ከትናንት በስቲያ በአዲግራት ዩኒቨርስቲ የሃብታሙን መገደል ተከትሎ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሙሉ በሙሉ የብሄር ግጭት ይከሰታል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተማሪዎች አስታወቁ። የአዲግራት ተማሪዎች ሃብታሙ ተደብድቦ መሞቱን በድምጽ አረጋገጡ። ዩኒቨርስቲውም አምኗል። ድብደባውን ፈጽመዋል የተባሉ መታሰራቸውን ዩኒቨርስቲው ይፋ አድርጓል። በግጭቱ ምሽት የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች በአንድነት በላይብረሪ ውስጥ ማደራቸውን አመልክተዋል።

በድምጽ ለአሜሪካ ሬዲዮ ከአዲግራት ዩኒቨርስቲ ምስክርነት የሰጠ ተማሪ ” በዕለቱ አሽሙር ቢጤ ያለው የትግርኛ ዘፈን ሲዘፈን የአማራ ተማሪዎች ዘፈኑ እንዲቆም ጠየቁ” ሲል ብሄርን ማዕከል ያደረገው ግጭት እንዴት እንደተነሳ አስረድቷል። በዚህ የዘፈኑ ይቁም ጥያቄ የተነሳ የተጀመረው ግብ ግብ ወደ ለየለትና ክፍል ድረስ የዘለቀ ድብድብ አስነሳ። የቻለ ሸሸ ያልቻለ ተጎዳ። 

ከጎጃም ለትምህርት ወደ አዲግራት ያመራው ሃብታሙ ያለው ስንሻው ህይወቱ አለፈ። አንዳንዶች “ሞቶ ተገኘ” ቢሉም ፊደል ለመቅሰም አዲግራት የተላከው ተማሪው ተደብድቦ መሞቱን ዩኒዘርስቲውም አላስተባበለም። ዛጎል ይህንኑ በዝርዝር መዘገቡ ይታወሳል። ከግድያው ጋር በተያያዘ ቁጥራቸው ያልታወቀ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በአዲግራት ፖሊስ ጥበቃ ያደረገለት ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ታውቋል። አሜሪካ ሬዲዮ እንዳለው በሰልፉ አዛውንቶች “እርቅ ይውረድ” ሲሉ ጠይቀዋል። በዩኒቨርስቲው 

ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንደሚሰማውና አሜሪካ ሬዲዮ ይፋ እንዳደረገው በወልደያ፣ በአምቦና በጎንደር ዩኒቨርስቲ የአዲግራቱን ግጭት ተከትሎ ብሄርን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ይህ እንቅስቃሴ ሊሰፋ እንደሚችል ተግምቷል። ከተጀመረ መላውን የአገሪቱን ዩኒቨርስቲዎች እንዳያዳርስ ስጋቱ ቤተሰቦችንና ዜጎችን አስጨንቋል።

” ለጄን ተበድሬ ሸኘሁ” ያሉ አንድ እናት በጭንቀት መታመማቸውን ይናገራሉ። እኚሁ በአዳማ የሚኖሩ እናት እንዳሉት ” ልጄ ሁሉም ቀርቶባት ብትመጣልኝ ዳግም የተወለድኩ ያህል ይሰማኛል። አሁን በርሬ እንዳልሄድ ገንዘብ የለኝም። ምን ልሁን?” በማለት እንደሚያነቡ የሚቀርቡዋቸው ለዛጎል ተናግረዋል። ልጃቸው በየትኛው ክልል በሚገኝ ዩኒቨርስቲ እንደምትማር ግን አላስታወቁም።

ሰመጉ ችግሩ ወደ ለየለት ብሄር ተኮር ግጭት እየተሸጋገረ መሆኑንን አሁናገሪቱ በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በዝርዝር በመጠቆም ነው። ሰመጉ እንዳለው በሁሉም ዘርፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚታየው ችግር አሳሳቢ ነው። አገሪቱን ከተራ የደጋፊነትም ሆነ የተቃዋሚነት ስሜት በመውጣት ከገባችበት ቀውስ ለማውጣት ቀድሞ መሮጥ ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል።

በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ህይወቱ ካለፈው ሃብታሙ በተጨማሪ አንድ የኦሮሚያ ተወላጅ ተማሪ በሽሽት ከሶስተኛ ፎቅ ዘሎ መውደቁና ጉዳት የደረሰባቸው ተጨማሪ ተማሪዎች ህክምና ቢያገኙም ጤናቸው በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም። የአማራ ክልልም ሆነ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣኖች ይህንኑ አደጋ አስመልክቶ ስላደረጉት ማታርትም ይሁን በስፍራው ተገኝተው ስላደረጉት ነገር እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

 

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

አሁን ከየአቅጣጫው የሚወጣው መረጃ ” የጎሳ ፖለቲካ ቢቀርስ ” የሚል ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ ደግሞ ተማሪዎች በክልላቸው ወይም ዋስትና የስማናል በሚሉት አካባቢ ሄደው እንዲማሩ ማድረግ ዋና መፍትሄ መሆኑንን ነው። አለያ ግን አገሪቱ የተረጨባት የጥላቻ ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ ሲነድ ማየት ግድ ነው!!

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *