ስለ ‘’ወንበር’’
ስንጽፍ….’’ስልጣን ነዉ’’ እያሉ
ስለ ‘’መንገድ’’
ስንጽፍ….’’ስደት’’ ነዉ እያሉ
ስለ ‘’መጮህ’’
ስንጽፍ….’’አመጽ’’ ነዉ እያሉ


ስለ ‘’መሳቅ ስንጽፍ’’….’’ምጸት
ነዉ’’ እያሉ
ቅኔ ሳንናገር ቅኔ እያናገሩ
በብረት ካቴና እኛን አሳሰሩ
መታሰሩ ሳያንስ…..
አስበን ያልነዉን አስበዉ
ሳይሰሙ
ቃል እየፈጠሩ
ፊደል እየጫሩ
በአቦ ሰጡኝ ግምት ያላልነዉን
ሲሉ
እኛን አሰቀሉ እኛን አስገደሉ
መገደሉም ሳያንስ መሰቀሉም
ሳያንስ
ለወጭ ወራጁ አጉልተዉ
እንዲታይ
መቃብራችን ላይ
‘’በማያገባቸዉ ገብተዉ
ተቀጠፉ’’
የሚል ሞት ለጠፉ::
.
.በሰለሞን ሳህለ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *