በሶ፣ ቆሎና ጥሬ እየበሉ፡ በወጣ ገባው አስቸጋሪ አገራችን እየተንገላቱ፡ በደምና በመከራ ነፃ አገር ያቆዩ አርበኞችን፤ ለኑሮ አስፈላጊያቸው የሆነውን ነገር በሀገራቸው ውስጥ ሰርተውና አሰርተው ራሳቸውን ችለው የኖሩ ጀግኖች የመሰረቷትን አገር እያስተዳደረ፡ የመሰረቷትን ግን ኋላቀር፣ ነፍጠኛ፣ አድሃሪ፣ ቅኝ ገዢ፣ ባ ጨቋኝ፣ ወዘተ…እያለ የሚያጠለሸውን የትግራይ ባሪያ አሳዳሪ የአፓርታይድ አገዛዝ አንተ ባቀረብኸው አስረጂ ትይዩ ሊቀርብ አይችልም። የትግሬ ነጻ አውጭ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ [ማለትም ሌላውን በቅኝ ግዛት ይዞ] ሌላውን እንዲያ ነው እንዲህ ነው ማለቱን ከቁም ነገር መቁጠሩ የተሻለ ሀሳብ ያለቀብን ያስመስላል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *