መኮንን ሀብተጊዬርጊስ ብሩ (ዶ/ር)

ከእንግዲህ በኋላ የኢትዬጲያን ሕዝብ የነፃነት ጉዞ ሊያቆም የሚችል ሕገ-እዝጋብሔር ብቻ ቢሆንም የማይቀረዉን ትንሳኤ ግን ሊያንጓትቱ የሚችሉ በርካታ ይሁዳዎች በየቦታዉ አይጠፉም።  ላለፉት አርባ ዓመታት ህወኣቶች ሲያታልሉ፣ ሲዋሹ፣ ሲገድሉ፣ ሲሰርቁ፣ ሲያናቁሩና ሲያሰቃዩ የዘለቁ የእርኩስ መንፈስ መገለጫዎች ናቸዉ። በዘመናቸዉም ሁሉ በጓሮ በር በመግባት የተካኑ ሌቦች በመሆናቸዉም ብዙ ንፁሃንን እያታለሉ ወደ ይሁዳነት መቀየር ችለዋል።

በዶላር ከቸበቸቧቸዉ የደርግ ጦር አዛጆች ጀምሮ እስከ እነ ልደቱ አያሌዉ የቁርስራሽ ተቋዳሾች ድረስ ህወኣት  ሔዋንን አማልሎ ከፈጣሪዋ እንዳጣላትና ልትወርስ ካለችዉም ሄዶም ገነት እንደለያት እባብ  ብዙዎችን አስተዋል። በፓርቲ ላይ ፓርቲ …..በመሪ ላይ መሪ…..በቡድን ላይ ቡድን  እየፈጠሩ በደካማ የሰዉ ልጅ ባህሪ ምክንያት የትዉልድን ሰላማዊና ነፃ ኑሮ በራሳቸዉ በባለቤቶቹ እያኮላሸ እዚህ ደርሰዋል። ህወኣት አሁንም ጠገበ በተባለዉ ኦሕዴድ ላይ ሌላ የተራበ ኦሕዴድ….ኢዬጲያዊነትንና ታላቅነትን እየሰበከ ባለዉ. ለማ መገርሳ ላይ ሌላ ልደቱን መሳይ ይሁዳ ለመቅጠር ወይም ለመመልመል የእባብነት ባህሪዉን እንደሚጠቀም  ሁሉም ልብ ሊለዉ ይገባል።

ህወኣት ጊዜዉ ያለፈበትና ፓለቲካዊ ሕይወቱ ያበቃ  የወንበዴዎች ጥርቅም ነዉ። ህወኣት እንደ እባብ ተለሳልሶ የሚናደፍ የእርኩስ መንፈስ ማደሪያ ነዉ። ህወኣት እንደ እስስት ጊዜ እስኪመቻች ድረስ ሌላዉን መስሎ የሚቆይ ተለዋዋጭ ነዉ። በዚህም የዋሁ የኢትዮጲያ ሕዝብ ብዙ ተታሏል።  በመታለሉም በመቼም ጊዜ ታሪኩ ተለማምዶት የማያዉቀዉን ግፍና በደል ያይና ይቀምስ ዘንድ ሆኗል። ንብረቱን በኤፈርትና በመሣሰሉት ተዘርፏል…… የመከላከያና የደህንት ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ማንበብና መፃፍ በሚያስቸግራቸዉ ዱኩማኖች ተነጥቋል……. አየር መንገዱ ……ጉምርኩ …….ኢምባሲዉ……. ቡቲኩ…… በሙሉ ቆርፂ ቆርፂ ብቻ ለሚሉ አስረክቧል። ትናንት የጉራጌ ልጆች በሳቅና ፍቅር ይነግዱበት የነበረዉ መርካቶ ዛሬ እንደ ወልቃይት ጠገዴ የመገበያያ ቋንቋዉ ትግሪኛ መስሏል። ይህን ያህል በእኛ ላይ ሊሰለጥኑ የቻሉት እባብና እስስት በመሆናቸዉ ብቻ ሳይሆን በእኛም መሀል ብዙ ይሁዳዎች በመፈጠራቸዉ ነዉ። ስለዚህ በዚህ ላይ መነጋገርና መፍትሔ ማበጀት አለብን። በተለይም እነለማ መገርሳ እና በተወሰነ መልኩ እነደጉ የጀመሩትን ጎዳና ሊያደናቅፍ የሚግደረደር አባ ዱላን የመሰለ ኦሮሞ አልያም አለምነህ መኮንንን የመሰለ የተሸጠ አማራ ስለማይጠፋ በዚህ ላይ መስራት ያስፈልጋል።

ህወኣት በሴይጣናዊ መንፈስ ስለሚመራ ሁሌም ለጥፉት ያሴራል። የኢትዮጲያ ሕዝብ መረዳት ያለበት ከእርኩስ መንፈስ ጋር ማሴር መጨረሻዉ ጥፋት መሆኑን ነዉ። ማስረጃ ከፈለጋችሁ ዛሬ በየቦታዉ በህወኣት ሴይጣናዊ ሴራና በበርካታ ይሁዳዎች ፈቃድ ተኮላሽተዉ የሚገኙትን ጠይቁ……. ኦነግ …….ቅንጅት …….አንድነት……ልደቱ….. ታምራት ላይኔ ……ነጋሶ ጊዳዳ…….ጁነዲን ……..ወዘተ። በመሆኑም  ይህን መሰሉን የህወኣት አፍራሽ እርምጃ ይጠነቀቅ ዘንድ ስመክር ሙሁራንም ይህን የህወኣት ባህሪ እንዴት መቋቋም ይችላል የሚለዉን ያመላክቱ ዘንድ በመጠየቅ ነዉ።

ነገሮችን አለማወቅ ወይም አለመረዳት የችግሮች ወይም የጥፋት ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ ኦሕዴድም ይሁን ብአዴን የህወኣትን እንቅስቃሴ ለማወቅ የሚጥሩትን ያህል አጠገባቸዉ ያሉትንም በደንብ ማዉቅ  ያስፈልጋቸዋል። ለዚህ ደግሞ  የተለያዩ የደህንነት ማዋቅር ሊያቋቁሙ ያስፈልጋቸዋል። እንደ ክልል አመራርነታቸዉ ክልላቸዉን መቆጣጠር አለባቸዉ። በጣት በሚቆጠሩ ሰዎቾ የሚመራ ሁለት ወይም ሶስት እርስ በእርስ የማይተዋወቁ የደህንነት ሴሎች ሊዋቀሩ ቢችሉና ተጠሪነታቸዉ ለሁለት ወይም ሶስት  ለክልሉ  ከፍተኛ አመራሮች ቢሆን ብዙ አደጋ ሊከላከሉ ይችላሉ። በዚህም ዘዴ ህወኣትንም ይሁን ይሁዳ ሊሆኑ የሚፈቅዱትንም ባንዳና ተላሎች መመከት ይቻላል።ሌላዉና ወሳኙ ተግባር ሕዝቡ ነፃነቱን አዉቆ ይጠይቅ ዘንድ ዉስጥ ለዉስጥ ማደራጀት ነዉ። ህወኣት እስረኛ እፈታለሁ እንዲል ያደረገዉ የለማ መገርሳ አልያም የደጉ ቁርጠኝነት ብቻ አይደለም…. ይልቁንም የሕዝቡ ግፊት ነዉ ። ስለዚህ የሁለቱም ክልል አመራሮች የበለጠ ይጠነክሩ ዘንድ ከሕዝባቸዉ በተለይም መሣሪያ ከያዘዉ ሃይል ጋር መናበብ አለባቸዉ። ሌላዉና በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልገዉ ግን ይሁዳ ሊሆኑ ከህወኣት ጋር በሚሞዳሞዱ ግለሰቦች ላይ ሊወሰድ የሚችል የማያዳግም ቅጣት አኳያ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ነዉ። ቄሮ እና ፋኖን የትግሉ አካል ማድረግ እዚህ ጋ ይጠቅማል።

መልካምም ይሁን እርኩስ መንፈስ ሰዉ እራሱ በፈቀደዉ መጠን ይሰለጥንበት ዘንድ ይሆናል። ስለዚህ ከዓዲዎች ከሀገር አይበልጡምና ለሚመለከተዉ አካል አሳልፎ መስጠት ከጥፋት ያድናል።

ኢትዬጲያ ለዘላለም ትኑር።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *