Semayawi Englishአባላቶቹና በየደረጃው ያሉ አመራሮቹ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንግልት፣ እስርና፣ ማሳደድ እየደረሰባቸው እንደሆነ ያስታወቅው የሰማያዊ ፓርቲ፣ የፓርቲው መዋቅር በአማራ ክልል መፈረሱን አመለከተ። የፓሪወ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዳስታወቁት አቤት ቢሉም ሰሚ ማግኘት እንዳልተቻለና ፓርቲው ላይ ህገ መንግስትን የጣሰ የማፍረስ ተልዕኮ እየተከናወነ ነው።

“እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ዋናው ሥራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዓላማዎችን ለህዝቡ ማስተዋወቅ መሆን ሲገባው፣ ስራችን እስረኛ መጠየቅ እና ስንቅ ማመላለስ ሆኗል” ሲሉ አቶ የሺዋስ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል። ፓርቲው ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በስፋት የደረሰው በደል የተብራራ ሲሆን፣ በህግ ተመዝግቦ የሚሰራን ፓርቲ በመመሪያ ህልውናውን የማክሰም ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ቦታና ስም በመጥቀስ አመልከተዋል።

በደቡብ ክልል ስለጤ ዞን፣ በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን ፓርቲያቸው ችግር እንደገጠመው ያስታወቁት አቶ የሺ ዋስ በአማራ ክልል የሚሆነው የከፋ እንደሆነ ተናግረዋል።  በሰሜን ጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ ደብረማርቆስ የፓርቲው አመራሮች በመታሰራቸው ያፓርቲው መዋቅር መፍረሱን አመልክተዋል። ፓርቲያቸው የአማራ ክልል ላይ ሰላማዊ ትግል እንዳያከናውን ከተከለከለ በግልጽ እንዲነገራቸው ተማጽነዋል።

Related stories   The National Movement of Amhara(NaMA) Denounces International Violations of the Sovereignty of Ethiopia

ፓርቲው በፌስ ቡክ ገጹ  “እነ ማሩ ዳኘውና መልካሙ ታደለ ፍ/ቤት ቀረቡ” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ዜና አሰራጭቶ እንደነበር የሚታወሰ ነው።

ነሐሴ 1/2008 በባህርዳር ከተማ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ዛሬ ሀምሌ 10/2009 ፍ/ቤት የቅረቡት በነ ማሩ ዳኘው ዋሴ መዝገብ 9 የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትና ደጋፊዎች ከ11 ወራት እስርና እንግልት በኃላ የፈጠራ ክስ ተመስርቶባቸው ፍ/ቤት ቀርበዋል።

ለዚሁ ጉዳይ ትላንት እሁድ ሐምሌ 9/2009 ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር የተጒዙት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የህዝብ የግንኙነት ኃላፊው መምህር አበበ አካሉ፣ በቅርቡ ከእስር የተፈታው መቶአለቃ ጌታቸው መኮንን ከመኢአድ፣ አቶ አበበ ጌትነት እና የተከሳሾች ቤተሰቦች በችሎቱ ተገኝተዋል። አቶ ማሩ ዳኘው፣ አቶ መልካሙ ታደለ፣ አቶ እጅጉ አስማረና ወጣት ወርቁ ጥላሁን ከማረሚያ ቤት የቀረቡ ሲሆን አቶ እጅጉ አጥፊዎቹ መቀጣት ሲገባቸው እኔ በሌለሁበት የፓርቲ አባል ተብየ በዚህ እድሜዬ እሰቃያለሁ ሲሉ ብምሬት ተናግርዋል።

ዳኞች ክሱን በማንበብ የተከሳሾችን ምላሽ የጠየቁ ቢሆንም ክሱ የደረሳችው ከ2 ቀናት በፊት በመሆኑና ዐቃቤ ህግም ተጨማሪ ማስረጃዎች አሉኝ ስላለ ከቀጠሮ በፊት እንዲያቀርብ ተከሳሾቹም ለሀምሌ 19/2009 እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፓርቲው በዚህ ጉዳይና በአማራ ክልል በተለይ በባህርዳር፣ በደብረማርቆስ፣ በጎንደርና በደሴ እየደረሰበት ስላለው እንግልትና ወከባ ነገ ሐምሌ 11/2009 ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ከፓርቲው ጽ/ቤት ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

“ተቀናቃኝ” ፓርቲዎች አገሪቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንባት ” ድርድር ” የሚባል ውይይት በሚያደርጉበት በአሁኑ ወቅት አንድ ፓርቲ መዋቅሩ በድንብና በውስጥ ለውስጥ መመሪያ እንዲፈርስ መደረጉ ይፋ ሲሆን መስማት አስፋሪ እንደሆነ የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። እንዚህ ክፍሎች እንደሚሉት መነጋገር ጥሩ ጅምር ቢሆንም ጎን ለኦጎን ፓርቲ የማክሰምና ፖለቲከኞችን የማጥፋት ዘምቻ በይፋ ሲካሄድ አላየሁም አለሰማሁም ማለት አግባብ አይሆንም። ድምሩም ሃፍረት ነው።

Related stories   PM Abiy, U.S Senator Inhofe Hold Encouraging Conversation about Tigray

በሌላ በኩል የቪኦኤው ሰለሞን አባተ የሚከተለውን ዘግቧል

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *