የኦሮሞ ወጣቶች ላበረከቱት በጎ ተግባር በድጋሚ ምስጋና ተቸራቸው። ምስጋናውን ያቀረቡት የአማራ ክልል የድንናዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ምስጋና ሲያቀርቡ ተግባሩን “መቼም የማይረሳ” ብለውታል። አያይዘውም የኦሮሞ ወጣቶች የሰሩት ተግባር የአንድነት መንፈስን የገነባ ሲሉ አድምቀውታል። ጣናን እየበላ ያለው የእንቦጭ ዓረም በሰው ሃይል ለማጽዳት ቢሞከርም አለመቻሉንና 5,396 ሄክታር የሚያክለውን የውሃውን አካል መሸፈኑንን አስታውቀዋል።

ዶክተር በላይነህ አየለ የአካባቢ ደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመስሪያ ቤታቸውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በተለይም ጣናን በመታደግ ረገድ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ሲያስረዱ የችግሩን አሳሳቢነትና እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ተናግረዋል። አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፌስ ቡክ ገጻቸው ይህንን ብለዋል።
ዶክተር በላይነህ በሪፖርታቸው እንቦጭ በጣና ላይ ከተከሰተበት 2004 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በህዝብ ተሣትፎ ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ የተሠራ ቢሆንም እስከ አሁን ማስወገድ እንዳልቻለ አንስተዋል። በአሁኑ ሰዓት በሐይቁን 5,396 ሔክታር ወይም 53 ሺህ ሜትር ካሬ የሀይቁን እና ዳርቻውን አካባቢ እንደሸፈነው እንዳለም አክለው አስቀምጠዋል።

አረሙን ለማስወገድ ከሰው ጉልበት በተጨማሪ በማሽነሪ ለመደገፍና ግስጋሴውን ለመግታት በጎንደር ዪኒቨርስቲና ባህርዳር ከተማ ከሚሞከረው ባለፈ በክልሉ መንግስት በጀት ተመድቦ 11 ቴክኖሎጂ ተጠንተው 4 በመምረጥ ጨረታ ወጥቶ የግዢ ሥራ ተጀምሯል ሲሉ አብራርተዋል።
ዶክተር በላይነህ በሪፖርታቸው ጣናን ለመታደግ የተረባረቡትን ሁሉ አመስግነው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች ጣናን ኬኛ፤አባይ ኬኛ ፤ አማራ ኬኛ ብለው አገር አቋርጠው በጣና ላይ መዝመታቸው ልብ የሚነካ እና መቼም የማይረሳ የአንድነት መንፈስ የፈጠረ ስራ ስለ ሰሩ ለወጣቶቹ እና ለመላው የኦሮሚያ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።
የምክር ቤት አባላት ጣና የሀገር ሀብት በመሆኑ የፌደራል መንግስትን ትኩረት ሊያገኝ ሲገባው በፌደራል መንግስት በኩል ትኩረት የተነፈገው ሰለሆነ የክልሉ መንግስት ግፊት ሊያደርግ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ከዚህም በተጨማሪ “መንግስት ለጣና የሰጠው ትኩረት እና የተፈጠረው ንቅናቄ ሊመሰገን ይገባዋል ። ነገር ግን ተሰራ ተብሎ የሚነገረው እና በተጨባጭ የተሰራው ልዩነት ስላለው በጥንቃቄ ሊመራ ይገባል፤ የክልሉ አመራሮች በአካል ተገኝተው ህዝቡን ማነሳሳታቸው ጥሩ ሆኖ ህዝቡ የሚፈልገው በማሽን አረሙ ተወግዶ ማየት ነው፤ ምክንያቱም ጣና የማንነታችን መገለጫ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *