Share and Enjoy !

Shares

አቶ በቀለ ገርባ ክሳቸው በሽብር ወንጀል ስር ሊታይ አይችልም በሚል ውድቅ የተደረገ የክስ ሃሳብ እንደገና ተጠቅሶባቸው የዋስትና መባታቸውን እንደተከለከሉ ጠበቃቸው አስታወቁ። ጠበቃቸው ይህንን ያስታወቁት አምስት ጊዜ ሲንከባለል የቆየውን የዋስትና ጥያቄ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ፍርድ ቤት ውድቅ ካደረገው በሁዋላ ነው።

bekele-gereba

ቀደም ሲል ውጪ ካሉ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸውና ኦሳ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል በሚል በተራ ቁጥር 2 እና 3 ተመስርቶባቸው የነበረው ክስ ማስረጃ አልቀረበበትም በሚል በሽብርተኛ ወንጀል ሊያስከስሳቸው  እንደማይችል፣ በዚሁም አግባብ በተራ የወንጀል ህግ ጉዳያቸው ሊታይ እንደሚገባ ውሳኔ ተሰጥቶ ነበር።

በዚሁ መሰረት የአገሪቱን ህገ መንግስት ጠቅሰው የዋስትና መብታቸውን እንዲከበርላቸው የአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች ጠይቀው ነበር። ለአምስት ጊዜ የተለያየ ምክንይት እየተሰጠ ሲንከባለል የቆየው ብይን በመጨረሻ ውድቅ ተደርጓል። ለዋስትናው መብት መከልከል ዋና ምክንያት የሆነው ” ቢፈቱ ከአገር ይወጣሉ ፣  ከተፈቱ ዳግም የማነሳሳት ስራ ይሰራሉ ” የሚል ነው።

Related stories   የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ የተፋጠነ ፍትሕ መስጠት እንዲቻል ከቀጠሮ ቀን በፊት ችሎት ሰየመ

ይህ አቃቤ ህግ ያቀረበው መከራከሪያ ቀደም ሲል ማስረጃ ያልቀረበበት ተብሎ ውድቅ የተደረገ ሲሆን፤ አቶ በቀለ ገርባ ቀደም ሲል ታስረው ሲፈቱ ከአገር ውጥተው ተመልሰዋል በሚል ጠበቃቸው ተከራክረዋል። አቶ በቀለ በበኩላቸው ” ደሮም ፍትህን አገኛልሁ ብዬ አላስብም” ማለታቸው ተሰምቷል።

” ፍትህ አገኛለሁ ብዬ አስቀድሜም አላስብም እዚህ የምንመላለሰው ጉዳዩን የዓለም ህብረተሰብ እንዲያውቀው ነው” ያሉት አቶ በቀለ ገርባ  ቀደም ሲል ጉዳዩን የኦሮሚያ ፍርድ ቤት በውክልና የሚያየው ሆኖ ሳለ፣ መከልከሉ ቀድሞውም የፍርድ አካሄዱን መዝመም እንደሚያሳይ  ተባግረዋል። ውሳኔውም ምንም እንዳላስደነቃቸውና የሚጠብቁት እንደሆነ አመልክተዋል።

በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸው ሰነዶች አቶ በቀለ በተለይ የጉራጌና የሥልጤ  ተወላጆች ከኦሮሚያ መውጣት እንዳለባቸው በመግለጽ ያስተላለፉት ትዕዛዝ፣ ተስማምተው የሚኖሩ ሕዝቦችን ለአመፅ ማነሳሳት መሆኑን እንደሚያስረዱና ምንም እንኳን የፖለቲካ ፓርቲ አመራር ቢሆኑም፣ መንግሥትን ማውረድ የሚቻለው በምርጫ ብቻ በሚደረግ ውድድር ሒደት መሆኑን እያወቁ በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ ያስተላለፉት መልዕክት አግባብ አለመሆኑን የሚያስረዱ መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ በብይኑ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም አቶ በቀለ ዓቃቤ ሕግ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 14 እና 23(1) መሠረት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያገኘው ማስረጃ፣ ከላይ የተጠቀሱትን የሚያስረዱ ሆነው በመገኘታቸው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/አ 113(2) መሠረት በመቀየር፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 257(ሀ) ማለትም ‹‹መገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር›› የሚለውን መተላለፋቸውን በማስረዳቱ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

አቶ በቀለ በቃሬዛ ያምጡኝ እንጂ በራሴ ፈቃድ ወደ ችሎት አልመጣም በሚል መናገራቸው አይዘነጋም

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *