ሕወሓት-ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆናጠጠ ጀምሮ ወደ ውጪ እንጂ ወደ ውስጥ ለማየት ያልታደለ ወይም የማይፈልግ ድርጅት ሆኖ ቆይቷል፡፡ እኔ እንኳ ከማስታውሳቸው የጦስ ዶሮዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

– የደርግ መንግስት ርዝራዦች/ አኩራፊዎች- (ስልጣን በያዘ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት)
– ቦናፓርቲስቶችና ጥገኞች (በ93 ክፍፍል ወቅት)
– ነውጠኞችና አደገኛ ቦዘኔዎች (በ97 ምርጫ ማግስት)
– የዱሮ ሥርዓት ናፋቂዎች (በ97 ምርጫ ማግስት)
– በሻዕቢያ መንግስት የሚደገፉ የእስልምና አክራሪዎች (ከሱማሊያው የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረት ጋር ከተደረገው ጦርነት በኋላ)
– የሻዕቢያ መንግስት ተላላኪዎች (ራሳቸውን ግንቦት 7/ አርበኞች ግንባር/ ኦነግ እያሉ የሚጠሩ ድርጅቶች)
– የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች (ከግድቡ መገንባት በኋላ)
– ትምክህተኞች፣ ጠባቦች፣ አክራሪዎችና ፀረ አንድነት ኃይሎች (ከኦሮማራ ንቅናቄ በኋላ)
– በውጪ ሀገራት ቁጭ ብለው በማህበራዊ ሚዲያዎች የጥላቻ መልዕክቶች የሚያሰራጩ አካላት (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ)
– ፈጣን ዕድገቱ በራሱ የፈጠረው ችግር (ከቀለዱ አይቀር እንዲህ ነው)
– አመራሩ በተገኘው ልማት በመርካት ለተሻለ ውጤት አለመነሳት (ይችም የምትገርም ቀልድ ነች)
– አመራሩ ከፈጣን ዕድገቱ ጋር መሄድ አለመቻሉ
– የከፍተኛ አመራሩ ችግር ……… ወዘተ

ሠበብ ሳያልቅበት የሁሉም ችግሮች ምንጭ ራሱ ሕወሓት-ኢህአዴግ መሆኑን ቢቀበል ይሻለው ነበር፡፡

እንዘጭ እምቦጭ
Related stories   ሆሆሆ- በቅሎ ወለደች !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *