በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ካሉት አንዱ የፓውዛ መብራት መሶሶ ላይ በመውጣት የኢትዮጵያን የቀድሞ ባንዲራ ሲያውለበልብ ነበር የተባለ ወጣት መያዙን ማህበራዊ ሚዲያዎች በምስል አስደግፈው ይፋ አድርገዋል። በምስሉ ላይ እንደታየው ወጣቱ ፖሊስ ሲይዘው የአገሩን ባንዲራ ለብሶ ይታያል።
ፖሊስና እሳት አደጋ መከላከያ በመተባበር በከፍታ መወጣጫ ማሽን ተጠቅመው ወጣቱን ሊያወረዱት ሲረባረቡ ምስሉ ያሳያል። ይህንኑ ዜና በፎቶ ይፋ ያደረጉት ክፍሎች እንዳሉት ፖሊስ ልጁን ካወረደ በሁዋላ ወደ እስር ቤት ወስዶታል። ቀደም ባሉት ዓመታት / በደርግ ጊዜ በአራቱም አቅጣጫ የቆሙት ምሶሶዎች ላይ በመንጠላጠል ኳስ ማየት የተለመደ ነበር።
በውቅቱ የነበረው ፉክክር ውጪ ለሚቀመጡ እና የመግቢያ ሳንቲም ለሌላቸው ወገኖች እጅግ ስሜት ቀስቃሽ ስለነበር ውስጥ ያሉ ሰዎች ውጪ ካሉት ጋር በአየር ላይ ገንዝበ ተነጋግረው መሶሶው ላይ ይወጣሉ። ከዛም ስታዲየሙ ብረት ጋር ሲደርሱ እጃቸውን ይዘረጉና ከውስጥ ካለው ሰው ጋር ያገናኛሉ። እውስጥ ያለው ሰው ትንፋሽ ስቦ 1,2,3 ይልና መሶሶው ላይ ያለው ሲፈናጠር ይስበውና ያስገባዋል። ከዛም በድርድሩ መሰረት ከፍሎ ኳስ ያያል። ድሮ እንዲህ ነበር። ምሶሶው ጫፍ ላይ ፖሊስ ሸሽተው የሚወጡት ደግሞ ብዙም የሚጨክንባቸው ስለሌለ ኳስ ሲያልቅ ፖሊስ ወደ ቤቱ ሲሄድ እነሱም ወርደው ወደ ቤታቸው ያመራሉ። ይህን ለስታዲየም ሰፈር ትዝታ የጨመርነው ነው። አሁን ተያዘ የተባለው ልጅ ሆን ብሎ ባንዲራ ለማውለብለብ ይውጣ ኳስ ለማየት ብቻ የታወቀ ነገር የለም። ፖሊስም የልጁን የኳስ ስሜትና የሚነገረውን የዜና ገበያ በመለየት ውሳኔውን እንዲያላላ …