qero oromo

በኦሮሚያ የተጠራው ቤት ውስጥ የመቀመጣ አድማ በተጀመረበት በዛሬው እለት ጭር ብለው የዋሉ ከተሞች መኖራቸው ተሰማ። የንግድ ቤቶችና የመጓጓዣ አገልግሎት በተቋረጡባቸው ከተሞች፣ አንዳንድ ነጋዴዎች ተገደው ሱቆቻቸውን እንዲከፍቱ ሲደረጉ፣ አገልግሎት ለመስጠት በተንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉ መንግስት በይፋ ያለው ነገር የለም።

ከኦሮሚያ ካሉበት አካባቢ ለዛጎል አስተያየት የላኩ እንዳሉት አድማው በተለይም የንግድ ተቋማት አካባቢ መጠነኛ ፍርሃት የታየበት ነበር። ፍርሃቱ ቢኖርም የማምረር ነገር እንደሚታይ ግን አልሸሸጉም። ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ያደሩት የግንኙነት ሰንሰለት እና የመረጃ ቅይይሩ አስገራሚና በሹክሹክታ መወያያ መሆኑን እነዚሁ ክፍሎች ጠቁመዋል።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

ማንኛውም መረጃ በተፈለገበት ወቅት፣ የተፈለገበት ቦታ እንደሚደረስና የግንኙነት ችግር አለ ብለው እንደማያስቡ ከአድናቆት ጋር የሚገልጹት ክፍሎች ” ኢህአዴግ ኦህዴድን ከስሯል” ባይ ናቸው። በሺህ የሚቆጠሩ አባላቱን ያሰናበተው ኦህዴድ በውስጡ የተፈጠረው መናጋት ሊድን የሚችል እንደማይመስላቸውም እነዚህ ክፍሎች ይጠቅሳሉ። በግንደበረትና አካባቢው የሚስተዋለው ይህ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች አምስት ቀን የታወጀው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ቀጣይነት ያሳስባቸዋል። የድሆች ነገር!!

ከሌሎች አካባቢዎች መረጃ ማግኘት ባይቻልም ቪኦኤ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአይን ምስክሮች አነጋሮ እንደዘገበው አድማው በታለመለት መሰረት ተጀምሯል። በዚሁ መሰረት አዲስ አበባ ዙሪያን ጨምሮ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። ህዝብ በጎዳና አይታይም። የመጓጓዣ አገልግሎት ተቋርጧል፤ በከፊል የተስተጓጎለባቸው ቦታዎች አሉ። አንዳንድ ተሽከርካሪዎችም ተሰባበረዋል።

Related stories   ሱዳን ክፉኛ ተመታ የወረረችውን መሬት ማስረከቧ ተረጋገጠ፤ ከዱላው በሁዋላ " ከኢትዮጵያ ጋር መረዳዳታን መልካም ግንኙነት እንሻለን" አለች

የሥራ ማቆሙና ቤት ወስጥ የመቀመጡ አድማ ዋና ምክንያቶች ከአቅም በላይ ተጥሏል የተባለውን ግብር፣ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎችና ከሶማሌ ጋር በሚያዋስኑ ስፍራዎች የሚፈሰውን ደም መንግስት ባስችኳይ እንዲያስቆም የሚጠይቁ ሲሆኑ ” ስርዓቱ በቃን፣ በአፈሙዝ አንገዛም” እስከማለት የሚደርስ መሆኑን ቪኦኤ ካነጋገራቸው ሰዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

ቪኦኤ ከተለያዩ ምንጮች አረጋገጥኩ እንዳለው በአዲስ አበባ አቅራቢያ ከሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች አንስቶ በደቡብ፣ በሰሜንና በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ከተሞች የንግድ ሱቆች መዘጋታቸው ታውቋል። በዘገባው ከምንግስት ወገን የተባለ ነገር አልተካተተም። አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት ግን የመንግስት ታጣቂዎች ሃይል እየተጠቀሙ ነው። ድብደባ የደረሰባቸው መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

Related stories   የአምነስቲ " ሽንቁረ ብዙ" ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምር

የቪኦኤ ሙሉ ዘገባ እነሆ 

ፎቶ ከፌስ ቡክ የተወሰደ

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *