የፌደራል መንግስት የሚባለው አካል ዝምታን መርጦ ጣናን አረም ሲያጠፋው የኦሮሚያ ክልል ያሳየው የድጋፍ ተነሳሽነት እጅግ ሊደነቅ ይገባል። ጣና ኢትዮጵያዊነት መሆኑኑን፣ መለያችን መሆኑንን፣ ተቀብሎ ድጋፍ ለማድረገ መነሳት ብቻ በራሱ ከበቂ በላይ ነው። አሁን በዚህ ዘመን!!
Addisu Arega Kitessa Bureau Head at Oromia Government Communication Affairs Bureau

ጣና የአባይ መነሻ ነዉ። አባይ የኢትዮጵያ አንድነት ተምሳሌት ነዉ። ጣና የአባይ ምንጭ ነው ጉደር፥ አንገር፥ ዲዴሳ፥ ዳቡስ፥ በለስ፥ ዠማ እና የመሳስሉት ወንዞች ከኦሮሚያ፥ አማራ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በመነሳት ውደ አባይ በመፍሰስ አንድ እጅግ ሀያል የሆነ፥ በዓለም ረዥሙን ወንዝ ይፈጥራሉ። አባይን! የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ በደም ጋብቻ እንደተሳስሩ ሁሉ! ኦሮሞና ጉምዝ ኦሮሞ እና ትግሬ፥ ጉራጌ ውዘተ በደም በጋብቻ በአንድነት እንደትሳስሩት ሁሉ! ልክ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት ቆመዉ ኢትዮጵያን እንደመስርቱ ሁሉ…

ዛሬ ጣና ችግር ላይ ነዉ። እምቦጭ ወሮታል። ጣና ከሌለ የአንድነታችን ምሳሌ የሆነው ታላቁ ወንዛችን አባይ ሊኖር አይችልም። የሀገራችን አንድነት እና የጥንካሬያችን ተምሳሌት የሆነዉ ታላቁ ወንዛችን አባይ እንዳይጠፋ ትናንት ሀገራችን ስትወረር በአንድነንት እንደቆምን ሁሉ ዛሬም በችግር ጊዜ በአንድነት መቆም ግድ ይለናል። በመሆኑም ክ200 በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች “Xaanaan Keenya! ጣና የኛ ነዉ” እያሉ ጣናን ለመታደግ እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ላይ ለመሳተፍ ወደ ባህር ዳር ጉዞ ጀምረዋል

ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን በችግር ጊዜ አብሮ መቆም፥ መረዳዳት እና መደጋገፍ ነዉ!

ፎቶ – ልሳነ አማራ 

በተመሳሳይ የኦሮሞ ወጣቶች የአማራ ውጣቶችን ሰልፍ እንዲወጡ ለመቀስቀስ ወደ ጣና እንዳመሩ ተደርጎ እየትናፈሰ ነው። ልሳነ አማራ ይህንን በፎቶ የተደገፈ መረጃ

Image may contain: 1 person, text

 በጣም የሚያሳዝነዉ ——– ሰዎች የኦሮሞ ልጆች ወደ ጣና የሄዱት የአማራ ልጆች አብረዉ ሰልፍ እንዲወጡና እንዲያምጹ ለማባበል ነዉ እያሉ ይገኛሉ፡፡ እኛ እኮ ብለናል እኒህ ሰዎች ለኢትዮጵያ አይሆኑም ብለናል፡፡ ጣናን የአማራ ወይም የጠላት ንብረት አድርገዉ እንደሚያዩት ከዚህ በላይ ማሳያ የለም፡፡ ያሳዝናል

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *