ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ብድር ለማቅረብ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት የተስተናገደ አዲስ ደንበኛ የለም

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ብድር ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ መመሪያን ጥር ወር ላይ ቢያወጣም በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለሚሰማሩ አዲስ ደንበኞች ብድርን እስካሁን አልሰጠም።

የባንኩ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ተሾመ አለማየሁ አዲሱን መመሪያ ተጠቅመው አዳዲስ ባለሀብቶች እየተስተናገዱ እንዳልሆነም ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ባንኩ ለሰፋፊ እርሻዎች ብድርን ለመውሰድ ያስቀመጠው የ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የካፒታል ጣርያ አበረታች ባለመሆኑ ነው አዲስ ደንበኞችን ማስተናገድ ያልቻለው በሚል በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ሰዎች ትችት ይነሳበታል።

ባንኩ ይህን ማድረግ ያስፈለገው ዘርፉ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ በማሰብ መሆኑን የሚናገሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፥ የ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ጣርያውን ማሟላት ለማይችሉ ደንበኞች ባንኩ በሊዝ ፋይናንስ ብቻ ብድር ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን ነው ያስታወቁት።

Related stories   WAR, JUSTIFIABLE WAR? "ጦርነት ለሃገር ህልውና" by Dr. Haymanot

አዲሱ መመሪያም ከዚህ ቀደም በዘርፉ ላይ የታዩ ችግሮችን በከፍተኛ ደረጃ ለማቃለል ያሰበ በመሆኑ የካፒታል ጣርያው የበዛባቸው ባለሀብቶች በሊዝ ፋይናንስ ሊስተናገዱ እንደሚችሉ የልማት ባንኩ ጠቁሟል።

ደንበኞች ባንኩ በፕሮጀክት ፋይናንስ የግብርና ኢንቨስትመንት ብድርን ለማቅረብ ከባለሀብቱ የ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር መዋጮን እና ይህንን ለአንድ አመት በባንክ መንቀሳቀሱን የሚያሳይ ሰነድን መፈለጉ ባለሀብቱን እንዳይበረታታ አድርጎታል ይላሉ።

Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

የልማት ባንኩ በበኩሉ የካፒታል ጣርያን ማስቀመጥ የፈለኩት የባለሀብቶችን ብቃት ለማረጋገጥ እንዲረዳኝና ከዚህ ቀደም በዘርፉ ላይ ያጋጠመ ችግር እንዳይደገም ነው ይላል ።

የጋምቤላ ኢንቨስተሮች ማህበር ሰብሳቢ እና የየማነ ኤንድ በላይ አግሮ ኢንድስትሪ ስራ አስኪያጅ አቶ የማነ ሰይፉ፥ ባንኩ መሳርያዎችን ያቅርብ እንጂ ለሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት በዋናነት የሚያስፈልገው የስራ ማስኬጃ ገንዘብ በሊዝ ፋይናንስ ስርዓት የማይስተናገድ በመሆኑ ለአዳዲስ ባለሀብቶች አማራጭ ሊሆን አይችልም ባይ ናቸው።
በዚህም ከአዳዲስ አልሚዎች ይልቅ ለነባሮቹ የተሻለ አማራጭ ይዞ የመጣ ነው ተብሏል።

Related stories   Speaking Truth to Power, Samantha: Stop Defending Ethiopia’s “Proud Boys”!

ካለፈዉ ልምድ የእርሻ ስራ ጥናቃቄን የሚፈልግ መሆኑን ተመልክተናል ያሉት ምክትል ፕሬዘዳንቱ፥ የባንኩን ህልዉና ለማስጠበቅ ሲባል የብድር አለቃቁ እና አሰራሩ በተገቢዉ መንገድ የተጠና እንዲሆን እያደረግን ነዉ ብለዋል።

ለሰፋፊ እርሻዎች ከዚህ ቀደም በዋናነት ብድርን ሲያቀርብ የነበረው የኢትዮጰያ ልማት ባንክ፥ በተለይ በጋምቤላ ክልል በነበረው ሰፊ ችግር ምክንያት ብድሩ ከ2008 እስከ 2009 ዓ.ም ባለው አንድ አመት ውስጥ ብድር መስጠት ማቆሙ ይታወሳል።

በተመስገን እንዳለ ፋና ብሮድካስቲንግ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *