Related image

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሶስተኛ የስራ ዘመን ዛሬ በንግግር ከፍተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ያለፈውን 2009 በጀት ዓመት የመንግስት አፈፃፀምን አቅርበዋል።

የ2009 ዓ.ም አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት 10 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን ገልጸዋል።

ይህ ውጤትም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጠንካራ ሁኔታ ማገገሙን የሚያመላከት እና በዓመቱ ይገኛል ተብሎ ከተተነበየው 11 ነጥብ 1 በመቶ ጋር በጣም የተቀራረበ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ ለ2009 የኢኮኖሚ እድገት ግብርና 36 ነጥብ 3 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 25 ነጥብ 6 በመቶ ከዚህም ውስጥ የማምረቻው ኢንዱስትሪ የ6 ነጥብ 4 በመቶ እና የአገልግሎት ዘርፍ የ39 ነጥብ 3 ድርሻ አንደነበራቸው አብራርተዋል።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ፥ በ2010 በጀት ዓመት ፈጣንነና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገት አንዲኖር የ11 ነጥብ 1 በመቶ ዓመታዊ አማካይ እንደግ እንዲሆን ይደረጋልም ብለዋል።

በዚህም ከግብርናው ዘርፍ ቢያንስ የ8 ነጥብ 0 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከጥቃቅንና አነስተኛ መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች 22 ነጥብ 6 በመቶ፣ ከትላልቅ ኢንዱስትሪዎች 21 ነጥብ 6 እንዲሁም ከግንባታው እንዱስትሪ 23 በመቶ እድገት ይጠበቃል ብለዋል።

የአገልግሎት ዘርፍም የ11 ነጥብ 0 እንደት እንዲያስመዘግብ ይጠበቃል ነው ያሉት።

የዋጋ ግሽበትን በተመለከተም በ2009 ዓ.ም የ12 ወራት ተንክባላይ አማካይ የዋጋ ግሽበት በተያዘው እቅድ መሰረት በነጠላ አሃዝ መገደብ መቻሉን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱም 7 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል።

ጠቅላላ ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት 7 ነጥብ 4 ሆኖ ሲመዘገብ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ደግሞ 7 ነጥብ 1 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

በ2009 ዓ.ም ከታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ ከታቀደው 94 ነጥብ 3 በመቶውን ማሳካት መቻሉን ፕሬዚዳንት ሙላቱ ገልፀዋል።

በ2010 ዓ.ም የተጀመረውን የታክስ ማሻሻ በተለይም በትላልቆቹ የታክስ ከፋዮች ላይ በማተኮር መሰራት እንዳለበት የሚያመላክት ነው ሲሉም ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተናግረዋል።

የውጭ ንግድን በመተለከተም የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲን ከማስፈን አኳያ በ2009 ዓ.ም ከሞላ ጎደል የተረጋጋ የነበረ ነው፤ በ2010 የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ በጥናት ላይ የተመሰረተ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉም አብራርተዋል።

ቁጠባ ከጠቅላላ የአገሪቱ ምርት 29 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው የማድረግ ስራ ይሰራልም ብለዋል።

ግብርናን በመተለከተም በ2010 ዓ.ም የቁም እንስሳት የወጪ ንግድን ጨምሮ በአጠቃላይ ከዘርፉ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት መታቀዱን አስታውቀዋል።

እንዲሁም ከአበባ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ከ220 ሚሊዮጨየን የአሜሪካ ዶላር ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር ማሳደግ ታቅዷል ብለዋል።

መሰረተ ልማቶች

  • በ2010 የገጠር መንገድ ተደራሽነትን ከ75 በመቶ ወደ 85 በመቶ ማሳገድ።
  • የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን መጨረስ እና አዳደስ መጀመር እንዲሁም የፌደራል እና የክልል መንገዶችን የመለየት ስራ።
  • በ2010 የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመርን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ማስገባት
  • ግንባታቸው የተጀመሩ የባቡር መስመሮችን ማስቀጠል
  • በ2010 የአዳዲስ የባቡር ግንባታዎች የሚጀመርበት ሁኔታ እንደሌለም ፕሬዚዳንት ሙላቱ ገልፀዋል

ኤሌክትሪክን በተመለከተም በ2010 ዓ.ም 60 በመቶ የደረሰውን የህዳሴ ግድብ ግንባታን ማፋጠን።

ጊቤ 3 በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ ማድረግ፣ የገናሌ 3 ግድብ ግንባታ አጠናቆ መደ ስራ እንዲገባ ማድረግ፣ የረጲ ባዮ ማስ እና የአይሻ ንፋስ ሀይል በእቅዳቸው መሰረት ተሰርተው ወድ ስራ እንዲገቡ ማድረግ።

የግሉ ዘርፍ በሀይል ማመንጫ ዘርፍ እንዲሳተፍ በትኩረት እንደሚሰራም ፕሬዚዳንት ሙላቱ አብራርተዋል።

በትምህርት ጥራት ዙሪያም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በጤናው ዘርፍም በ2010 ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ህብረተሰቡን ማሳተፈ መልኩ የመከላከል ስራ ይሰራል።

ጥራቱን የጠበቀ የሆስፒታል አገልግሎት፣ የመድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት አሰጣጥም ማሻሻል እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በጤናው ዘርፍ የሚኖራቸውን ሚና ማሳገድ ስራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

fana 

በተጨማሪም የሚከተለውን ብለዋል

መንግስት የጀመረውን የተሃድሶ ንቅናቄና የጸረ ሙስና ዘመቻ በማስፋት እንደሚያስቀጥል የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ አመት የስራ ዘመንን ዛሬ በንግግር ከፍተዋል።

በንግግራቸውም ከሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ከጥልቅ ተሃድሶ፣ ስለምርጫ ህጉ ማሻሻያ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች ስለተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም የወጣቶች ፈንድና ስለ ሴቶች ተጠቃሚነት አንስተዋል።

በመክፈቻ ንግግራቸው አመቱ የማስፈጸም አቅምን በማጎልበት የህዝቡን ተሳታፊነትና ባለቤትነት መንፈስ በማጎልበት ልማታዊነትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ጥረት የሚደረግበት መሆኑን ነው ያነሱት።

ያለአግባብ የመጠቀምና የሙስና ዝንባሌና ተግባርን ለመቆጣጠር የተጀመረውን ንቅናቄ በስፋትና በጥራት ማስኬድም የመንግስት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል።

ከፀረ ሙስና ጋር በተያያዘ የተጀመረው ዘመቻም ተጠናክሮ ይቀጥላል የሉት ፕሬዚዳንቱ፥ የሙስና ምንጭን ለማድረቅና ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የተጀመሩ የአሰራር ማሻሻያዎች እንደሚተገበሩም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለሙስና ተጋላጭ የሆኑት የግብር አስተዳደር፣ የመንግስት ግዥ እና የግንባታ ኮንትራት አስተዳደር፣ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ተቋማትም የአሰራር ማሻሻያው ይተገበርባቸዋል ተብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በሙስና ተግባር ላይ የተሰማሩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ተባባሪዎቻቸውን በህግ እንዲጠየቁ የማድረጉ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ የሚረዱ የህዝብ ምክር ቤቶች ህዝቡን ወክለው አስፈጻሚውን አካል የሚቆጣጠሩበት ሁኔታም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ልማትን በመደገፍ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ዴሞክራሲን ማጠናከር የሚያስችሉ አዋጆች እና ፖሊሲዎችን ያፀድቃል ተብሏል።

የምርጫ ህግ ማሻሻልን በተመለከተም የዛሬ አመት ቃል የተገባለት የምርጫ ህግ ማሻሻያ በዚህ አመት ሊተገበር እንደሚችል አንስተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ማሻሻያው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በ2012 ለሚደረገው አጠቃላይ ምርጫ እንዲደርስ የሚደረግ ይሆናልም ነው ያሉት በንግግራቸው።

በኢህአዴግ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የተጀመረው ውይይትና ድርድር በተቀመጠው መርሃ ግብር መሰረት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፥ የድርድር በሩ ዛሬም ክፍት ነው ብለዋል።

በዚህ ዓመት የሚካሄደው የአካባቢ እና ማሟያ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

በወቅታዊ ጉዳይ ንግግራቸው በመስከረም ወር መጀመሪያ በኦሮሚያ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተወሰኑ ስፍራዎች የተከሰተውን ግጭት ጠቅሰዋል።

የተከሰተው ሁኔታ መወገዝ ይገባዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ መንግስት ግጭት የተከሰተባቸውን አካባቢዎች ከማረጋጋት ባሻገር አጥፊዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ አስረድተዋል።

የሁለቱም ክልል የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ህዝቦች፣ ወጣቶችና ሴቶች ሁኔታው ወደ ነበረበት እንዲመለስ ከመንግስት ጎንብ እንዲቆሙም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የወጣቶች ስራ ፈጠራ እና ተዘዋዋሪ ፈንድ አጠቃቀምን በዳሰሰው ንግግራቸው፥ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

የታየው አፈጻጸምም ከፌደራልና ከክልል መንግስታት ከተገኘው ገንዘብ ጋር በሚመጣጠን መልኩ የሄደ አለመሆኑም ተጠቅሷል።

ከሴቶች ተሳትፎ ጋር በተያያዘም በገጠር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሴቶች በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሴቶች ተጠቃሚነት በጤናው ዘርፍ ለውጦች እንዲታዩ ማስቻሉንም በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

የሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ኢትዮጵያ በአለም መድረክ የተወደሰችበትን የአረንጓዴ ልማት አጠናክሮ ማስቀጠል፥ የበጀት አመቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ሆነዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ የራሷን እና የሌሎች ታዳጊ ሀገራትን መብትና ጥቅም የሚያስከብሩ ስራዎችን መተግበር መቻልም የአመቱ ቀዳሚ ተግባራት ይሆናሉ።

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *