ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በተመሳሳይ በወታደራዊ ዘርፍ ለመስራት የሚያስችላትን ስምምነት በካቢኔ ደረጃ ማጽደቋ ታውቋል። ባለፈው ረቡዕ ጸደቅ የተባለው ስምምነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያድግ መሆኑን ፋና አመልክቷል።

የደቡብ ሱዳን ካቢኔ የሀገሪቱ መንግስት በመከላከያ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ። የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዌዪ፥ ካቢኔው ያፀደቀው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ሚኒቴሮች በሚሰሩ ስራዎች ላይ ተመስርቶ እያደገ የሚሄድ ነው ብለዋል።

የደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ኩዎል ማኛንግ ያቀረቡትን ረቂቅ የመከላከያ ስምምነትም ካቢኔው ተቀብሎ ማፅደቁን ነው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ያስታወቁት። ሁለቱ ሀገራት ባላፈው ጥቅምት ወር 2009 ላይ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ከስመምነቶቹ ውስጥም የመከላከያ ዘርፍ አንዱ ነው።

ባሳለፍነው አርብ በደቡብ ሱዳን ካቢኔ የፀደቀው ስመምነተም ሀገራቱ የሁለቱ ሀገራት የጋራ ድንበር ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል። የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባሳለፍነው ጥር ወር 2009 ዓ.ም በደቡብ ሱዳን ጁባ የአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በጉብኝቱ ወቅትም ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። ሀገራቱ በፀጥታና ደህንነት ጉዳይ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በኢንቨስትመንት በኢኮኖሚና ንግድ ጉዳይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጁባ በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላም የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለጻቸው ይታወሳል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ከር ማያርዲት በበኩላቸው፥ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ ዘርፍ ያለውን ትብብር ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ፍላጎት እንዳላቸው ፋና በዘገባው አመልክቷል።

South Sudan’s cabinet approves defense cooperation deal with Ethiopia

South Sudan’s cabinet on Friday approved a military cooperation deal signed with neighbouring Ethiopia, saying the defense pact will be developed into a series of agreements between the two countries.

 “It is an agreement or a Memorandum of Understanding (MOU) which will be developed into a series of agreements between the two ministries of defense for corporation in all aspects of defense, Information Minister, Michael Makuei said after the cabinet meeting.

Makuei pointed out that the cabinet approved the military cooperation agreement presented by defense minister Kuol Manyang.

In October 2016, South Sudan’s President Salva Kiir and Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Desalegn signed a series of cooperation agreements, including a security and military arrangement to stop hosting armed opposition groups in their respective countries.

The deal signed at the presidential palace in Juba called on Ethiopia not to support armed groups, probably targeting members of the opposition under the leadership of the former First Vice President, Riek Machar.

Ethiopia led the mediation of the peace process between Kiir and Machar which was signed in August 2015, but its implementation was disrupted by the resumption of war between the two groups in July 2016 in the capital Juba.

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *