ኢህዴን የኢህአዴግ ምንጭ???
‘በጫካ ትግሉ ወቅት ትግራይን የመገንጠል አላማችንን ስህተትነት ወዲያው ተረድተን የመገንጠል ጥያቄችንን ተውን’ የሚሉት ህወሃቶች፤ ‘ለትግራይ ብቻ ከመታገል ወደ ህብረብሄራዊነት አድገን ኢህአዴግን መመስረታችን ሌላው እርምት የወሰድንበት አቅጣጫ ነው’ ባዮች ናቸው፡፡ ኢህአዴግን ከመሰረቱ ትቂት አመት በኋላ ግን ህብረ-ብሄራዊውን ኢህዴን ወደ ብአዴንነት እንዲያንስ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡ ህወሃቶች ኢህዴንን ወደ ብአዴን ሲያሳንሱ በስመ ኢህአዴግ የሃገሪቱን ፖለቲካ በእናት ፓርቲያቸው ህወሃት በኩል የመዘወሩን ረቂቅ ፖለቲካዊ እቅድ ታሳቢ አድርገው እንደነበረ ፈዛዛው ኢህዴን ይግባው አይግባው የሚያውቀው ራሱ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ህወሃት እንደዚህ ባለ ጥበብ ህወሃትነቱን ሳይለቅ ኢትዮጵያን ለመዘወር ደግሞ ኢህአዴግ የሚለውን ካባ ሲለብስ ደንጋራው ኢህዴን ወደ ጎሰኝነት ተኮማትሮም “እልፍ ሆኛለሁ” እያለ መዘመሩ አልቀረም፡፡ ሙሉውን አስፈንጣሪውን በመጫን ያንብቡ  ደንጋራው ብአዴን

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *