የአዲስ ዓመት አቀባበል አካል የሆነው ‘’የአንድነት ቀን’’ እየተከበረ ነው

ከነገ ወዲያ የሚከበረው የ2010 ዓ.ም አዲስ ዓመት አቀባበል አካል የሆነው ‘’የአንድነት ቀን’’ ዛሬ በመከበር ላይ መሆኑንን፣ ዕለቱም ‘’ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ’’ በሚል መሪ ቃል የሚመራ መሆኑንን የኢህአዴግ ሚዲያዎች እያስታወቁ ነው። ባልተለመደ ሁኔታ ” አንድነት” የሚል ሃሳብ ማቀንቀን የጀመረው ኢህአዴግ በዚህ ሃሳቡ የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

ብሄራቸውን ሲጠየቁ ” ከየትኛው ወገን እንደሆን መናገር ይቸግረናል። የተቀላቀልን ነን። ከተለያየ ብሄረሰብ አባትና እናት ነው የተወለድነው። ኢትዮጵያዊ ነን ” ለሚሉ ” በአየር ላይ ያለ ኢትዮጵያዊነት” በሚል ሲገስጻቸውና ሲያሸማቅቃቸው የነበረው ኢህአዴግ፣ ዛሬ ስለ ኢትዮጵያዊነት ማውራቱና ስለ አንድነት መስበኩ ብዙም የሚዋጥ እንዳለሆነ በተቃራኒው እየተገለጸ ነው።

Related stories   ጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል – በትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪ ሆነው ተሾሙ

አቀንቃኝ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሰለ ኢትዮጵያ መዝፈኑ ዋጋ እያስከፈለው መሆኑ፣ ስለ አገሩ ስጋት ገብቶት ሁሉም ዜጎች ወደ ልባቸው እንዲመለሱ የሚጋብዝ የፍቅርና የአንድነት ስራዎቹን ወደ መድረክ ሲያመጣ ሊመሰገንና ድጋፍ ሊሰጠው ሲገባ በተቃራኒው የግል መብቱን ሳይቀር እያጣ ነው። ይህንን የሚያነሱ ወገኖች ኢህአዴግ ከልቡ ሰለ አንድነት ቢያስብና ቢጨነቅ ኖሮ መጀመሪያ ቴዲን መድረክ ባልከለከለ ነበር ይላሉ። እናም የአሁኑ የአንድነት ሰብከት ” የለበጣ ነው” ልክ ሲያቃጥል በማንኪያ እንደሚሉት ሲሉ ይተቻሉ።

Related stories   የባይደን አስተዳደር ፖሊሲ አምስተኛው ምሰሶ የኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን ቡድን መወሰንና የ 2021 ምርጫን ማዋደቅ (1ኛ ክፍል 2)

ሌሎች ወገኖች ደግሞ ይህንን ቢመሽም ከልብ ከሆነ ጅማሮው ሊመሰገን እንደሚገባና በበጎ ጎኑ መታየት እንዳለበት ያምናሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት፤ ኢህአዴግ የጎሳ ፖለቲካ አደጋ አሳስቦት ወደ እንዲህ ያለው ሃሳብ መመለሱን ከውድቀቱ ጋር በማመሳከር የእርቅ ሃሳብን አጠንክሮ በማራመድ ከሕዝብ ይሁንታና ድጋፍ ለማግኘት መትጋት እንዳለበት ያሳስባሉ። አለያ ግን ከንቱ ውዳሴ እንደሚሆን ያምናሉ። እንዚህ ወገኖች ኢህአዴግ እገሌ ከገሌ ሳይል በአዲሱ ዓመት በሩን ለሰላምና ለፍትሃዊ እርቅ ክፍት ሊያደርግ እንደሚገባውም ያምናሉ።

ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውን፣ ሰራተኞች የሥራ ቦታቸውን በማጽዳት እና የአቅመ ደካሞችን በመጎብኘትና ቤታቸውን በመጠገን እንደሚከበር የዛሬው በዓል እንደሚከናወን ሚዲያዎች አስታውቀዋል። ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በመነሳት ከእምነት ተቋማት መሪዎች ጋር በመሆን በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሚተዳደሩ ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችም እንደሚጎበኙም ተመልክቷል።

Related stories   ም.ጠ.ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ

ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎችን እስር ቤት አጉሮ፣ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ለምን ተቃወማቹህ በሚል እስር ቤት ከርችሞ ” የፍቅር ሰላምታ፣ የአንድነት ወግ፣ አዲስ ዓመት ” ማለት ብዙም እንደማያስኬድ የሚገልጹ ወገኖች ” አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ብቸኛው አማራጭ እቅር ብቻ ነው፤ ፍትህ ያለበት እርቅ!!”

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *