ነገሮች እንደ ድሮ አይቀጥሉም። የብሄር ብሄረሰቦች መብት የሚፃረሩ ቡድንተኝነት፣ መርህና ፕሮግራምን መሰረት ያላደረገ መተዛዘል፣ አለመተጋገል፣ በጥርጣሬ መተያየት፣ ለመነጋገርና ዝግጁ አለመሆን መደገም እንደሌለባቸዉ ፤እንዲሁም ለአንድ ፖለቲካዊ ፕሮግራም፣ ለአንድ ህዝብና ሀገር የቆመ ድርጅቶች እንደ ቀድሞ ተግባብተው ለመስራት ወስነዋል፤ ከዚህ ሌላ አማርጭም እንደሌለ ተግባብተዋል።

በዚ የቀዉስናቭ ያለመረጋጋት ወቅት ከወደ ኢህአዴግ ምክርቤት ጥሩ ዉይይት እየተደረገ መሆኑ ልነግራቹህ እፈልጋለሁ። ቆፍጠን መረር ያሉ ዉሳኔዎች እየተላለፉ ይገኛሉ። በሚከተሉት ከፍተኛ ተግባራዊ ለዉጥ ያመጣሉ በተባሉ ዙርያዎች ዉሳኔዎች እየተላለፉ ናቸው። እርግጠኛ መሆን የሚቻለው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ የማይግባባው ኢህአዴግ ከዚህ በኃላ አይኖርም። በዚህ ክፍተት ምክንያት ሲፈነጭ የነበረው የዉስጥም የዉጭም ሃይል ቦታ እንደማያገኝ ልገልፅላቹህ እወዳለሁ።

እስካሁን ባለው ዉይይት ብዙ የተነሱ ነገሮች ቢኖሩም የሚከተሉት አራት ነጥቦች እንድታዉቁዋቸዉ ዘንድ እነሆ፡፡

1,የተፈናቀሉ ዜጎች በቂ ካሳ ተከልልዋቸው ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ። በአጣሪ ኮሚሽን የሚጣሩ ነገሮች ተጣርተው በዚህ የማፈናቀል ወልጀሎች ተሳታፊ የነበሩ ባለስልጣኖች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ። ይህም ከፍተኛ አመራሮችንም ጭምር ያካትታል።

2, በአራቱም የኢህአዴግ አባላት ተከስቶ የነበረው መጠራጠርና ኩርፍያ ከምን እንደመነጨ፣ ምን ጉዳት እንዳስከተለ በዝርዝር ካየ በኃላ ድፍረት የተሞላባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች አስቀምጦ ሁሉም የግንባሩ አባላት ሙሉ ለሙሉ ተስማምተዉበታል። በድርጅቶቹ የሚታየው ብሄርን ማእከል ያደረገ የጎራ መደበላለቅ እና የሰልፍ መዛባት ባስቸዃይ ለማረምም ተስማምተዋል። ይህ እንዲፈጠር ያደረጉ ባለስልጣናትና መደበኛና ኢመደበኛ የሆኑ አፈ ቀላጤዎቻቸው እንዲታረሙና ተጠያቂ እንዲሆኑ መግባባት ተደርሶበታል።

3, በየቦታው ብልጭ ድርግም እያለ ያለው አለመረጋጋት መነሻው ዉስብስብ ቢሆንም በኢህአዴግ የአላማ አንድነት መላላት የተፈጠረ በመሆኑ ቁጥር ሁለት ባስቸዃይ ተግባራዊ ሲሆን የመንግስትና የህዝብ ትኩረት ወደ ልማት የሚዞርበት ስትራቴጂ ይነደፋል። ኢትዮጵያ ከሁከት ቀጠና ወደ ልማት አዉድማ መቀየር ዋናው የሁሉም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እምብርት መሆን አለበት በሚለው ኢህአዴግ መግባባት ላይ ደርሷል።

4, የፌዴራል መንግስት በሙስና ላይ ጀምሮት በሁከት ምክንያት ተስተጏጉሎ የነበረው ፀረ ሙስና ትግል በስፋትና በጥልቀት በቅርቡ ይቀጣጠላል። ሙሰና ያለ ምንም ሃፍረትና ድምበር ለመታገል የጋራ አቛም ተይዞበታል። በየቦታው በተፈጠረው ሁከት ምክንያት መታሰር የሚገባቸው ጉምቱ ሙሰኞች በዚህኛው ዙር ገቢ እንደሚሆኑና ለዚህም የድርጅቶቹ አመራሮች ሙሉ ትብብር እንደሚያደርጉ ተስማምቷል።

ማጠቃለያ፥ ነገሮች እንደ ድሮ አይቀጥሉም። የብሄር ብሄረሰቦች መብት የሚፃረሩ ቡድንተኝነት፣ መርህና ፕሮግራምን መሰረት ያላደረገ መተዛዘል፣ አለመተጋገል፣ በጥርጣሬ መተያየት፣ ለመነጋገርና ዝግጁ አለመሆን መደገም እንደሌለባቸዉ ፤እንዲሁም ለአንድ ፖለቲካዊ ፕሮግራም፣ ለአንድ ህዝብና ሀገር የቆመ ድርጅቶች እንደ ቀድሞ ተግባብተው ለመስራት ወስነዋል፤ ከዚህ ሌላ አማርጭም እንደሌለ ተግባብተዋል።

ዉይይቱ በሌሎች አጀንዳዎች በስፋት ቀጥልዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከዚህ ስብሰባ በኃላ የ ፖለቲካ ሰልፉ ግልፅ ሆኖ እንዲወጣ ያደርጋል ብቻ ሳይሆን ከዉስጥ መደበኛና ኢመደበኛ ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ከግብፅና ከሻዕብያ ተላላኪ አምስተኛ ረድፈኞች እንዲሁም ከነብሰ በላ ባለስልጣኖች ሊራገፍ የሚችልበት፣ በዚህም ህዝቡ የሚደመጥበት፣ ሰላማችን የማይናጋበት፣ ብሄር ብሄረሰቦች የማይጠራጠሩበት ሀገር የመሆን እድል የሚሰጡ ዉሳኔዎች እየተላለፉ ናቸው።

ሙሉ መግለጫው ሲወጣ ደም ብዛት፡ ሰኻር፡ የሚነሳባቸው ይኖራሉ፡፡ በተስፋ መቁረጥ መቃብር እሚደፈኑም ብዙ ናቸዉ፡፡

ዝግጅት ክፍሉ- ይህ ጽሁፍ የተበተነው በማህበራዊ ገጽ ነው። ከአቶ ሰማኽኝ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ አግኝተን ለጥፈነዋል። ጽሁፉ ከፍተኛ ጉዳዮችን ያካተታና በታላላቅ መረጃዎች የታጨቀ በመሆኑም ከመረጃነት ከመሆኑ አንጻር ቢስተናገደም፣ እዚህ ላይ እስካተምነበት ድረስ በሚታወቁ የድርጅት ደረ ገጾች ላይ እንዳልታየ ለመግለጽ እንወዳለን።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *