የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ለምስክርነት ተጠርተው ሳየገኙ የቀሩት እነ አቶ ለማ መገርሳ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው መጥየቃቸው ታወቀ። አዲስ ሃሳብ እናራምዳለን የሚሉት የኦህዴድ መሪዎች፣ “ወገኖቼ ላይ በሚደርሰው ጫና ሳቢያ ስራ በቃኝ” ያሉት አባዱላ ገመዳ ለምስክርነቱ ቅድሚያ አለመስጠታቸው ተቃውሞ አሰነዘረባቸው።

በኢትዮጵያ አሁን ባለው የፍርድ ሂደት እስረኞችን ያለበቂ ማስረጃ ፍርድ ቤት እያመላለሱ ማሰቃየት የተለመደ መሆኑንን ያመለክቱ ለዛጎል እንዳሉት፣ የኦህዴድ መሪዎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማክበር ተውዳሽ መሆን እንዳለባቸው አመልክተዋል። በሌላም በኩል ተራማጅነታቸውን የሚያውቁትን በመናገር በተግባር ማሳየት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

በእስር ቤት የሚሰማውን ሮሮና በከሳሽ አቃቤ ህግ የሚቀርበውን ወሃ የማያነሳ ምክንያት የሚከታተሉ በበኩላቸው “ይህ አሁን የሚደረገው ሁሉ ቂምን የሚያከማች፣ አለመግባባትን የሚያሰፋ፣ ከመሆኑም በላይ ሌላ ትርፍ የለውም” ህዝብ በአመለካከታቸው ዛቢያ የታሰሩ ንጹሃን ዜጎች እንዲፈቱለት በሚጠይቀበትና ህይወቱን በመክፍል እያሳየ ባለበት ወቅት በረባ ባልረባ እስረኞች ላይ የስቃይ ዘመቻ ማጠናከር ቢቆም የተሻለ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

“አራቱ የኦሮሚያ ባለስልጣኖች ስራ ሊበዛባቸው ቢችልም ተከሳሾች ላይ እየደረሰ ካለው ችግር አንጻር፣ ምንም ይሁን ምን የፍርድ ሂደቱ እንዲቀላጠፍ እገዛ ማድረግ ይገባቸዋል። ተራማጅነትም የሚለካው በዚሁ ነው” በማለት በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች የጻፉም አሉ።

ከተከሳሾች ውስጥ አቶ በቀለ ገርባ የጠቀሷቸው የመከላከያ ምስክሮች የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣ በጽህፈት ቤታቸው አማካይነት በስራ ብዛት / ስብሰባ መሆኑ ነው/ ለምስክርነት እንደማይመጡ ከማሳወቃቸው ውጪ ተለዋጭ ቀጠሮ ስለመጠየቃቸው የተባለ ነገር የለም። የተቀሩት አቶ ለማ መገርሳ ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ ጫልቱ ናኒ አባዱላ ገመዳ ግን ተለዋጭ ቀጠሮ መጠየቃቸው የሚኮነን ባይሆንም ፣ ለመመስከር ፈቃደኛነታቸውን ማሳየታቸው ከአቶ ሃይለማሪያም ይልቅ የተሻሉ አስብሏቸዋል።

ከኦህዴድ ፅህፈት ቤት የተላከ ደብበዳቤ 

ደብዳቤውም “በቀን 7/3/2010 ዓመተ ምህረት በተፃፈልን ደብዳቤ የክልላችን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ለመከላከያ ምስክርነት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መታዘዛቸው ይታወሳል። በመሆኑም፦

1.አ ቶ ለማ መገርሳ 

2. ዶክተር አብይ አህመድ 

3. አቶ አባዱላ ገመዳና 

4. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በአስቸኳይ ሀገራዊ ስብሰባ ምክንያት ቀርበው መመስከር ስለማይችሉ የተከበረው ፍርድ ቤት ችግሩን በመረዳት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ እንዲያመቻችልን እና ቀርበው እንዲመሰክሩ እንዲደረግልን የተለመደ ትብብራቹሁን በአክብሮት እንጠይቃለን” ይላል። ችሎቱም በደረሱት ድብዳቤዎች ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 27/2010 ዓ.ምተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ቀሪ ምስክሮችን ለማድመጥ ከየካቲት 5- 9 ቀን 2010 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተመሳሳይ ዜና በአቶ በቀለ ገርባ ለምስክርነት የጠሩትና በወህኒ ቤት የሚገኘው

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

የድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አንዱአለም አራጌን አቶ በቀለ ገርባ ምስክር አድርገው ቢጠሩትም ወህኒ ቤቱ “አላቀርብም” የሚል መልስ ሰጥቷል። በምክንያትም ያቀረቡት “አቶ አንዱዋለም ከባድ ፍርደኛ በመሆኑ ነው” የሚል ነው። የቃሊቲ እስር ቤት ሃላፊዎች “ፍርድ ቤቱም ለአቶ አንዱአለም አራጌ መጥሪውያው እንዲደርሰው በፖስተኛ ተላከ እንጂ አቅርቡት አላልንም” በማለት ለችሎት ተናገረዋል።  አቶ አንዷለም አራጌ ትንታግ ፖለቲከኛና የጸና አቋም አላቸው ከሚባሉት ቅድሚያ የሚሰለፍ እንደሆነ ሰፊ ምስክርፕች አሉት። ለዜናው ግብአት የጌታቸው ሽፈራውን መረጃዎች ተጠቅመናል።

Related stories   ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *