ባልደረባዬም ሙሊት ነው። ሴትየዋ እንደ ጋሪ ነች። መናገር እንጂ ማሰብ አትችልም። ፋናና ኢቲቪን የምታዳምጥም አትመስልም። ቀባጠረች። ግድያው ላይ እና የስር ቤቱ ሮሮ ላይ ሙግት ገቡ። ቡና ስኒ ተሰበረ። ተዘላለፉ። በብሄር ተኮር ስድብ ተናረቱ። ይህን ጊዜ ያበደው ጥሎ ወደ ሚኖርበት ከተማ አመራ።

ህም አለ ያገሬ ሰው!! የሰው ልጆች በምክንያትም ይሁን ያለምክንያት ይሞታሉ። ሁሉም ቦታ ሁሉም ዓይነት ሞት አለ። ሁሉም አይነት ገዳዮችና አስገዳዮች በሁሉም ቦታ አሉ። ገዳይ፣ አስገዳይ፣ ተገዳይ፣ አጋዳይ፣ ተገዳላይያበደው አመመው። ምራቁ ደነደነበት። ሲቃጠል ምራቁ ይደነድናል። ይህን ጊዜ የሚሰራውን አያውቀውም። ሰላምታም ይዘነጋል።

አይ አንቺ እናት፣ አምጠሽ የወለድሽው ያንሺ ልጅ ሌላዋ አምጣ የተገላገለችውን ይገላል። አንሺ ማሪያም፣ ማሪያም ተዘምሮልሽ የወለድሽው ልጅ፣ ማሪያም ማሪያም ተብሎ በምልጃ የተወለደውን የሌላ እናት ልጅ ያስገድላል። ያበደው ትንግርት ሆነበት። ሁለት እናቶች ገዳይና ተገዳይን አምጠው ወልደው …. ምን አልባትም እኮ አንድ መደብ ላይ የተወለዱ …. ምን ምን አልባት አለው? ልክ እኮ ነው ወንድም ወንድሙን

ያበደው ቤት ፍለጋ ወደ ከተማ ወጣ ብሎ ነበር። ብርድ ነበርና አንዲት ቡና መቸርቸሪያ ቤት ተባልደረባው ጋር ገባ። ከዚያ የማይጠፉ አሉ። ሁሌም ሲያወሩ የሚኖሩ። የሚቀይሩት ልብስ እንጂ ወሬ አይደልም። ሁሌም አንድ አይነት ናቸው። ድግምገሞሽ!! ያበደው ስልቹ ነው። ድግምግሞሽ አይወድም። ሁሌም የሚያማርሩትንም አይቀርብም።

አንዷን አገኛት። ወሬ ጀመሩ። ፊርማዋ ከደረቀ ቆይቷል። የአበሻ ፈረንጅ ሆናለች። ነገ ምን መመሪያ እንደሚወጣ ባይታወቅም ለዛሬው የፈረንጅ ማንነትዜግነት መያዟ ልቧን አጠጥሮታል። አቀማመጧብቻ ወሬ ቀጠልን። አገርቤት ከርማ መመለሷን ተናገረች። ያበደው እንግዳ ስለነበር ዝም ብሎ ይቀዳል።

ያበደው እጅ ነስቶ ይቀዳል። እሷ አድማጭ አግኝታ ትቀደዳለች። ዳያስፖራው ሳይገባው ፖለቲካ እያለ እንደሚዘላብድ፣ አገር ቤት ያለው እውነት ሌላ እንደሆነ አስረዳች። እሷ የሳለቻት ኢትዮጵያ የት ነው የምትገኘው እስከሚል ያበደው ዞረበት። “ ከተማው አብዷል” ስትል ስለህንጻው ግንባታ አወጋች። ሰው መቀመጫውን ቀርቅሮ እንደሚጠጣ አከለች፤ እድገቱ በመሰላል እንኳን እንደማይደረስበት መሰከረች። አሁን ያበደው አላስችል አለውና ጠየቀ “ እዛው ኢትዮጵያ?” አላት። አረጋገጠች”” ማየት ማመን እንደሆነ አመላከተች።

ስለ እርብሻው ጀመረች። “ ጥቂት” ስትል አሳንሳ ጉዳዩ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ገለጽች። ሰው ይሞታል። ይታሰራል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ነበር። አሁንም መልኩን የቀየረ አዋጅ አለ…. የማይጻፉትንም ጉዳዮች ጠቅሶ ጠየቀና “ ይህ ሁሉ ለጥቂቶች” ሲል ምላሽ ጠበቀ። ባልደረባዬ …

ባልደረባዬም ሙሊት ነው። ሴትየዋ እንደ ጋሪ ነች። መናገር እንጂ ማሰብ አትችልም። ፋናና ኢቲቪን የምታዳምጥም አትመስልም። ቀባጠረች። ግድያው ላይ እና የስር ቤቱ ሮሮ ላይ ሙግት ገቡ። ቡና ስኒ ተሰበረ። ተዘላለፉ። በብሄር ተኮር ስድብ ተናረቱ። ይህን ጊዜ ያበደው ጥሎ ወደ ሚኖርበት ከተማ አመራ።

ኦሮሚያና አማራ የሚገሉት የመከላከያ አባላት ሳይሆኑ ራሱ ወንደምህ ነው። ሆዳም ወንድምህ ነው። ህወሃት ምን ያድርግህ? ደሙን አፍሶ ነጻ አወጣህ።አይተህ የማታውቀውን አሳየህ… “ ስትል አምባረቀች። ተቆጣች። ለምን ተቆታች መሰላችሁ?

ባልደረባዬ ሰማ ሰማና “ ሁሉም እኮ የራሱን ክልል በነጻነት ቢያስተዳድር ሰላም ይሆን ነበር። ችግሩ እኮ ህወሃት አስተዳድሪዎች ለሹምና ልግዛ ማለቱ ነው።….. ካልሆነ ደግሞ ተገንጠሉ…. ከዛ እዩትና ወደፌት የሚሆነው ይሆናል…. እስከመቼ ሰው ይሞታል? እስከመቼ ጥይት?…. አንቺ አልደረሰብሽም ይሆናል… ”ሌላም ብዙ ብዙ አለ….

ያበደው ወደ ማደሪያ ጎጆው እያመራ አሰበ። “ ሆዳም ወንደምህ” ምን አጠፋች ይህቺ ሴት? ምንም!! በቃ ብልጭ ሲልባት የልቧን ተናገረች። አላውቀበት ያሉ …. አይ ኦህዴድ፣ አይ ደህዴን? አይ ብአዴንአይ ሁሉምያበደው የሰማውን መርዶ ይዞ የፈረንጇ ቦሰና ጋር ሄደ። ነገራት። ገረማት። “ምን” አለች? ወንድም ወንድሙን ይገላል? ያስራል? ይገርፋል? ሃሬ ጉድእግዚኦ ማለቷ ነው!!

ሰላም ሁኑ!!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *