ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነት ስፍራን ተረክባለች።የፀጥታው ምክር ቤት ቤት አባል ሀገራት አምባሳደሮች በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት በወሩ ፕሮግራም ላይ ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትነት ዙሪያ ተነጋግረዋል።

 

ethiopia_at_un.jpg

ethiopia_at_un_2.jpg

ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንትነትዋ ወቅት የተባበሩት መንግስታት ድረጅት ከአፍሪካ ህብረት ጋር ሠላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ያለውን አጋርነት ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ የምትሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

በዚህ መሠረት የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጋራ ስብሰባ ጰጉሜ 2 እና 3 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል።

ኢትዮጵያ እንደ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንትነትዋ ስብሰባውን ከአፍሪካ ህብረት ጋር በምክትልነት ትመራዋለች።

ከተባበሩት መንግስታት ድርጀት እና አፍሪካ ህብረት አጋርነት በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊያ የሠላም ሁኔታ እና በቻድ ሃይቅ አከባቢ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በወሩ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠቃል።

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ የተለያዩ አገራት መሪዎች የሚሰተፉበት እና በተባበሩት መንግስታት ድረጅት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የሚመክር ስብሳበ በኢትዮጵያ የፕሬዚዳንትነት ጊዜ በኒውዮርክ እንደሚካሄድም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *