በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የከተማ መስተዳድር ከንቲባዎች፣ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሃይሎች እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር እንደተወያዩ ተዘግቧል። ውይይቱን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሩና የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሃላፊ ናቸው የሚባሉት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ሲሆኑ ለቀጣይ አንድ አመት ሀገሪቷ የምትመራበት ወጥ የሰላም እና ፀጥታ እቅድ እንደወጣና በእቅዱ ላይም ውይይት ተደርጎ ስምምነት እንደተደረሰ ገልጸዋል።
አቶ ሲራጅ በአገሪቷ የሚነሱ ተቃዉሞዎችን ከዚህ በኋላ የፌዴራል መንግስቱ ጸጥ እንደሚያሰኝ ነው የገለጹት።
ከአቶ ሲራጅ መግለጫ ለመረዳት እንደሚቻለሁ፡
1) ከዚህ በኋላ የክልል መንግስታት ጸጥታን በማስከበር አንጻር ማገዝ እንጂ ምንም ስልጣን እንደሌላቸው ነው። አገሪቷ በተዘዋዋሪ መንገድ በወታደራዊ እዝ ውስጥ እንደወደቀች ነው።
2) የአስቸኳይ ጊዘ አዋጁ በጓሮ በር ተመልሶ እንደመጣ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ ሊሉ አልፈለጉም። ለምን ባለፈው የደነገጉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለመስራቱን ማመን ስለሚሆንባቸው። ከዚህም የተነሳ በተለየ መልክ “ልዩ እቅድ” በሚል አዋጁን ለመደንገግ እየተዘጋጁ ነው።
በሰብሰባው አቶ ለማ መገርሳ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የክልሉ አስተዳዳሪዎች ከፊት ተቀምጠው ከመድረኩ የሚነገረዉን ሲያዳምጡ ተስተዉለዋል።
በአቶ ሃይለማሪያም ጽ/ቤት ስለተደረገውና አቶ ሲራጅ ስለገለጹት ልዩ እቅድ የክልል መንግስታት ምንም አይነት አስተያየት እስከአሁን አልሰጡበትም።
በተለይ በአማራው ክልልና በኦሮሚያ፣ የክልሉ መንግስታት ከፌዴራል መንግስት በላቀ መልኩ በአንጻራዊነት በሕዝቡ በተቀባይነት እንዳላቸው ይታወቃል። እንኳን የክልል ሃላፊዎች ወደ ጎን አድርጎ፣ የክልል መንግስታትን ድጋፍ በመያዝ የፌዴራል መንግስቱ አገር የማረጋጋት አቅምና ብቃት እንደሌለው የሚገልጹት የፖለቲካ ተንታኞች የአገር ችግር የሚፈው በጠመንጃ ሳይሆን የሕዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ በማከበር መሆኑን ይናገራሉ። ሆኖም እስከአሁን ከአራት ኪሎና ከመቀሌ ባለስልጣናት የሕዝብን ጥያቄ በማክበር አንጻር መሻሻሎች ለማድረግ ማቀዳቸውን የሚያሳዩ ምንም አይነት ፍንጮች አይታዩም።
በግርማ ካሳ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *