ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሸራተን አዲስ ሆቴል  በመሩት ሶስተኛው ሀገራዊ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የምምክር መድረክ ላይ፤ “እስከአሁን ከወጣቶቻችን ጋር የተጋጨነው ይበቃናል” ሲሉ መንግስታቸው ከችግሩ ስር እንጂ የችግሩ መገለጫዎች ላይ ትኩረት እንደማያደርግ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።

“አምስት የኪራይ ሰብሳቢዎች ቦታ እንዳለ ለይተን አውቀናል

በምክክር መድረኩ ላይ ከባሕር ዳር የንግዱ ዘርፍ፣ “በባሕርዳር ከተማ በግድ ሱቆች እንዲዘጉ እየተደረገ ነው። ድንጋዮች በመወርወር ዝጉ እየተባልን ነው። ሱቃችን ስንዘጋ መንግስት ደግሞ እያሰረን ነው። ስለዚህም መንግስት ከክልሉ ጋር በመተባበር ሁኔታዎችን ቢቆጣጠርልን። አሁንም በዚህ መልኩ የተያዙ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት አሉ” ሲሉ ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፣ “ባሕርዳር ላይ አሁንም በተወሰነ መልኩ አልቆመም። መገራገጭ አለ፤ እናቆመዋለን። የታሰሩ ሰዎች አሉ ለተባለው በጥናት ላይ የተመሰረተ ነው። ዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ በቀድሞውም የነበሩ፤ ሰዎች ናቸው። ከአሁን በኋላ የሀገሪቱን መረጋጋት በምንም ሒሳብ ለድርድር አናቀርብም። ማንም ሰው ሊሆን ይችላል፤ ወጣት እየቀሰቀሰ፣ ታክሲ እየቀሰቀሰ፣ ባጃጅ እየቀሰቀሰ፣ ሱቅ ዝጉ እያለ፣ ገንዘብ እየሰጠ እያሰማራ፤ ሕፃናትን ከፊት ለፊት እያደረገ ሕፃናቱን ከፊት ለማግኘት አናደርገውም። ሥሩን ፈትሸን፣ ሥሩን እንነቅላለን።” ብለዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አያይዘውም፤ “እስከአሁንም ከወጣቶቻነን ጋር የተጋጨነው ይበቃናል። ሥሩን ሳንነቅል አንተውም። እንደበፊቱ መንግስት እንደሆነ ይሆናል እከሌ ከተነካ… እንትን ይሆናል… የሚባል ጨዋታ አብቅቷል። እንኳን እነእንትና የሚባሉት ቀርቶ በአሁን ሰዓት የመንግስት ባለስልጣናት መያዣ መጨበጫ አጥተው ነው ያሉት። ሁለት ስለት ያለው ቢለዋ አንዱን ቆርጦ ሌላውን የሚያስቀርበት ሁኔታ የለም። እዚህ ውስጥ እገሌ የሚባል ባለስልጣን ስለማውቅ እንደፈለኩ እሆናለሁ የሚል ሰው ካለ፤ አሁኑኑ እጁን ይሰብስብ። የሚቀጥለው እርምጃ ወደ ንግዱ ማሕበረሰብ መግባት ነው። ይህች ሀገር ልማታዊ ካልሆነች፤ ይችህ ሀገር ሰላማዊ ካልሆነች፤ የማናችንም ሕይወት ዋስትና የለውም። ከዚህ በፊት ውስጥ ውስጡን የሚወሩ ነገሮች አሉ፤ እከሌ የሚባል ባለስልጣን ስለሚያውቅ አይነካም ይባላል፤ እስቲ እንደማይነካ እናያለን። እውነት ነው የምላችሁ፤ የማይነካ ሰው የለም። ምክንያቱም፤ ሀገር ይበልጣል። ከግለሰቦች ሀገር ይበልጣል። አማኝ ካለ ወደ እምነቱ ይሂድ፤ ሰውን የሚተማመን ካለ ግን አይሰራም። በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ትልቁ ምሶሶ፤ የህግ የበላይነትን ማስከበር ነው። ሌባም ቢሆን ራሱን የመከላከል መብቱ የተጠበቀ ነው። ሁሉም ነገር በሕግ የበላይነት የሚዳኝ ነው።”

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አክለውም፤ “አምስት የኪራይ ሰብሳቢዎች ቦታ እንዳለ ለይተን አውቀናል። አንዱ መሬት ነው። መንግስት የፈለገውን ያደርጋል የሚሉ አሉ። እኛ ግን የፈለግነው አናደርግም። ለምሳሌ ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ተደራድረን በሕገ ወጥ መንገድ የወሰዱትን መሬት እንዲመልሱ አድርገናል። ይህም ሆኖ የተጀመረውን ትግል ለማንቋሸሽ ብዙ እየተባለ ነው የሚገኘው። አሁን ላይ የመንግስትን ጥረት ካልገታነው እሳቱ የት እንደሚደርስ አይታወቅም በሚል የሚረብሹ አሉ። የፈለጉትን ቢሉ ትግላችን አጠናክረን እሳቱ መድረስ እስከሚችልበት ድረስ መሄዳችን አይቀርም።”

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገራሚ ጥያቄ ለመድረኩ አቅርበዋል። ይኸውም፤ “ለምን የንግዱ ማሕበረሰብ አንድም ጥቆማ አልሰጠንም? ንግድ ምክር ቤቱና ዘርፍ ማሕበራቱም አንድም ጥቆማ አልሰጡንም። ሕዝቡ ነው፤ የጠቆመን። ከእናንተ መካከል ሌባ ጠቁሚያለሁ የሚል ካል ይንገረኝ። ኃላፊነታችሁን ሳትወጡ መንግስት ላይ ደፍድፋችሁ የፀረ ሙስና ትግል በዚህ መልኩ ይሄዳል ብላችሁ ካሰባችሁ፣ አይሄድም። ከማንም በላይ ሌባ የምታውቁት እናንተ ናችሁ። ምንም የሌለው ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ የብዙ ፎቆች ባለቤት ሲሆን የምታውቁት፤ እናንተ ናችሁ። አብራችሁ የምትበሉት የምትጡት እናንተ፤ ናችሁ። በሰርግ በድግስ አብራችሁ የምተቆዩ፤ እናንት ናችሁ። ስለዚህ እኛን አከናንባችሁ፣ አሁን ላይ መንግስት ዘግይቶ እንዲህ እያደረገ… ብላችሁ ልትሄዱ አትችሉም፤ ጠቁሙ። ስለዚህ ኃላፊነታችሁን ተወጡ። መንግስት ጉልበት አለው፤ እስር ቤት አለው፤ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል፤ ስለዚህ የራሱን ስራ ይሰራል። እናተም የራሳችሁን ስራ ስሩ። ውድድሩ ፍትሃዊ እንዲሆን፣ ፍትሃዊ ያልሆነ ውድድር ጎጂ ነው በሉ። አራት የጥቆማ ቦታዎች አሉ። እነሱም፤ ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ፣ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ የምርመራ ቢሮ አለ፣ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪ አለ። በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ውስጥ አቤቱታ የሚቀበል በሚኒስትር ዴኤታ የሚመራ አለ።… የምንታገለው ኃይል አደገኛ ነው። የራሱ ኔትወርክ ያለው ሲሆን ሕዝባዊ ንቅናቄ በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ ካላንቀሳቀስን የመጨረሻውን ግብ ሊመታ አይችልም” የንግዱን ማሕበረሰብ መክረዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

sendeknewspaper

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *