ዓመታዊዉን የቅዱስ ገብርኤል በዓል የሚያከብሩ ምዕመናንን አሳፍረው ከአዲስ አበባ ወደ ቁልቢ ይጓዙ የነበሩ አራት አዉቶብሶች ትናንት አሰበተፈሪ አጠገብ አርበረከቴ ሲደርሱ በአካባቢዉ ነዋሪዎች መደብደባቸውን የተመድ አስታወቀ። ድርጅቱ ለሰራተኞቹ በሚያሰራጨዉ የደሕንነት ማስጠንቀቂያ እንዳለዉ አደጋዉ የደረሰባቸው አዉቶብሶች የሠላም ባስ ኩባንያ ነበሩ።

ጃዋር መሐመድ በፌስ ቡክ ገጹ ድብደባ መፈጸሙን በማስተባበል ዘግባው ሙያዊ የማታራት ስራን ያላካተተ እንደሆነ ተችቷል። “ያገኛችሁትን መረጃ አጣሩት ፣መጠነኛም ቢሆን የጋዜጠኛነት ስራችሁን ስሩ” ሲል በፌስ ቡክ ገጹ አስተያየቱን በተቃውሞ የጀመረው ጃዋር መሐመድ፣ ወጣቶቹ ወደ ቁልቢ የሚጓዙ ምዕመናን ኢላማ እንዳላደረጉ ገልጿል። ዋናው ኢላማ በኦሮሚያ እንዳይንቀሳቀስ እገዳ የተጣለበት የህወሃት ንብረት በሆኑ አውቶቡሶች ላይ ብቻ መሆኑንንም አመልክቷል። ወጣቶቹ ተሳፋሪዎች በትክክል ለጸሎት የሚጓዙ መሆናቸውን እንኳን እንደማያውቋቸው ገልጿል። ውጣቶቹ የተለመደውን ተግባራቸውን ፈጽመዋል ነው ጃዋር ያለው። አያይዞም ለተሳፋሪዎቹንም ደህንነት በማሰብ እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ከአውቶቡሱ እንዲወጡ አድርገዋቸዋል ብሏል። ሰላም አውቶቡስ ላለፉት አራት ወራት በዚያ አቅጣጫ መጓዝ ማቆሙን ያስታወሰው ጃዋር፣ ጉዳዩን የተቀነባበረ ብሎታል።

የቁልቢ ገብርኤልን አመታዊ በዓል የሚያከብሩ ምዕመናን አሳፍረዉ ከአዲስ አበባ ወደ ቁልቢ በመጓዝ ላይ በነበሩ አውቶቡሶች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል ተባለ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሰራተኞቹ ባሰራጨው የጸጥታ ማስጠንቀቂያ ማስታወሻ እንደገለጠው አውቶቡሶቹ በተቃዋሚዎች ጥቃት የተፈጸመባቸው ጭሮ አቅራቢያ በምትገኘው አርባረከቴ ከተማ አዉራ መንገድ ላይ ነው።

ተቃዋሚዎቹ መንገደኞቹን በማስወረድ አራቱን አውቶቡሶች በድንጋይ መደብደባቸውን እና የአብዛኞቹ መስታወቶች መውደማቸውን ማስታወሻው ገልጧል። በመረጃው መሰረት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ተቃዋሚዎቹ አውቶቡሶቹን በእሳት ከማጋየታቸው በፊት ወታደራዊ ኃይል ደርሶ እንደበተናቸውም አትቷል።

አውቶቡሶቹ በወታደራዊው ኃይል ታጅበው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል ተብሏል።ሰላም ፤ ስካይ እና ኢትዮ ባስ ከተባሉት ውጪ ሌሎች በነፃነት ይጓዙ እንደነበር ይኸው ማስታወሻ አትቷል። ሶስቱ የሕዝብ ማመላለሻ ኩባንዮች የገዢው ፓርቲ ባለሥልጣናት ንብረቶች ናቸው በሚል ለጥቃት መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያሰራጨው ማስታወሻ የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ አትቷል። 

ቁልቢ ደርሶ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰዉ ባልደረባችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደሚለዉ ደግሞ አዲስ አበባን ከሐረር እና ድሬዳዋ ጋር የሚያገናኘዉ መንገድ ዛሬም ዉጥረት እና ሥጋት እንደሰፈነበት ነዉ። ነጋሽ መሐመድ ዮሐንስን ዛሬ ከቀትር በኋላ በስልክ አነጋግሮት ነበር።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  ነጋሽ መሐመድ

DW (Amharic) do a little journalistic work to check your facts. The youth were not targeting the Qulubi pilgrims. They were targeting Weyane owned Selam Bus which has been banned from Oromia. The youth did not even know the passengers were pilgrims. Even then they did the usual caution. They disembarked the passengers to ensure their safety before attacking the buses. Note that Selam Bus had stopped traveling on that route for last 4 months until this trip which means its a set up

Jawar Mohammed

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *