ወንጀሉ የተፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው ጠማማ ፎቅ አካባቢ ጥቅምት 23 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ነው። የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሸ አማረች መልኬ እድሜው በግምት 4 ወር የሚሆነውን ህጻን ልጇን በጀርባዋ ጭንቅላቱን ወደ መሬት ዘቅዝቃ አዝላ እየተጓዘች ነበር።

በዚህ ጊዜ ድርጊቷን የተመለከተ በአካባቢው የነበረ ሰው ልጁን ተቀብሎ በማቆየት መልሶ ይሰጣታል። ከዚያ በኋላም ተከሳሿ ልጁን ከጎኗ አስቀምጣ የእግረኛ መተላለፊያ መንገድ ላይ ያለበቂ ጥንቃቄ ተኝታ ትገኛለች።

በዚህም በፈጸመችው የልጅ ማሳደግ ግዴታን አለመወጣት ወንጀል ህግን በመተላለፏ ምክንያት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቂርቆስ ምድብ ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባታል፡፡ 

የክሱን ሂደት ምርመራ እና ክትትል ሲያደርግ የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት ተከሳሽ ጥፋተኛ መሆኗን በቀረበው የሰውና ሰነድ ማስረጃ አረጋግጧል፡፡

የፌደራል ዐቃቤ ህግም በበኩሉ፥ በተከሳሿ ላይ የቅጣት ማክበጃ አለመኖሩን በማስረዳት፥ ህፃኑ 4 ወር እድሜው ላይ መገኘቱ ተጋላጭነቱ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ የወንጀል ደረጃው በመካከለኛ ተይዞ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠይቋል፡፡ 

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፊደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም፥ ተከሳሽ በተከሰሰችበት የህግ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ መሆኗን በማስረዳት፥ በቀን ህዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት የ200 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲትቀጣ ወስኗል፡፡

ፋና ብሮድካስት 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *