ድርጅቱ በሶስቱ ዋና ጉዳዮች ችግር ካለበት አሁን ለመወያየት የሚያስችል ህይወት የለም። የሞተ ነው ማለት ነው። አንድ አገር የሚመራ ፓርቲ፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከነጠፈበት፣ የእርስ በርስ መጠራጠር ከበላው፣  የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ እጦትና የሕዝባዊ ወገንተኝነቱ ከተሸረሸረና እዚህ ደረጃ ከደረሰ በየትኛው መስፈርት አለ ይባላል?”

ከድርጅቱ አመራርነት ተገለዋል የተባሉትን ነባር ታጋትዮች እያሳተፈ መካሄድ የጀመረው የኢህአዴግ ስራ አስፈሳሚ ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶው ተመልሶ ወደ አዘቅት መግባቱን አስታወቀ። አንድ ፓርቲ በሚለካባቸው የመኖር ምልክቶች ሲለካ አከርካሬው መጎረዱን በዝርዝር አመላከተ። ቀደም ሲል ጀምሮ ሲባሉ የነበሩ ድክመቶችን መዘርዘር ከስራ አስፈጻሚው ተሰጠ የተባለው መግለጫ ” ስብሰባው ሲጠናቀቅ ለህዝብ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ ውሳኔዎች ይወሰናሉ” ይላል። የህዝብ ጥያቄ ፖለቲካዊ “በቃችሁ” ስለመሆኑ ኢህአዴግ አሁንም ያለው ነገር የለም። 

ባለፉት ሁለት አመታት ኢሕአዴግ ያደረገው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ ከውጤት አንጻር ገምግሞ ያወደሰው ስራ አስፈጻሚው፣  “ጥልቅ ተሃድሶው ” በሚፈለገው ደረጃ ጥልቀት ያልነበረው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተመልሶ ወደ አዘቅቱ ተመልሷል ሲል ራሱን ባደነቀበት አንቀጽ ላይ ርግሟል። ይህንኑ ተመልሶ አዘቅት ውስጥ የገባውን “ጥልቅ ግምገማ” እንዴት ነፍስ እንደሚዘራበት አላብራራም። ይልቁኑም አገሪቱ ለወደቀችበት አስጊ ሁኔታና ለደረሰው እንዲሁም እየደረሰ ላለው እልቂት ሃላፊነቱን ወስዷል።

እስካሁን በተደረገው ጥልቅ ግምገማ ከስኬት ጎዳና እያራቁ የሚገኙ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት መታጣት፣ የእርስ በርስ መጠራጠር፣ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ እጦትና የሕዝባዊ ወገንተኝነት መሸርሸር ተገቢ ውይይት እንደተደረገባቸው ያውሳው መግለጫ፣ “የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ፣ የልማትና የሰላም ጥያቄዎችን በሚገባ ለመመለስ በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል” ሲል ያውጃል።

የዘወትር የዛጎል ተባባሪ የሆነው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ከዴን ማርክ እንዳለው ድርጅቱ በሶስቱ ዋና ጉዳዮች ችግር ካለበት አሁን ለመወያየት የሚያስችል ህይወት የለም። የሞተ ነው ማለት ነው። ” አንድ አገር የሚመራ ፓርቲ ” ይላል አስተያየት ሰጪው ” አንድ አገር የሚመራ ፓርቲ፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከነጠፈበት፣ የእርስ በርስ መጠራጠር ከበላው፣  የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ እጦትና የሕዝባዊ ወገንተኝነቱ ከተሸረሸረና እዚህ ደረጃ ከደረሰ በየትኛው መስፈርት አለ ይባላል?” 

በሁሉም አቅጣጫ የፈሰሰው ደም፣ ከማጎሪያ ቤቶች የሚሰማው የግፍ ድምጽ፣ በየደጁ የተጣለው ድንኳን፣ የተፈናቀሉ ወግኖች፣ የጎሳ ፖለቲካው ያስከተለው የተከማቸ ቂም በቃላት ድርደራ ሊሽር እንደማይችል ኢህአዴግ ከማንም በላይ እንደሚረዳው አስተያየት ሰጪው ያስረዳል። በፖለቲካ የህልውናው ውሃ ልክ የደረሰበትን ደረጃም ያውቃል። ኢህአዴግ የማይረዳው እሱ ራሱን እንደሚያታልለውና ለራሱ ይቅርታ እንደሚያደርገው ህዝብ በሙሉ የሚታለለ አድርጎ ማሰቡ ነው።

በአገሪቱ ለደረሱ ጥፋቶች ሁሉ ተጠያቂ መሆኑንን ያመነ ድርጅት ቀሪ ተብሩ ስልጣኑንን በፈቃዱ መልቀቅ ብቻ እንደሚሆን የገለጸው አስተያየት ሰጪ ” አገሪቱ አሁን ለወደቀችበት አደገኛ ቀውስ በሽታው እኔ ነኝ ያለ ፓርቲ ራሱን እየሰደበ ሲምልና ሲገዘት መስማት የዘመኑ ሃፍረት ነው” በማለት ያስረዳል። 

አሁን ያለው ትውልድ በነሱ ፖለቲካ ያደገ፣ የኖረና፣ የተሰራ መሆኑንን ለሚረዱ ፖለቲከኞች እንዲህ አይነት ቀልድ ማሰማት ትርፉ ችግሩን ማባባስ እንደሆነ አስተያየት ሰጪው አመልክቷል። 

የኢህአዴግ ፓርላማ በአስቸኳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንሰላለው የዘር ግጭትና አደጋ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቀበት በአሁኑ ሰዓት ለኢህአዲግ ስራ አስፈጻሚ የተላከ በሚል የተሰራጨው መግለጫ ” አለን ” የሚል መልስ ለመስጠ እንደሆነም ግምት አለ። 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *