ለኢህአዴግ ሸምቀቆ የተባለው ኤች አር 128 መራዘሙ የድል ያህል ሆኖ የኢህአዴግን ደጋፊዎች አስደስቷል። በሌላ በኩል መራዘሙ በቅድመ ሁኔታ የተከናወነ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። ከሁሉም በላይ ግን የኢህአዴግ ወዳጅ የሆኑት ሴናተር አዲስ አበባ መክረማቸው፣ እንዲሁም ሶማሌ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ ከአሜሪካ ጋር አልሸባብን ለመደምሰስና ሶማሊያን ሰላማዊ አገር ለማድረግ ስምምነት ተደረሰ መባሉን በማጉላት  ህጉ የከሸፈ እንደሆነ ተደርጎ እንዲገመት ውትወታው ብዙ ነው።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

አሁን በኢትዮጵያ ጉሮሮ አንቆ የያዘው የህዝብ አመጽ ነው። በሎቢ ወይም ጀንጃኞች የማይቀለበስ፣ ከፍተኛ ምሬትና ተቃውሞ ያለበት፣ ከዚሁ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የሚወሰዱ የአመጽ መገለጫዎች መካረራቸው፣ አመጹን ለማስቆም እየተወሰዱ ናቸው የተባሉና የሚባሉ ረብ የለሽ እርምጃዎች… ተዳምረው ከ26 ዓመት በፊት በህግ ጸድቆ መተዳደሪያ የሆነው የጎሳ ፖለቲካ ነገሮችን ወደ መጨረሻ እየገፋቸው ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ሁሉም ወገኖች በሁሉም አቅጣጫ ለመፍትሄ በሚያጋንጥጡበት ወቅት የተሰማው ይህ ህግ ትልቅ ግምት እንዲያገኝ አድርጎታል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች መንግሥት እንዲመሠረት የሚጠይቀው የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ረቂቅ ባለፈው መስከረም 18/2010 ዓ.ም. ድምፅ ሊሰጥበት የተወሰነ ቢሆንም፣ መስከረም 22 የሕጉ ረቂቅ በምክር ቤቱ ለውሳኔ ከተያዙ አጀንዳዎች ላይ አንዲነሳ መደረጉ ታላቅ ዜና የሆነውም በዚሁ መነሻ ነበር። ስጋት የያዛቸው መራዘሙ ድል ስለመሆኑ  ጮቤ የሚያስረግጥ ዜና ሲያቀርቡ፣ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ” ታገሱ” ብለዋል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

ኤችአር – 128 ድምፅ ሳይሰጥነት ለ30 ቀናት መተላለፉን ያረጋገጡልን የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ምንጮች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እራሱ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ጊዜ እንዲሰጠው በመጠየቁ፣ የምክር ቤት አባላትም ለዚህ ዕድል ለመስጠት ፈልገው እንደሆነ የዘገበው የአሜሪካን ሬዲዮ ነው። የትዝታ በላቸው ጥንቅር በየአቅጣጫው በስሜት ለሚዘሉት ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ነው

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *