via ዝግጅት/ የቼልሲ ተጫዋቾች በኩንጉፉ የታገዘ አስቸጋሪ ልምምድ ሰሩ — ኢትዮአዲስ ስፖርት
የቼልሲ ተጫዋቾች የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ጉዟቸውን በዚህ ሳምንትም ቀጥለው በሻውሊን መነኩሴ እገዛ ከዚህ ቀደም በእግርኳስ ላይ ያልተለመደ የልምምድ ጊዜ አሳልፈዋል።ሰማያዊዎቹ በአሁኑ ጊዜ የእሲያ ጉዟቸው አንዱ አካል በሆነው እና ከአርሰናልና ባየር ሙኒክ ጋር በተጫወቱበት ሲንጋፖር ይገኛሉ። በእቅዳቸው መሰረት ከባየር ሙኒክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት የተሸነፉት ቼልሲዎች በኩንጉፉ ማርሻልአርት ባለሙያው የቡድሃ መነኩሴ አለማማጅነት በተለይም ለተከላካዩ ጋሪ ካሂል ከባድ የሆነ ልምምድ ሰርተዋል።
ጋሪ ካሂል “የፈረስ አቋቋም” የሚባለው ልምምድ በእጅጉ ያስቸገረው ይመስላል
ቼልሲዎች አብዛኛውን የክረምቱን ልምምዳቸውን የሚያሳልፉበት ሲንጋፖር ቡድሂዝም በሰፊው ተከታይ ያለው እምነት ነው።
የመኃል ተከላካዩ እንግሊዛዊው ጋሪ ካሂል የማርሻል አርቱ እንቅስቃሴ በሆነው እና ሁለት ጡቦችን በሁለት እጆች እንዲሁም በራስ ቅል ላይ ደግሞ በውሃ የተሞላ ክፍት ሳህን አድርጎ “ሆርስ ስታንድ” የተሰኘውን አቋቋም ለመስራት ሲቸገር ታይቷል።
ይህ ብቻም ሳይሆን ተከላካዩ በጨርቅ የታሰሩ ጡቦችን በእንጨት ላይ በመጠምጠም የእጅ ጥንካሬን ለመስራት የሚደረገውን ልምምድ ለማከናወን በእጅጉ የተቸገረ ተጫዋች ሆኗል።
ይህን ልምምድ ቲቧ ኮርትዋ፣ ዊሊ ካባሌሮና ማርኮስ አሎንሶም ሰርተውታል።
የሰማያዊዎቹ ቁጥር 1 ግብ ጠባቂ የሆነው ኮርትዋ በኩንጉፉ እንቅስቃሴ መሰረታዊ የሆነውን በጣት የመቆም አቋቋምን ለመስራት ያደረገው ሙከራም በቡድን አጋሮቹ ዘንድ ፈገግተን ጭሯል። በአንፃራዊነት የተሰጡትን የኩንጉፉ ልምምዶች በተገቢው በመስራት ተወዳዳሪ ያልነበረው ስፔናዊው ተከላካይ አሎንሶ ነበር።