ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢህአዴግ በይፋ ተከዳ – በፓርላማ ያለመከሰስ መብትን እንደማያስተናገዱ በአዴንና ኦህዴድ ስምምነት አላቸው

“የህወሃት የበላይነት አብቅቷል” ሲሉ ነው ማብራሪያቸውን የጀመሩት። ድፍን የኦህዴድ አባላት ህይወታቸውን ለመስጠት ተሳማምተዋል። አቋሙ በድርጅት ደረጃ የተያዘ መሆኑንን ያመለክታሉ። ህወሃት አሁን ያሉት አመራሮች እንዲነሱ ምኞቱ ቢኖረውም የሚሰማው እንደሌለ ይጠቁማሉ። ለዚሁም ሲባል የፌደራልና የክልል የህዝብ ተወካዮች ሆነው እንዲባረሩ የሚፈለጉትን ለማሰረ የሚጠየቀውን ያለመከሰስ መብት ማንም የሚቀበል የለም። ታመነም አልታመነም ኦህዴድ ድንበር አበጅቷል።

ፓርላማ ዛሬ ሊያካሂድ የነበረውን ውይይት በመቃወም ብአዴን ቁርጠኛ አቋም መያዙ ተሰምቷል። ተጋባዥ ተሰብሳቢዎችም በተመሳሳይ ተቃውሞ አሰምተዋል። ቢቢሲ ይህንን ያረጋገጠ ሲሆን ዛጎል ያነጋገራቸው የኦህዴድ ሰው ጉዳዩን በጥበብ መያዝ አግባብ እንደሆነ አመልክተው ሰለ ራሳቸው ድርጅት በመተኑ ተባግረዋል።

ዛሬ በንትርክ የትቋረጠውን የፓርላማ ስብሰባ አስመልክቶ ይህንን ያሉት የኦህዴድ ከፍተኛ ሰው ናቸው። እኚሁ ሰው ለዛጎል እንዳሉት የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊካሄድ የነበረው ውይይት በተቃውሞ መቋረጡ ኦህዴድ ያሰመረው አዲስ ድንበር ማሳያ ነው። ከዚህ በላይ የሕዝብ አንደበት እንደሚሆን አመልክተዋል።

የዛሬውን ስብሰባ ማቋረጥና እንዲቁረጥ ማድረግ በቂ ማሳያ መሆኑንን ያመለከቱት እኚሁ የኦህዴድ ሰው፣ ” ዛሬ ላይ ቆመን ስናስበው ሰው መሆናችን ሁሉ እስኪረሳ ድረስ፣ ወገኖቻችን ሲሞቱ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰቃዩ፣ ሲፈናቀሉ የማይሰማን በድን አድረገውናል። እኛ ግን ወጥመዱ ብዙ ስለነበር ስራችንን እየሰራን ነበር። አሁን ላይ ኦህዴድ ህዝብ መካከል ህዝብን ሆኖ ከህዝብ ጋር የሚደርስበትን በሙሉ ለመቀበል የወሰነበት ደረጃ ደርሷል፤ ካሁን በሁዋላ በቀድሞው መንገድ የሚቀጥል ነገር የለም” 

ስለዛሬው ስብሰባ መቋረጥ ለተጠየቁት ” ጥድፊያ አያስፈልግም፤ ብዙ ቅድሚያ የሚሰሩ ጉዳዮች አሉ። ዋናዎቹ ጉዳዮች ሲያልቁ ቀስ ብለን ከሚመስሉን ሁሉ ጋር እንመክርበታለን” የሚል አጠቃላይ ድምዳሜ ላይ እንደተደረሰ ገልጸዋል። አያይዘውም አሁን ሕዝብ ከሚያነሳው ግዙፍ ጉዳይ አንጻር በጥቅማ ጥቅም ላይ ጊዜ መስጠት “የትኩሳት ማስታገሻ እንደመቃምና ዋናውን በሽታ እንደመርሳት ይቆጠራል” ብለዋል።

ሰፊ ህዝብ እንደሚወከሉ ያስታወቁት የኦህዴድ ሰው ከመሰል “ወዳጅ” ድርጅቶች ጋር ያለውም ህብረት ጠንካራ በመሆኑ ካሁን በሁዋላ የፖለቲካው ብልጫ ወደየትም እንደማያዘነብል አስታውቀዋል። የልዩነት ደጆች እየተዘጉ መሆናቸውንም አመላክተዋል። በደጅ ህዝብ እየተጨፈጨፈ በቢሮ የህዝብ ወዳጅና አጋር መምሰል በራስ መቀለድና ከሰውነት ተራ መውጣት እንደሆነ በቁጭት ተናግረዋል።

ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ መተናቀቅ በሁዋላ ነገሮች እንደሚለወጡ ይነገራል በሚል ለተጠየቁት ” አሁን እኮ ኦህዴድ ህዝብን ተቀላቅሏል። ስራ አስፈጻሚው መመለስ ያለበት ለህዝብ እንጂ ለኦህዴድ አይደለም” የሚል መልስ ሰጥተዋል። “አቶ ለማን ወይም ዶ/ር አብይን በማስደሰት ወይም በማስፈራራትና በማሰር የሚፈጠር ነገር የለም። ያ ዘመን አልፉል። አሁን ኦህዴድ ቱቦ ነው። ህዝብ እንደ ጅረት የሚያልፍበት!! ጥያቄው ከሕዝብ ስለሆነ ሆነ መልሱም ለሕዝብ ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

የኢህአዴግ መገናኛዎች “የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ” በሚል የሚል ዘገባ ማስተላለፋቸውን አስመልክቶ ” በተቃውሞ ተቋረጠ ቢሉ ይገርማል። ዛሬ ሁሉም ሰው የሚዲያ ባለቤትና ሪፖርተር መሆኑንን መዘንጋት የት ያደርሳል ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊን ከማመን እነሱን ማመን ለሚቀላቸው እንደሚያዝኑም አመልክተዋል።

ከተለያዩ ምንጮች እንደሚሰማው በዋናዎቹ የፖለቲካው ጡንጨኞች ዘንድ አሁን ያላውን የኦህዴድ አመራር የማስወገድ እቅድ አለ። እቅዱ ተግባራዊ የሚሆነው ደግሞ በድርጅት ደረጃ የፓርቲዎቹ ስራ አስፈጻሚዎች፣ ምክር ቤቶችና ከዛም በላይ ጠቅላላ ጉባኤ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል። በዚሁ ሳቢያ እንዲወገዱ የሚፈለጉትን አመራሮች ለማባረርም ሆነ ለማሰር ቁልፉ ያለው ኦህዴድ እጅ ብቻ ነው። 

aba dula 1

በብአዴን በኩልም በተመሳሳይ እንዲህ ያለ ሁኔታ መኖሩ በተደጋጋሚ መጠቆሙ ይታወሳል። በተለይ ሁለቱ ፓርቲዎች ህወሃት ጉያ ውስጥ የመቀጠላቸው ጉዳይ ባለመረዳት፣ በእውቀት ማነስና ከድርጅታዊ ተራ ጥቅም አንጻር በመተመን ከየአቅጣጫው የተዥጎረጎረ አስተያየት እየተሰነዘረበት ቢሆንም ጉዳዩ በወፍ ዘራሽ በሚሰራጩ አስተያየቶች ሊቆም እንደማይችል ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየተናገሩ ነው። ስለጉዳዩ የተሻለ ግንዛቤ አለን የሚሉ ክፍሎች ” እኛ ያልጸለይነው ጸሎት አይነት ፖለቲካ የሚያራምዱ ጉዳዩን እንዳያበላሹት፣ ካበላሹት እና ህዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ከሆነ ጉዳቱ የሁሉም ይሆናል” ሲል ቢያንስ በዝምታ እንዲተባበሩ፣ ያልገባቸውን ቀስ ብለው እንዲመረመሩ፣ ከማህበራዊ ገጾች ጉንጭ አልፋ ንትርክ ራሳቸውን እንዲያቅቡ ይመክራሉ። ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለውጥ እንደሚመጣ እኒህ ክፍሎች ያምናሉ። ፋና የሚከተለውን ዘግቧል። ለማመጣጠን ሲባል እንዳለ አቅርበነዋል።

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊካሄድ የነበረው የህዝብ ውይይት መድረክ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ላይ የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ዛሬ በጠራው መድረክ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው ነበር።

ነገር ግን ተሳታፊዎች ረቂቅ አዋጁ ወደ ህዝብ ወርዶ ውይይት እንዲደረግበት በመጠየቃቸው የምክር ቤቱ የህዝብ አስትያየት መሰብሰቢያ መድረክ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።

የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የህዝብ ውይይቱ ረቂቅ አዋጁ ከተመራበት ያለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ ሊካሄድ የታሰበ እንደነበር ተናግረዋል። ቋሚ ኮሚቴውም የረቂቅ አዋጁን አጠቃላይ ይዘት በተመለከተ አስረጅዎቹን ጠርቶ በአዋጁ ላይ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱንም ነው የተናገሩት።

አሁን ላይ የታሰበው የህዝብ ውይይትም በፕሮግራም የሚካሄድና በደረጃ ወደ ህዝቡ ሊወርድ የታሰበ እንደነበርም አስረድተዋል። ረቂቅ አዋጁ ከተመራበት ጊዜ ጀምሮ አዋጁን ለማዳበር ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው፥ የዛሬው የህዝብ ውይይትም የዚህ አንድ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

ይሁን እንጅ በዛሬው የህዝብ ውይይት ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ህዝባዊ ውይይት መቅደም አለበት በማለታቸው በዚያው ስምምነት ላይ ተደርሶ ለሌላ ጊዜ መራዘሙንም አንስተዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም በአዋጁ ላይ በአዲስ አበባ የተካሄደውን አይነት ህዝባዊ ውይይት በየደረጃው በክልሉ የሚካሄድ ይሆናል ብለዋል።

በቀጣይም በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች ህዝቡን እያወያዩ ለረቂቅ አዋጁ ተጨማሪ ግብዓት እንዲሰበሰብ ይደረጋልም ነው ያሉት። ጎን ለጎንም ቋሚ ኮሚቴው ከአዋጁ ጋር በተያያዘ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እያከናወነ እንደሚቆይም ጠቁመዋል።

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ በምታገኘው ልዩ ጥቅም ላይ ሊመክር የነበረው ስብሰባ ተበተነ

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ሊኖራት በሚገባው ልዩ ጥቅም ላይ ለመምከር በተወካዮች ምክር ቤት የህግና የከተሞች ልማት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የተጠራው ስብሰባ መሰረዙ ተነግሯል።

የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አረጋ ሱፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ውይይቱ የተሰረዘው ኦሮሚያን ወክለው በምክር ቤቱ የሚገኙ የፓርላማ አባላት እና በስብሰባው ላይ የተገኙ ሌሎች ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ወገኖች ባነሱት ተቃውሞ ነው። የዚህ የልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ጉዳይ በ2009 ዓ.ም ለምክር ቤቱ በቀረበበት ሰዓት የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብ በስፋት እንዲወያይበት በሚል አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር።

“በዛሬው ስብሰባም ተሳታፊዎች ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል ‘የኛ ሕዝብ ተፈናቅሏል፤ የተፈናቀሉት ሰዎች ልጆች በረሃብ እየተቸገሩ፣ ሌሎች ደግሞ እየሞቱ ስለሆነ የተረጋጋ አዕምሮ ሲኖር ማየት አለብን’ የሚሉት ይገኙበታል’ ይላሉ አቶ አረጋ። እናም ተሳታፊዎቹ በሙሉ በአንድ ኃሳብ ስለተቃወሙ ስብሰባውን የጠራው ኮሚቴ ምክክሩን ለሌላ ጊዜ እንዳስተላለፈው ተናገረዋል። በስብሰባው ላይ ኦሮሚያ ክልል መንግሥትን በመወከል የተገኘ ባለሥልጣን አልነበረም።

በጨለንቆ በመከላከያ ሠራዊት ስለተገደሉ ንፁሃን ዜጎች እና በሀገሪቱ ውስጥ እየታየ ባለው የሰላም ችግር ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከተጠየቁ በኋላ ምክር ቤቱ በስራ ላይ አልነበረም የሚሉት አቶ አረጋ የምክክር ጥሪውን እንደ ቀሪው ህዝብ ሁሉ ከመገናኛ ብዙኃን እንደሰሙ ይናገራሉ።

“ምክክሩ እንዲቀር ያደረጉት ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው” የሚሉት ደግሞ ሌላኛው የምክር ቤት አባል አቶ አንዳርሳ መገርሳ ናቸው። “ሕዝቡ ቀድሞ በጉዳዩ ላይ ሳይመክር መቅረቱ እና በአሁኑ ወቅት ከዚህ የበለጠ አጣዳፊ ልንወያይባቸው የሚገባን ጉዳዮች መኖራቸው ናቸው” ብለዋል። ለዚህም ጥያቄ የተሰጠው መልስ ከዚህ ምክክር በኋላ ሕዝቡን ለማወያየት የሚከለክል ነገር የለም የሚል ቢሆንም ጉዳዩ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ስለገጠመው ምክክሩ ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ይናገራሉ።

በተመሳሳይ የኦሮሚያ ኮሚዩኒሽን ጋዳዮች ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ለክልሉ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር አይደለም ሲሉ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ፎቶ ፋና ብሮድካስት

Related stories   ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ