የአምባሰሏ ንግስት ማሪቱ ለገሰ በጠና ታማ ሆስፒታል ተኝታለች። ህመሟ የሃሞት ጠጠር ሲሆን – በሌዘር ህክምና በሽታውን ለማስወገድ ህክምና እየተደረገላት ይገኛል። የማሪቱ ህይወት “እጅግ አሳዛኝ” የሚል ቃል አይገልፀውም!! 12 ልጆች ወልዳ 11 ልጆቿን በሞት ተነጥቃለች። በህይወት የቀረላት አንድ ልጅ ነው። አሜሪካ ከመጣች 20 አመት ቢሆናትም ወረቀት (መኖሪያ ፈቃድ) የላትም። ግሪን ካርድ ስለሌላት አገር ቤት መሄድና ልጆቿን አፈር ማልበስ አልቻለችም። ጉዳይዋን የያዘ አንድ ሀበሻ ጠበቃ ከዝች ምስኪን ባለፉት አመታት 17 ሺህ ዶላር ወስዶ ምንም አልፈየደላትም። በየግዜው 500 እና 600 ዶላር ይወስዳል። ምንም ለወጥ የለም። ማንም ሰው መጥቶ አመት ባልሞላ ጊዜ መኖሪያ ወረቀት እየጨረሰ እያየን…የዝች ክብርት እህታችን ጉዳይ 20 አመት እንዲህ መሆኑ ያሳዝናል!! የስራ ፈቃድ ያገኘችው በቅርብ ነው።

በዚህ እድሜዋ ተሯሩጣ ስራ መስራት የማይታሰብ ነው። በማንኛውም ዝግጅት ስትጠራ በፈቃደኝነት በነፃ ትሰራለች። የእሷን ጉዳይ ግን ዞር ብሎ የሚያይላት የለም!!..የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ለሁለት ተከፈለና በሼኹ የሚመራው ቡድን ማሪቱ ዘንድ ሄዶ እንድትዘፍን ሲጠይቃትና ቼክ ይዘው ሲሄዱ የመለስችው “ከህዝቤ ጋር ነኝ! ..ገንዘቡ ይቅርብኝ! አልሰራም!” ነበር ያለችው። በሳምንት አንድ ቀን ዘፈን ሰርታ 150 ዶላር ከሚከፍላት “ሉሲ” ሬስቶራንት በቀር ከኮሚኒትው አንድም ከእሷ ጎን የቆመ የለም! አሜሪካ – ጁሽ የሆነች ለማሪቱ ቤትና የተወሰነ ነፃ ህክምና እንድታገኝ ስታደርግ ኮሚኒቲው ምንም አላደረገም። ማሪቱ ለመጨረሻ ጊዜ አልበም ብትሰራም ስፖንሰር በማጣት ይዛው ለመቀመጥ ተገዳለች።…የአንባሰሏ ንግስት ማሪቱ ለገሰ የውስጥ ብሶትና መከራ በሆዷ እንደታመቀ ነው!ከጎኗ ያልተለይዋት አርቲስት ፀሀይ ካሳ፣ የክራር አቀንቃኝ መልካም ሰው ፋንታሁን መለሰና አርቲስት አልማዝ ናቸው። በዲሲና አካባቢው የምትኖሩ ድምፃዊ ማርቱ ለገሰን መጠየቅ ከፈለጋችሁ አድራሻው ይህ ነው፤

Sibley Memorial Hospital
5255 Loughboro Rd NW, Washington DC, 20016
7th floor Room number 740

@አርአያ ተስፋማሪያም

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *