ኢህአዴግ አስገራሚና አስደማሚ በሚባል የስኬት ጎዳና ላይ እየተንደረደረ ነው። እመርታው ከእይታ ውጪ በመሆኑ በቃላት ሊገለጽ የሚችል አይደለም። አገሪቱን በማበልጽግ ከአውሮፓ አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በቋፍ ላይ ነው።

ከአፍሪካ አገሮች ጋር ሊፎካከር በማይችል የእድገት ሩጫ ሁሌም ሪኮርድ እያስመዘገበ ነው። ይህንን ሃቅ አገሪቱ ውስጥ ባሉ ሚዲያዎችና ገለልተኛ ጋዜጠኞች ለህዝብ እያሳወቀና እያስተዋወቀ ይገኛል። የሚዲያ ስራ ላይ ያሉትም ይህንን በልበ ሙሉነት እየተናገሩት ነው።

የሕዝቦች ብሶት የወለደው ኢህአዴግ ባለ ራዕዩ፣ አስተዋዩ፣ሃቀኛው፣ ምሁሩ፣ ደጉ፣ ተመራማሪው፣ ነብዩ፣ ምጡቁ መሪው ቢለዩትም በሳቸው መንፈስ በመመራት ሰሞኑንን የደረሰበትን ደረጃ ይፋ አድርጓል። ይህ አስደማሚ ስኬት በጥቂቱ፣ እጅግ በጥቂቱ እንደሚከተለው ቀርቧል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

የፖለቲካ ቀውሱ ወደ ኢኮኖሚ ቀውስ አድጓል!!
1 የውጭ ብድር ለመክፈል ዶላር አጥቼ ተቸግሪያለሁ።በዚህ ምክንያት ተጨማሪ ብድርም ማግኘት አልቻልኩም – ኢትዮቴሌኮም
2 ለጋምቤላ እርሻ የተወሰደው ብድር ማስመለስ ስላልተቻለ ያልተመለሰልኝ የብድር መጠን 9 ቢለዮን ደረሰ – ልማት ባንክ
3 የጨረቃ ጨርቅ ዘርፉ ለውጭ ሚንዛሪ እያበረከተ ያለው ድርሻ እያሽቆለቆለ ነው – በዘርፉ ላይ ጥናት ያሄሃዱ ሙሁራን
4 የሀገሪቷን የእኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ከ700 ቢለየን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል – የብሄራዊ ባንክ ገዥ
5 ስራ ይጀምራሉ ከተባሉት አስር የስኳር ፋብሪካዎች አንዱም ስራ አልጀመረም- የኢህአዴግ መሪዎች
6 የህዳሴው ግድብ ያልቃል በተባለበት ጊዜ ከግማሽ እልፍ ያለው ትንሽ ነው።በተለይ በለፈው ሁለት ዓመት ተሰራ የተባለው በፐርሰንት አንዴ ከፍ ሌላ ጊዜ ዝቅ እያለ … ሪፖርቶች
7 ማዳበሪያ ፋብሪካዎቹን የበላቸው ጅብ አልጮህ ብሏል – ሪፖርቶች
8 ከአስቸኳይ አዋጅ ወደ ደህነት ኮሚቴ ተዛውረናል- ኢህአዴግ

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

ከላይ ያየናቸው ነጥቦች በሙሉ በሀገረቷ የሰፈነው የፖለቲካ ቀውስ እና የአመራር ልሽቀት ወደ ኢኮኖሚ ቀውስ መሸጋገሩን አመላካች ናቸው። የፖለቲካ ቀውሱ የኢኮኖሚን ቀውስ እያጣደፈው ነው። ይህ አስደማሚ እድገት እያመጣ ያለው ጣጣ ሀገሪቷን ወደ አጠቃላይ ቀውስ እንዳያመራት ስጋት ያላቸው አሸባሪዎ፣ ጸረ ልማቶች፣ እያሉ መቀጠል አይቻልም። ይህንን ጣጣ ለመቀልበስ ቆራጥ አመራር የግድ ነው።

ደረጀ ገረፋ ቱሉ

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *