ዛሬ በተካሄደው የኢህአዴግ ፓርላማ ስብሰባ አቶ አይለማሪያም ደሳለኝ አባሎች ላቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ የአቶ አባ ዱላና አቶ በረከትን መልቀቂያ አስመልክቶ የሚከተለውን ብለዋል።

መልቀቂያ ያስገቡ የስራ ሀላፊዎች

በቅርቡ በፈቃዳቸው ከስራ ሀላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡ የስራ ሀላፊዎች ጉዳይም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተነስቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው በአንድ የዴሞክራሲ መርህን በሚከተል ድርጅትም ሆነ መንግስት ውስጥ ይህ ሊሆን የሚችል እና ሊለመድ የሚገባው መሆኑን አንስተዋል።

ሁለቱ አመራሮች ማለትም አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ እና አቶ በረከት ስምዖን ከለጋ እድሜያቸው ጀምር በአገሪቱ አሁን ለመጣው ለውጥ የታገሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። የሁለቱም ጥያቄዎች በተቀራረበ ጊዜ የቀረቡ በመሆናቸው የተመሳሰሉ ቢመስሉም አይደሉም ብለዋል።

አቶ አባዱላ ገመዳ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ በጥያቄያቸው ላይ የተለያዩ ውይይቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

አቶ አባዱላ በጎ ፈቃዳቸው ሆኖ በሃላፊነታቸው ቢቀጥሉ የመንግስት ፍላጎት መሆኑን ያነሱት አቶ ሀይለማርያም፥ በጥያቄያቸው እስከገፉ ድረስ ግን ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል ነው ያሉት።

አቶ በረከት ስምዖንን በተመለከተም አመረራሩ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ከሃላፊነታቸው ለመነሳት ጥያቄ አቅርበው በድርጅቱ ባህል መሰረት ውይይት ተደርጎ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውሰዋል።

አሁን ላይ ከሃላፊነቴ መልቀቅ አለብኝ በማለታቸው ከመንግስት ስራ ቢወጡም ትግላቸውን አያቆሙም በሚል እምነት ከላቀ ምስጋና ጋር ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቀዋል።

ድርጅት እና መንግስት በየጊዜው አመራር እየወጣ እየገባ የሚያስኬዷቸው እንደመሆኑ ሁለቱም በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚመሩ እንደመሆናቸው የሚያስፈራ አይደለም ብለዋል። እንዲህ ዓይነቱ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ሊለመድ እንደሚገባውም ነው ያመለከቱት። ፋና እንዳለው

Related stories   የመተከል ዞን ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት በኮማንድ ፖስት ስር ይቆያል -የክልሉ መንግስት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *