ሳዑዲ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ከፍተኛ እዳ እንዳለባቸውና እሳቸውን አስገድዶ የማስከፈል ችግር መኖሩን መስማት የተለመደ ነው። እዳ ብቻ ሳይሆን ድርጅቶቻቸው ግብር በውቅቱ ባለመክፈልም ይታወቃሉ።


የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው ሼኹ በዱቤ ከገዟቸው ድርጅቶች ሁለት ቢሊዮን ብር ሳይከፍሉ ዓመታት ተቆጥረዋል። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ በተለያዩ ወቅቶች ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ወደ ህግ ሊያመራ እንደሚችል ለዓመታት ሲጠቁሙም ነበር።
እዳ ካለባቸው ሌሎች ድርጅቶች በተለይ ሺኹ በእዳ የገዟቸው ሆራይዘን አዲስ ጎማ፣ ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ፣ የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በበቃ ኮፊ ስቴት ኩባንያዎች አስመልክቶ ያለባቸውን ሁለት ቢሊዮን ብር ዕዳ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ እንዲከፍሉ መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር ያስታወሰው ዜና፣ አሁን በመጨረሻ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መወሰዱን ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩን የጠቀሰው ሪፖርተር ሆራይዘን አዲስ ጎማ 198.7 ሚሊዮን ብር፣ የቡና ማከማቻና ማዘጋጃ 174.6 ሚሊዮን ብቻ ከፍለዋል። ሌሎቹ ድርጅቶች ግን በተደረሰው ስምምነት መሰረት፣ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ እዳቸውን አልከፈሉም። በመጨረሻም ሚኒስቴሩ ህግ ይገላግል ዘንድ ወስኗል።
እንደ አቶ ወንዳፍራሽ በኩባንያዎቹ ላይ በተናጠል ክስ ተመሥርቷል ሲሉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት መቆጠባችውን የሪፖርተር ዜና ያስረዳል። ሚኒስቴሩ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት በተጨማሪ፣ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከባለዕዳ ኩባንያዎቹ ጋር ምክክር አድርጎ ነበር፡፡ በወቅቱ ባለዕዳዎቹ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የገበያ ክፍተት፣ እንዲሁም የምርታማነት ችግር መኖሩን በመግለጽ የመክፈያ ጊዜ እንዲከለስላቸው አፅንኦት ሰጥተው ጠይቀው እንደነበር ዜናው አስታውሷል።
ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ ኦሮሚያ ክልል ወደ ህግ አቅርቦ እርምጃ በመውሰድ ቀዳሚ ሲሆን የወቅቱ ፐሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ሳይፈሩ ግብር እንዲያስከፍሉ፣ ሼኹ ያጠሩትን ሰፊ መሬት የማይሰሩበት ከሆነ በህግ አግባብ እንዲወርሱ መመሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሲፎክርና ሲምል ያለ እርምጃ አስተዳዳሪ ያፈራርቃል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *