ህዝቦች በታሪክ በማናቸው ኣለም በመካከላቸው መሰረታዊ የሆነ የማይታረቅ ቅራኔ እና ግጭት ንሮዋቸው ኣያውቅም ። ቢኖራቸውም በቤት ዘመድ በጎረቤት ሽማግሌ  ፣በገር   ሸማግሌ ፣በሃይማኖት መሪዎች ታርቀው ተመልሰው ኣብረው በሰላም ይኖራሉ ። የሃገራችን ህዝቦችም ወደ ኃላ ተመልሰን ታሪክ ስንዳስስም ባለፉት ኀላ ቀር በሆኑ ስርኣቶች እንኳን ብንመለከት የመሬት ወሰን ፣የግጦሽ ፣ በጋብቻ ኣንዱ ለኣንዱ በማመጽ ፣ ባልታሰበ ድንገት በባህላዊ መዝናኛ ስፍራዎች በሰርግ በባኣላት  ፣በስሜት ወ ዘ ተ ይጣላሉ እስከ ሂወት ማጥፋት ይሄዱ ነበር  ። ይህ ግጨት ግን ከላይ እንደ ጠቀስኩት መሰረታዊ የመደብ ልዩነት ስለሌላቸው ባሉዋቸው ባህላዊ የግርጭት የኣፈታት ዘቤ ይፈቱት ነበር ።

የኃላ ኃላ ግን  የመደብ  ልዩነት  ፣የሀብት ልዩነት ፣ እኔ  ልብለጥ  ፣እኔ ነኝ የበላይ ፣እኔ ልዘዝ ፣ ኣንተ ኣታዘኝም  ከሚል የሚፈጠር  የግል ፍላጎታቸው  ለሟሟላት ወይ  ለማርካት  ለህዝቦች በሆነ ደካማ ጎን በመግባት  ኃላ ቀር  የባህል እሴቶች በመጠቀም   በህዝቦች መካከል  ያልሆነ ስሜት   በመፍጠር የግላውነት  ስልጣናቸው በመረጋገጥ  ህዝቡን  ከፋፍለው   ከተራ ጠብ እስከ  በጦርት    የመተላለቅ  ወንጀል በመፈጸም  መሰረታዊ ልዩነት  የሌላቸው ህዝቦች ከፋፍለው  እርስ በእርሳቸው  በመጣረስ   እነሱ ንጉሶች ሆነው  የሃገሪቱ  ሁሉም ኣይነት እሴቶች  ሰብስበው በመያዝ  በመጠቀም  የግላዊ  ፍላጎታቸው በህዝብ ደምና ሂወት ኣስከፍለው  ከማይታረቅ ደረጃ ካደረሱ በኃሏ እነሱ  የህዝቦች  ግጭት ቀዋሚ ዘብ ኣድርገው  ናጥጠውና ዶልቷቸው  ይኖራሉ ። ይህ የሆነበት  ወይ ገዥዎች የህዝብን ንቃተ ህሊና   ተጠቅመው   የሚጫወቱባቸው የነበሩ ህዝበች   መሰረታዊ  ወዳጃቸውና ጠላቷቸው ባለማወቃቸው ወይ በመሳታቸው ነው።

በሀገራችን የነበረ እና ያለው የጎጥ የወረዳ የኣውራጃ የክልል ፣የሀይማኖት ፣ የዘር የቢሄር ልዩነት ባለፉት የዘውዳዊውና የደርግ ስርኣቶች ህዝብን ባሉት ባህሏዊ እሴቶች ተጠቅመው በመጋጨት በመከፋፈል ጨቋኝና በዝባዥ ፋሽት ስርኣቷቸው ኣስቀጥለዋል ። ይህ የሆነበት ገዜው በሀገራችን ቡዙ የተማረ ሰው ባልነበረበትና ጠላቱና ወዳጁ ባለሟወቁ ወይ መሳቱ ነው ።
የኣሁኑ ይባስ  የኢህኣደግ በተለይ ደግሞ የሀወሓት ፣የባኣዴን ፣ የኦሆዴድ ፓርቲዎ በሚል  ስም የተሰባሰቡ  ቡዱኖች   እና  ተቀጥያ   ኣጋሮቻቸው በኣሁኑ  የሰለጠነ 21 ክፍለ  ዘመን  እጅግ  ብዙ  ከህዝባችን ከ40% በላይ የተማረና ቀለም  የቆጠረ  ሰው ባለበት፣  ከ200  ኣመት በላይ ወደ   ኃላ  ተመልሰው  የመዘበሩት የሀገራችን ሃብት ሟጥጠው ይዘው የስርኣቱ መዋቅር ወይ ኔትወርክ  በዘመድ ኣዝማድ ፣በቤተሰብ  ወይ የምዝበራ  ሸሪኮቻቸው ጥቂት ሌቦች የህዝብ  ሀብት በሞኖፖል  የያዙ ተዘርግተው ኣስፋፍተው በመያዝ የስልጠን እድሜያቸው ለመራዘም  ታሳቢ በማድረግ  ለህዘባችን  ባሉት ኃላ ቀር  ባህላዊ እሴቶች  በመጠቀም በማሃከላቸው  ገብተው ከፋፍለው በመጋጨት ምንም  መሰረታዊ የሆነ የመደብ ልዩነት በሌለባቸው ዜገች  መካከል  ገብተው  ወደ ዘርና ቢሄር ጎጥ ወርደው  ትግራይ  ኣማራ ኦሮሞ ኣማራ ፣ ሱሟል ኣፋር  ወ ዘ ተ  አስከታች ትምህርት ቤቶች በመውረድ በተለይይ በኣሁኑ ጊዜ  እንደ  ኣንደኛ   ጠላት ኣድርገው ለትግራይ ህዝብ በመነጣጠር  በዙ  የዚህች  ኣገር የወደፊት  ተሰፋ የሆኑ  ህጻን   ሊሂቃን   በመግደል  የስስታም  ኣላማቸው  ማሳኪያ  ኣድርገውታል  ። በተጨማርም በኦሮሞና በሱማል ያለው  ምንም የማያውቁ  ህጻን ልጆቻችና ወንድሞቻችን  የወደፊት የሀገራችን ተስፋ የሚሆኑ  ህጻናት ልጆቻችን እያለቁ  እነሱ እንደ  ሸራቶን ያሉ ግዙፍ ሆቴሎች እየተዝናኑ ይኖራሉ  ይስቃሉ  የህዝብ ሃብት ይረጫሉ  ። ልጆቻቸው በውጭ ኣገር በከባድ  የዶሏር  ወጭ  ተቀማጥለው ይኖሯሉ ።
ህዝባችን በተለይ ሙሁራንና ተማሪዎች ሳይማር ያሰተማራቸው ያልተማሩ ወገናቹ መርቶ ወዳጅና ጠላታቸው ኣውቀውና ለይተው እንዲቃወሙ ኣድርጎ የሙሁሯውነቱ መሪ ሚና እየተጠቀመ ለከፋፋይ ገዥዎችና በዝባዞች ታግሎ እንደማስወገድ ፈንታ እስትራተጅክ ወንድሙ ለሆነው ወይ ዜጋው በዲንጋይ እንደ ደእባብ ቀጥቅጦ መግደል ምንኛ ድንቁርና ኣሳዛኝ መሆኑ እጅጉን ያሳዝናል ።
ይህ የሚያመለክተው ደግሙ እናንተ ይህ ድርጊት የምትፈጽሙ ማህበረሰብ ምንም መሰረታዊ የመደብ ልዩነት የሌላቹ ወገናቹ የምትጨፈጭፉ ወገኖች በትክክልም ወዳጅና ጠላታችሁ የማታውቁ መሆናችሁን ያመለክታል ።
በመሆኑ ኣሁንም ወንድም ከወንድም ፣ወገን ከወገን ከመጨፋጨፍ በማኸላችን ገብቶ እኛን በማፋጀት ከፋፍሎ የስልጣን እድሜያቸው ሊያራዝሙ ወደ እሚፈልጉ ኣይናችና እጣታችነ በመቀሰር ተባብረን ታግለን ኣስወግደን ኣገራችን እናድን ። ኣሁንም ደግሜ ላሳስባችሁ እምፈልገው ልጆቻችን በማሀከላቸው ምንም ልዩነት በሌለባቸው ህዝቦቻችን በስተጀርባ ሆነው ጥቅማቸው በሚያሳኩበት መንገድ እየገፉ እሚያፋጁት ያሉ ወደዳቹም ጠላችሁም የበኣዴን ፣የህወሓት የኦሆድድ ሴራ የሚፈጸም ያለው ነው ።

በመጨረሻ ማሳሰብያ ፣
——————————
ለመላው  የኢትዮጱያ  ህዝቦች  ቢሄር   ቢሄረሰብ ሀይማኖት ኣማኒያን ፣ሙሁራን  ተማሪዎች  ፣የሀገራችን  ኣለኝታ  የሆኑ  የጸጥታ ሃይሎች  ፣ የፍትህ  ኣካላት    በመላው  የመንግስት  ሰራተኛ  ስቢክ ማህበራት ወ ዘ ተ በሙሉ  በዚህ ጽሁፍ መግብያ  እንደገለጸኩት  ፣እኛ ኢትዮጱያውያን  ከጥንት  ጀምሮ በውረድ ተዋረደ  በታሪካች  እንደሚታወቀው  ምንም እንኳን በዘመናቸው  የነበሩ የመሰፍንቶቸ ንጉሶች ለስርኣታቸው መቆያ ለከፋፍለህ ግዛ  ከሚል ስልታቸው  በህዝቦች መካከል  የሚፈጥሩት  የነበሩ  ትናንሽ ግጨቶች  ቢኖሩ ። ህዘብ ግን ለሚፈጥሩት  ሴራ  ከመጤፍ እንኳ  ሳይቆጥር  በሁሉም  ክፍለሀገሮች ተዘዋውሮ ይኖራል ፣ነሮ ይመሰርታል   ከማናቸው ዘር ወይ ቢሄር በዬየሃይማኖት እምነቱ  ጋብቻ ይፈጽማል  በሄደበት  ቦታ ይኖራል ፣ይነግዳል መሬት እኩል  ከኣካባቢው ህዝብ  እኩል  ያርሳል  ቤት ይሰራል  ፣ የመንግስት  ወይ የግል ድርጅት  ሰራተኛ  ፣ሀኪም ፣ኣስተማሪ ፣የግብርና ባለሞያ     ወ ዘ  ተ በእጣ ወይ በምድብ ተመድቦ ይሰራል   ነበር ። የእገሌ ቢሄር የእገሌ ዘር ኣይባልም  ነበር ።
የኣሁነዎቹ   የግራዚያኒ     ዘረኛ ፋሽሽቶች  ግን  ላባቸው  ያላፈሰሱበት ያልሰሩበት የመዘበሩት የህዝብ ሀብና  የስልጣን  ጥማታቸው ለመጠበቅ እና  ህዝብ  ነቅቶባቸው  እንደሆነ  እና ሊውጣቸው  እንደሆነ  በማወቃቸው  ኣንደኛ  ኣስቀድመው  ህዝቡን በሆነ መንገድ  እርስ በእርሱ  ኣፋጅተው  እነሱ  በግጭቱ  ተሸፍነው  የዬኣካባቢያቸው  ንገሶች ሆነው ምዝበራቸው  ለማስቀጠል።ሁለተኛ  ለወደፊቱም  ያች ከፍተኛ  ስልጣን  የሚሏት      የጠ / ሚንስቴርነት  እና ቁልፊ የሚኒስቴርነት ቦታ ለመያዝና  የሃገራችን   ኣንጡራ  ሃብት  በበለጠ ተደራጅተው  ሟጥጠው ለመዝረፍና  ለመበዝበዝ  ቦታቸው ለመማቻቸት  ታሳቢ በማድረግ  ነው ።
እናኖሆ  የጠነጠኑት  ሴራ  ደግሞ  ወጤቱ   ከላይ እንደጠቀስኩት  ኣሁን  ለኣንድ  ቢር  ለትግራይ  ህዝብ ያናጣጠረ  የፍጅት ኣዋጅ  ኣውጀው  አደጋ እየፈጸሙ እና ፍጅቱ  ከዛበላይ  እንዲሄድ  በጀርባ  ሆነው  ንቃተህሊናቸው  ዝቅላለ ወይ ከነሱ  ትርፍራፊ  ተጠቃሚ  ለሆኑ ወገኖች እነዱ እያጫረሱን  ይገኛሉ ።  በኦሮሞና  በሱማልም እያፈጁት ነው።በዚሁ ካልተሳካላቸው
ደግሞ ኣማራ ከኦሮም ሌላ ሌላ ሊፈጽሙ እሚያሳፍራቸው ነገር የለም ።
በመሆኑ ካላይ የጠቀስኳቹ የማህበረሰብ ኣካላት እንደዚህ ኣይነት ዘግናኝ ነገር ድሮ እንኳን ህብረተሰቡ ያልተማረና ኃላ ቀር በነበረበት መሪዎች እንደፈለጉ በጀርባቸው ያልጨፈሩበት እንዴት በኣሁኑ ጊዜ እጅግ ቡዙ የተማረ ህብረተሰብ ባለበት የኣለም ስልጣኔ በኣገራችን በተስፋፋበት እንዴት እንሸወዳለን ።
ስለዚህ ሁላችንን ዜጎች የጥንት ኣብሮኖታችን ታሪካችን ፣ሉኧሏዊ ኣገራችን ኣሴታ ጠብቃ ትጓዝ ዘንድ ለነዚህ ለህዝብ  ፣ለኣገር ደንታ የሌላቸው ለሆዳቸው ብቻ ኣጥብበው የሚያስቡ በታኞች ኣስወግደን የተረጋጋችና የበለጸገች ህዝቦቻ ተፋቅረው ተቃቅፎው በኣንድነት የሚኖሩባት ኣገር እንድትሆን ተጠናክረን እንጣር ። ኣምላክ ኢትዮጱያ ሀገራችንና ህዝቦቻ ኣንድነታቸው  ጠብቆ የኑርልን  አሜን
ከኣስገደ  ገብረስላሴ
መቀለ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *