ንግስት ይርጋ ፣ በአቃቢ ሕግ የቀረበበሽ የሽብርተኛ ክስ ተገቢ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ እንድትከላከለ ዛሬ ወስኗል። አቃቤ ሕግ “ንግስት ይርጋ ሽብርተኛ” ናት ብልኦ ሲቀርብ ካቀረባቸው ክሶች መካከል

– በጎንደሩ ሰልፍ የቆሰሉትን ለማሳከም የለበሰችውን ልብስ አውልቃ ከ5ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ማሰባሰቧ
– የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ፎቶ ባነር ማሰራቷ
– የኮለኔል ደመቀ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት በ120 ብር መግዛቷ
– ሰልፉ በሰላም በመጠናቀቁና በወጣቱ ተስፋ ስላለው እትዬ ጣይቱ ብሎ ስለተጠራች

እንግዲህ ምን ያህል በአገራችን የፍትህ ስርዓት እንዳለ በንግስት ላይ ከቀረበው አሳፋሪ. አስቂኝ ክስና ከፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መረዳት እንችላለን።

ፍርድ ቤቱ ይሄን ዉሳኔ የወሰነው ከሕወሃት ደህንነት የፖለቲካ መመሪያ ስለተሰጠው መሆኑን የሚጠራጠር ይኖርል ብዬ አላስብም። ሕወሃቶች ደግሞ ለጎንደር ሕዝብ ትልቅ ንቀትና ጥላቻ ስላላቸው፣ ንግስት ይርጋን ፈቱ ማለት የጎንደርን ህዝብ አስደሰቱ ማለት ስለሆነባቸው ብቻ ነው፣ በበቀል ይችን እህት በወህኒ እንድትቆይና እንድትሰቃይ የሚያደርጉት።

ህዝቡ ይሄን ማወቅ ያለበት መሰለኝ። ” ንግስት ይርጋ የአማራው ክልል ሕዝብን አመላካች ናት“ ብዬ ቀደም ሲል እንደጻፍኩት፣ በንግስት ላይ የተወሰነው ዉሳኔ ፣ በአማራው ክልል ሕዝብ ላይ የተወሰነ ዉሳኔ ነው። ንግስት ይርጋ በጎንደሩ አስደማሚ ሰልፍ ላይ የኮሎኔል ደመቀ ምስል ያለበትን ቲሸርት አድርጋ ነበር። በቲሸርቱ ላይ “ የአማራ ህዝብ አሸባሪ አይደለም” የሚልም ተጽፎ ነበር። ሆኖም ግን እነ ንግስት ይርጋ ፍጹም ሰላማዊ በነበረው በጎንደር ሰልፍ ላይ በመገኘታቸው ብቻ የሽብርተኛ ክስ ተቀባይነት ካገኘ፣ ሕወሃት “የአማራ ህዝብ አሸባሪ ነው” የሚል ዉሳኔ እንዳሳለፈ ነው መወሰድ ያለበት።

“አሸባሪ ነህ” የተባለ ህዝብ ፣ የተናቀ ህዝብ፣ አንገቱን እንዲደፋ የተደረገ ሕዝብ፣ ልጆቹን እያስበላ ያለ ህዝብ፣ በብአዴኖች ድለላና የቂቤ ንግግር እየተታለለ መቀመጥ ያለበት አይመስለኝም።

ሕወሃቶች የክልሉ ህዝብ ላይ በበቀል ነው የተነሱት። ይህ ህዝብ ካልተዳከመ ፣ ካልተመታ በስልጣናችን መቆየት አንችልም የሚል የፖለቲካ ስትራቴጂ ነው ያላቸው።

ግርማ ካሳ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *